ሮሜ 10:9-11
ሮሜ 10:9-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን ለይቶ እንደ አስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህ። በልቡ የሚያምን ይጸድቃልና፤ በአፉም የሚመሰክር ይድናልና። መጽሐፍ፥ “የሚያምንበት ሁሉ አያፍርም” ብሎአል።
ያጋሩ
ሮሜ 10 ያንብቡሮሜ 10:9-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“ኢየሱስ ጌታ ነው” ብለህ በአፍህ ብትመሰክር፣ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን፣ ትድናለህ። የምትጸድቀው በልብህ አምነህ ነው፤ የምትድነውም በአፍህ መስክረህ ነውና። መጽሐፍ እንደሚለው፣ “በርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም።”
ያጋሩ
ሮሜ 10 ያንብቡሮሜ 10:9-11 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። መጽሐፍ፦ በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላልና።
ያጋሩ
ሮሜ 10 ያንብቡሮሜ 10:9-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ኢየሱስ ጌታ መሆኑን በአፍህ ብትመሰክርና እግዚአብሔር ከሞት እንዳስነሣውም በልብህ ብታምን ትድናለህ። ሰው በልቡ ሲያምን ይጸድቃል፤ በአፉም ሲመሰክር ይድናል፤ በቅዱስ መጽሐፍ እንደ ተጻፈው፦ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም።”
ያጋሩ
ሮሜ 10 ያንብቡ