መዝሙር 81:4-7
መዝሙር 81:4-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ብቸኛውንና ችግረኛውን አድኑ፤ ከኃጥኣንም እጅ አስጥሉአቸው። አያውቁም፥ አያስተውሉምም፤ በጨለማ ውስጥም ይመላለሳሉ፤ የምድር መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ። እኔ ግን እላለሁ፥ “አማልክት ናችሁ፥ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ፤” እናንተ ግን እንደ ሰው ትሞታላችሁ፥ ከአለቆችም እንደ አንዱ ትወድቃላችሁ።
Share
መዝሙር 81 ያንብቡመዝሙር 81:4-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ይህ ለእስራኤል የተሰጠ ሥርዐት፣ የያዕቆብም አምላክ ድንጋጌ ነውና። ሙሉ ለሙሉ ግብፅን ለቅቆ በወጣ ጊዜ፣ ይህን ለዮሴፍ ደነገገለት፤ በማላውቀውም ቋንቋ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ትከሻውን ከሸክም ገላገልሁት፤ እጁንም ቅርጫት ከመያዝ አሳረፍሁ። በመከራህ ጊዜ ጠራኸኝ፤ እኔም ታደግሁህ፤ በነጐድጓድ መሰወሪያ ውስጥ መለስሁልህ፤ በመሪባ ውሃ ዘንድ ፈተንሁህ። ሴላ
Share
መዝሙር 81 ያንብቡመዝሙር 81:4-7 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ይህ ለእስራኤል የተደነገገ፥ የያዕቆብ አምላክ የሰጠው ሥርዓት ነው። እርሱ ይህን ትእዛዝ ለዮሴፍ ልጆች የሰጣቸው ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ ነው። ያልታወቀ ድምፅ እንዲህ ሲል እሰማለሁ፤ “እኔ ከትከሻችሁ ሸክምን አወረድኩላችሁ፤ የጡቡን ሸክም ከላያችሁ እንድትጥሉት አደረግሁ፤ በመከራ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ ጠራችሁኝ፤ እኔም አዳንኳችሁ፤ ከመሰወሪያ ስፍራዬ፥ ከሞገድ ውስጥ ሰማኋችሁ፤ በክርክር ምንጮች አጠገብ ፈተንኳችሁ።
Share
መዝሙር 81 ያንብቡ