መዝሙር 37:7-11
መዝሙር 37:7-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ነፍሴ ስድብን ጠግባለችና፥ ለሥጋዬም ድኅነትን አጣሁ። ታመምሁ እጅግም ተሠቃየሁ፥ ከልቤም ኀዘን የተነሣ እጮኻለሁ። አቤቱ፥ ፈቃዴ ሁሉ በፊትህ ነው፥ ጩኸቴም ከአንተ አይሰወርም። ልቤ ደነገጠብኝ፥ ኀይሌም ተወኝ፥ የዐይኖቼም ብርሃን ፈዘዘብኝ። ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ባላጋራ ሆኑኝ፥ ከበውም ደበደቡኝ፥ ዘመዶቼም ተስፋ ቈርጠው ተለዩኝ።
መዝሙር 37:7-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በእግዚአብሔር ፊት ጸጥ በል፤ በትዕግሥትም ተጠባበቀው፤ መንገዱ በተቃናለት፣ ክፋትንም በሚሸርብ ሰው ልብህ አይሸበር። ከንዴት ተቈጠብ፤ ቍጣንም ተወው፤ ወደ እኵይ ተግባር እንዳይመራህ አትከፋ። ክፉ ሰዎች ይጠፋሉና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን ምድርን ይወርሳሉ። ለአፍታ እንጂ፣ ክፉ ሰው አይዘልቅም፤ ስፍራውንም ብታሥሥ አታገኘውም። ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤ በታላቅ ሰላምም ሐሤት ያደርጋሉ።
መዝሙር 37:7-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በትዕግሥት ጸንተህ እግዚአብሔር የሚያደርገውን ለማየት ተጠባበቅ፤ ሌሎች ሰዎች ክፉ ሐሳባቸው ቢሳካላቸው አትበሳጭ። ቊጣ ወደ ክፉ ነገር ስለሚያመራ። ራስህን ከቊጣ መልስ፤ ከንዴትም ተጠበቅ፤ ክፉ አድራጊዎች ይገደላሉ፤ በእግዚአብሔር የሚታመኑ ግን ምድርን ይወርሳሉ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ክፉ አድራጊዎች ፈጥነው ይጠፋሉ፤ ብትፈልጋቸው እንኳ አታገኛቸውም። ትሑቶች ምድርን ይወርሳሉ፤ ብልጽግናንና ሰላምን በማግኘት ይደሰታሉ።