መዝሙር 37:3-6
መዝሙር 37:3-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከቍጣህ ፊት የተነሣ ለሥጋዬ ድኅነት የለውም፤ ከኀጢአቴም ፊት የተነሣ ለአጥንቶቼ ሰላም የላቸውም። ኀጢአቴ ከራሴ ጠጕር በዝቷልና፥ እንደ ከባድ ሸክምም በላዬ ከብዶአልና። ከስንፍናዬም ፊት የተነሣ አጥንቶቼ ሸተቱ፥ በሰበሱም፤ እጅግ ጐሰቈልሁ፥ ጐበጥሁም፥ ሁልጊዜም በትካዜ እመላለሳለሁ፤
Share
መዝሙር 37 ያንብቡመዝሙር 37:3-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በእግዚአብሔር ታመን፤ መልካምንም አድርግ፤ በምድሪቱ ተቀመጥ፤ ዘና ብለህ ተሰማራ። በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፤ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል። መንገድህን ለእግዚአብሔር ዐደራ ስጥ፤ በእርሱ ታመን፤ እርሱም ያከናውንልሃል፤ ጽድቅህን እንደ ብርሃን፣ ያንተን ፍትሕ እንደ ቀትር ፀሓይ ያበራዋል።
Share
መዝሙር 37 ያንብቡመዝሙር 37:3-6 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በእግዚአብሔር ታምነህ መልካምን አድርግ፤ በምድሪቱም በሰላም ትኖራለህ። በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፤ እርሱም የልብህን ፍላጎት ሁሉ ይሰጥሃል። አካሄድህን ለእግዚአብሔር ዐደራ ስጥ፤ በእርሱ ታመን፤ እርሱም ይረዳሃል። ጽድቅህን እንደ ብርሃን የጉዳይህንም ትክክለኛነት እንደ ቀትር ፀሐይ ያበራዋል።
Share
መዝሙር 37 ያንብቡ