የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 27:1-8

መዝሙር 27:1-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

አቤቱ፥ አም​ላኬ ሆይ፥ ወደ አንተ እጮ​ኻ​ለሁ፤ ቸልም አት​በ​ለኝ። ቸል ብት​ለኝ ግን ወደ ጕድ​ጓድ እን​ደ​ሚ​ወ​ር​ዱት እሆ​ና​ለሁ። በቤተ መቅ​ደ​ስህ እጆ​ችን ባነ​ሣሁ ጊዜ፥ ወደ አንተ የጮ​ኽ​ሁ​ትን የል​መ​ና​ዬን ቃል ስማ። ከኃ​ጥ​ኣን ጋር ነፍ​ሴን አት​ው​ሰ​ዳት፤ ክፋ​ትም በል​ባ​ቸው እያለ ከባ​ል​ን​ጀ​ራ​ቸው ጋር ሰላ​ምን ከሚ​ና​ገሩ ዐመፅ አድ​ራ​ጊ​ዎች ጋር አት​ጣ​ለኝ። እንደ ሥራ​ቸ​ውና እንደ ዐሳ​ባ​ቸው ክፋት ስጣ​ቸው፤ እንደ እጃ​ቸ​ውም ሥራ ክፈ​ላ​ቸው፤ ፍዳ​ቸ​ውን በራ​ሳ​ቸው ላይ መልስ። ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ ወደ እጆ​ቹም ተግ​ባር አላ​ሰ​ቡ​ምና አፍ​ር​ሳ​ቸው፥ አት​ሥ​ራ​ቸ​ውም። የል​መ​ና​ዬን ቃል ሰም​ቶ​ኛ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳ​ቴና መታ​መ​ኛዬ ነው፤ ልቤ በእ​ርሱ ታመነ፥ እር​ሱም ይረ​ዳ​ኛል፤ ሥጋ​ዬም ለመ​ለመ፥ ፈቅ​ጄም አም​ነ​ዋ​ለሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቡ ኀይ​ላ​ቸው ነው፥ ለመ​ሲሑ የመ​ድ​ኀ​ኒቱ መታ​መኛ ነው።

መዝሙር 27:1-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኅኔ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር ለሕይወቴ ዐምባዋ ነው፤ ማንን እፈራለሁ? ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ፣ ክፉዎች ገፍተው በመጡ ጊዜ፣ ጠላቶቼና ባላጋራዎቼ በተነሡብኝ ጊዜ፣ እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ። ሰራዊት ቢከብበኝ እንኳ፣ ልቤ አይፈራም፤ ጦርነት ቢነሣብኝ እንኳ፣ ልበ ሙሉ ነኝ። እግዚአብሔርን አንዲት ነገር እለምነዋለሁ፤ እርሷንም እሻለሁ፤ ይኸውም በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፣ የእግዚአብሔርን ክብር ውበት አይ ዘንድ፣ በመቅደሱም ሆኜ አሰላስል ዘንድ ነው። በመከራ ቀን፣ በድንኳኑ ውስጥ ይሰውረኛልና፤ በድንኳኑም ጓዳ ይሸሽገኛል። በዚህ ጊዜ በዙሪያዬ ባሉ ጠላቶቼ ላይ፣ ራሴ ከፍ ከፍ ይላል፤ በድንኳኑም ውስጥ የእልልታ መሥዋዕት እሠዋለሁ፤ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፤ እዘምርለታለሁም። እግዚአብሔር ሆይ፤ ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮኽ ስማኝ፤ ራራልኝ፤ ስማኝም። “ፊቴን ፈልጉ” ባልህ ጊዜ፤ ልቤ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ፊትህን እሻለሁ አለች።

መዝሙር 27:1-8 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር ብርሃኔና ደኅንነቴ ስለ ሆነ ማንንም አልፈራም እግዚአብሔር የሕይወቴ ከለላ ስለ ሆነ የሚያስፈራኝ ማነው? ክፉ ሰዎች ሲያጠቁኝና ሊገድሉኝ ሲቃጡ እነርሱ ራሳቸው ተሰናክለው ይወድቃሉ። ብዙ ሠራዊት ቢከበኝም አልፈራም፤ ጠላቶቼ በጦርነት ቢያጠቁኝ እንኳ በእግዚአብሔር መተማመኔን አልተውም። እግዚአብሔርን አንድ ነገር እለምነዋለሁ፤ የምለምነውም፦ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ የእግዚአብሔርን አስደናቂነት እንድመለከትና በቤተ መቅደሱም መጸለይ እንድችል ነው። በችግር ቀን በጥላው ሥር ይደብቀኛል፤ በመቅደሱ ውስጥ ይሰውረኛል፤ በአለትም ላይ ከፍ አድርጎ ይጠብቀኛል። አሁን ግን በከበቡኝ ጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ አደረግሁ፤ በደስታ “እልል” እያልኩ በመቅደሱ ውስጥ መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ እየዘመርኩም እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። እግዚአብሔር ሆይ! ወደ አንተ ጮክ ብዬ ስጣራ ስማኝ! ምሕረትን አድርግልኝ፤ ጸሎቴንም ስማ! ልቤ “የእርሱን ፊት ፈልግ” አለኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ! የአንተን ፊት እሻለሁ።

መዝሙር 27:1-8

መዝሙር 27:1-8 NASVመዝሙር 27:1-8 NASV