ሮሜ 3:27-31
ሮሜ 3:27-31 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ታዲያ ትምክሕት ወዴት ነው? እርሱማ ቀርቷል። በየትኛው ሕግ? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፤ በእምነት ሕግ ነው እንጂ። ማንም ሰው ሕግን በመፈጸም ሳይሆን፣ በእምነት እንደሚጸድቅ እናረጋግጣለን። እግዚአብሔር የአይሁድ አምላክ ብቻ ነውን? የአሕዛብስ አምላክ አይደለምን? አዎን፤ የአሕዛብም አምላክ ነው፤ የተገረዘውን በእምነት፣ ያልተገረዘውንም በዚያው እምነት የሚያጸድቅ አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነውና። ታዲያ እንዲህ ከሆነ ከእምነት የተነሣ ሕግን ዋጋ የሌለው እናደርግ ይሆን? ፈጽሞ አይደረግም፤ ሕጉን እናጸናለን እንጂ።
ሮሜ 3:27-31 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ትምክሕት ወዴት አለ? እርሱ ቀርቶአል፤ በየትናውስ ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፤ በእምነት ሕግ ነው እንጂ። ሰው የኦሪትን ሥራ ሳይሠራ በእምነት እንዲጸድቅ እናውቃለንና። በውኑ እግዚአብሔር ለአይሁድ ለብቻቸው ነውን? ለአሕዛብስ አይደለምን? አዎን፥ ለአሕዛብም ነው፤ የተገዘረውን በእምነት የሚያጸድቅ፥ ያልተገዘረውንም በእምነት የሚያጸድቀው እርሱ አንዱ እግዚአብሔር ነውና። እንግዲህ በእምነት ኦሪትን እንሽራለን? አንሽርም፤ ኦሪትን እናጸናለን እንጂ።
ሮሜ 3:27-31 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ትምክህት እንግዲህ ወዴት ነው? እርሱ ቀርቶአል። በየትኛው ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፥ በእምነት ሕግ ነው እንጂ። ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለንና። ወይስ እግዚአብሔር የአይሁድ ብቻ አምላክ ነውን? የአሕዛብስ ደግሞ አምላክ አይደለምን? አዎን፥ የተገረዘን ስለ እምነት ያልተገረዘንም በእምነት የሚያጸድቅ አምላክ አንድ ስለ ሆነ የአሕዛብ ደግሞ አምላክ ነው። እንግዲህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? አይደለም፤ ሕግን እናጸናለን እንጂ።
ሮሜ 3:27-31 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እንግዲህ የምንመካበት ነገር ምን አለ? በምንም አንመካም! የማንመካበትስ ምክንያት ምንድን ነው? ሕግን ስለምንፈጽም ነውን? አይደለም፤ ነገር ግን በእምነት ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ሰውን የሚያጸድቀው፥ ሰው የሕግን ሥራ በመፈጸሙ ሳይሆን በእምነት መሆኑን እንገነዘባለን። ወይስ እግዚአብሔር የአይሁድ ብቻ አምላክ ነውን? የአሕዛብስ አምላክ አይደለምን? በእርግጥ የአሕዛብም አምላክ ነው። እግዚአብሔር አንድ ነው፤ አይሁድንም ሆነ አሕዛብን በእምነት የሚያጸድቅ እርሱ ነው። ታዲያ፥ በእምነት ምክንያት ሕግን እንሽራለን ማለት ነውን? አይደለም፤ ይልቅስ ሕግን አጥብቀን እንይዛለን።
ሮሜ 3:27-31 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ስለዚህ ትምክህት ወዴት ነው? እርሱ ቀርቶአል። በየትኛው ሕግ? በሥራ ነውን? አይደለም፤ ነገር ግን በእምነት ሕግ ነው። ሰው ሕግ ከሚያዘው ሥራ ውጭ በእምነት እንደሚጸድቅ እናምናለንና። ወይስ እግዚአብሔር የአይሁድ ብቻ አምላክ ነውን? የአሕዛብስ አምላክ አይደለምን? አዎን የአሕዛብም አምላክ ነው፤ የተገረዘን ስለ እምነት ያልተገረዘንም በእምነት የሚያጸድቅ አንድ አምላክ አለና። ስለዚህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? በጭራሽ! ነገር ግን ሕግን እናጸናለን።