የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሮሜ 13:8-14

ሮሜ 13:8-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እርስ በር​ሳ​ችሁ ከመ​ዋ​ደድ በቀር ለማ​ንም ዕዳ አይ​ኑ​ር​ባ​ችሁ፤ ባል​ን​ጀ​ራ​ውን የወ​ደደ ግን ሕግን ሁሉ ፈጸመ። በኦ​ሪት እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “አታ​መ​ን​ዝር፤ አት​ግ​ደል፤ አት​ስ​ረቅ፤ በሐ​ሰት አት​መ​ስ​ክር፥ አት​መኝ፤” ደግሞ ሌላ ትእ​ዛዝ አለ፤ ነገር ግን የሁ​ሉም ራስ “ ባል​ን​ጀ​ራ​ህን እንደ ራስህ ውደድ” የሚ​ለው ነው። ባል​ን​ጀ​ራ​ዉን የሚ​ወድ በባ​ል​ን​ጀ​ራዉ ላይ ክፉ ሥራ አይ​ሠ​ራም፤ ስለ​ዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው። ከእ​ን​ቅ​ልፍ የም​ት​ነ​ቁ​በት ጊዜ እንደ ደረሰ ዕወቁ፤ ካመ​ን​በት ጊዜ ይልቅ መዳ​ና​ችን ዛሬ ወደ እና ደር​ሳ​ለ​ችና። ሌሊቱ አል​ፎ​አል፤ ቀኑም ቀር​ቦ​አል። እን​ግ​ዲህ የጨ​ለ​ማን ሥራ ከእና እና​ርቅ፤ የብ​ር​ሃ​ን​ንም ጋሻ ጦር እን​ል​በስ። በቀን እን​ደ​ሚ​ሆን በጽ​ድቅ ሥራ እን​መ​ላ​ለስ፤ በዘ​ፈ​ንና በስ​ካር፥ በዝ​ሙ​ትና በመ​ዳ​ራ​ትም አይ​ሁን፤ በክ​ር​ክ​ርና በቅ​ና​ትም አይ​ሁን። ነገር ግን ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ልበ​ሱት፤ የሥ​ጋ​ች​ሁ​ንም ምኞት አታ​ስቡ።

ሮሜ 13:8-14 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፤ ሊኖርባችሁ የሚገባ ዕዳ እርስ በርስ መዋደድ ብቻ ይሁን፤ ሰውን የሚወድ ሕግን ይፈጽማል። “አታመንዝር፤ አትግደል፤ አትስረቅ፤ የሌላ ሰው የሆነውን ማናቸውንም ነገር አትመኝ” የሚሉት ትእዛዞችና ሌሎችም ትእዛዞች ሁሉ “ሰውን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ” በሚለው በአንዱ ትእዛዝ ተጠቃለው ይገኛሉ። ሰውን የሚወድ ሁሉ በሚወደው ላይ ክፉ ነገር አያደርግበትም፤ ስለዚህ ሰውን የሚወድ ሕግን ሁሉ ይፈጽማል ማለት ነው። እንግዲህ ከእንቅልፍ የምትነቁበት ሰዓት አሁን መድረሱን ዕወቁ፤ በፊት ካመንበት ጊዜ ይልቅ አሁን የምንድንበት ቀን ይበልጥ ወደ እኛ ቀርቦአል። ሌሊቱ እያለፈ ነው፤ ቀኑም ቀርቦአል፤ ስለዚህ በጨለማ የሚሠራውን ሥራ እንተው፤ የብርሃንን የጦር መሣሪያ እንልበስ። ቅጥ ባጣ ፈንጠዝያ፥ በስካር፥ በዝሙትና በመዳራት፥ በጭቅጭቅና በምቀኝነት ሳይሆን በቀን ብርሃን እንደሚኖሩ ሰዎች በጨዋነት እንመላለስ። ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት እንጂ የሥጋችሁን ፍላጎት ለማርካት አታስቡ።