መዝሙር 33:1-3
መዝሙር 33:1-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔርን ሁልጊዜ አመሰግነዋለሁ። ምስጋናውም ዘወትር በአፌ ነው። ነፍሴም በእግዚአብሔር ትከብራለች፥ ገሮችም ይስሙ፥ ደስም ይበላቸው። እግዚአብሔርን ከእኔ ጋር ከፍ ከፍ አድርጉት፥ በአንድነትም ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ።
Share
መዝሙር 33 ያንብቡመዝሙር 33:1-3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ጻድቃን ሆይ፤ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ቅኖች ሊወድሱት ይገባቸዋል። እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፤ ዐሥር አውታር ባለውም በገና ዘምሩለት። አዲስ መዝሙር ዘምሩለት፤ በገናውን ባማረ ቅኝት ደርድሩ፤ እልልም በሉ።
Share
መዝሙር 33 ያንብቡ