መዝሙር 3:1-8
መዝሙር 3:1-8 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔር ሆይ! ጠላቶቼ እንዴት ብዙዎች ናቸው! ብዙዎችም በጠላትነት በእኔ ላይ ተነሥተዋል፤ ብዙ ሰዎች “እግዚአብሔር አያድነውም” እያሉ ስለ እኔ ይናገራሉ። እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን ጋሻዬ ነህ፤ ድልን በማጐናጸፍ ክብርን የምትሰጠኝ አንተ ነህ። ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ እርሱም በተቀደሰ ተራራው ላይ ሆኖ ይሰማኛል። እኔ ተኛሁ፥ አንቀላፋሁም፤ እግዚአብሔር ሌሊቱን ሙሉ ስለ ጠበቀኝ ከእንቅልፌ ተነሣሁ። በዙሪያዬ የከበቡኝን በብዙ ሺህ የሚቈጠሩትን ጠላቶቼን አልፈራቸውም። ጌታ ሆይ! ተነሥ! አምላኬ ሆይ! መጥተህ አድነኝ! የጠላቶቼን መንጋጋ ስበር፤ ጥርሶቻቸውንም አድቅቅ። ማዳን የእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፥ በረከትህ በሕዝብህ ላይ ይሁን።
መዝሙር 3:1-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አቤቱ፥ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ! በእኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው። ብዙ ሰዎች ነፍሴን አልዋት፦ “አምላክሽ አያድንሽም።” አንተ ግን አቤቱ፥ መጠጊያዬ ነህ፤ ክብሬና ራሴን ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ነህ። በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤ ከተቀደሰ ተራራውም ሰማኝ። እኔ ተኛሁ፤ አንቀላፋሁም፤ እግዚአብሔርም አንሥቶኛልና ተነሣሁ። ከሚከብቡኝና በእኔ ላይ ከሚነሡ ከአእላፍ አሕዛብ አልፈራም። ተነሥ፥ አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ አድነኝ፤ አንተ በከንቱ የሚጠሉኝን ሁሉ መትተሃልና፥ የኃጥኣንንም ጥርስ ሰብረሃልና። ማዳን የእግዚአብሔር ነው፥ በረከትህም በሕዝብህ ላይ ነው።
መዝሙር 3:1-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶቼ ምንኛ በዙ! ስንቱስ በእኔ ላይ ተነሣ! ብዙዎች ነፍሴን፣ “እግዚአብሔር አይታደግሽም” አሏት። ሴላ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ዙሪያዬን የምትከልል ጋሻ ነህ፤ ክብሬንና ራሴንም ቀና ቀና የምታደርግ አንተ ነህ። ወደ እግዚአብሔር ድምፄን ከፍ አድርጌ እጮሃለሁ፤ እርሱም ከተቀደሰ ተራራው ይመልስልኛል። ሴላ እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁ፤ እግዚአብሔር ደግፎ ይዞኛልና እነቃለሁ። በየአቅጣጫው የከበበኝን፣ አእላፍ ሕዝብ አልፈራም። እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ! አምላኬ ሆይ፤ ታደገኝ፤ የጠላቶቼን ሁሉ መንጋጋ ትመታለህ፤ የክፉዎችንም ጥርስ ትሰባብራለህ። ማዳን የእግዚአብሔር ነው፤ በረከትህ በሕዝብህ ላይ ይሁን። ሴላ
መዝሙር 3:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
አቤቱ፥ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ! በኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው። ብዙ ሰዎች ነፍሴን፦ አምላክሽ አያድንሽም አልዋት። አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ጋሻዬ ነህ፥ ክብሬና ራሴንም ቀና የምታደርገው አንተ ነህ። በሙሉ ድምጽ ወደ ጌታ እጮሃለሁ፥ ከተቀደሰ ተራራውም ይሰማኛል። እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፥ ጌታም ደግፎኛልና ነቃሁ። የሚከቡኝን አእላፍ ሕዝብ አልፈራም። ተነሥ፥ አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ አድነኝ፥ አንተ የጠላቶቼን መንጋጋ መትተሃልና፥ የክፉዎችንም ጥርስ ሰብረሃልና።