ሮሜ 5:19-21
ሮሜ 5:19-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በአንድ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኀጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንድ ሰው መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ። ኦሪትስ ኀጢአትን ታበዛት ዘንድ መጣች፤ ኀጢአትም ከበዛች ዘንድ የእግዚአብሔር ጸጋ በዛች። ኀጢአትም ሞትን እንደ አነገሠችው እንዲሁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ጸጋ ጽድቅን ለዘለዓለም ሕይወት ታነግሠዋለች።
Share
ሮሜ 5 ያንብቡሮሜ 5:19-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኀጢአተኞች እንደ ሆኑ፣ በአንዱ ሰው መታዘዝ ደግሞ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ። ሕግ በመምጣቱ መተላለፍ በዛ፤ ነገር ግን ኀጢአት በበዛበት ጸጋ አብልጦ የተትረፈረፈ ሆነ፤ ይህም የሆነው ኀጢአት በሞት እንደ ነገሠ ሁሉ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ደግሞ የዘላለም ሕይወት ይገኝ ዘንድ ጸጋ በጽድቅ እንዲነግሥ ነው።
Share
ሮሜ 5 ያንብቡሮሜ 5:19-21 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ። በደልም እንዲበዛ ሕግ ጭምር ገባ፤ ዳሩ ግን ኃጢአት በበዛበት፥ ኃጢአት በሞት እንደ ነገሠ፥ እንዲሁ ደግሞ ጸጋ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣ በጽድቅ ምክንያት ለዘላለም ሕይወት ይነግሥ ዘንድ፥ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በለጠ።
Share
ሮሜ 5 ያንብቡ