መዝሙር 22:1-3
መዝሙር 22:1-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔር ይጠብቀኛል፥ የሚያሳጣኝም የለም። በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ አሳደገኝ። ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።
ያጋሩ
መዝሙር 22 ያንብቡመዝሙር 22:1-3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውኸኝ? እኔን ከማዳን፣ ከመቃተቴም ቃል ለምን ራቅህ? አምላኬ ሆይ፤ በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ አንተ ግን አልመለስህልኝም፤ በሌሊት እንኳ አላረፍሁም። አንተ ግን ቅዱሱ ነጋሢ፤ የእስራኤልም ምስጋና ነህ።
ያጋሩ
መዝሙር 22 ያንብቡመዝሙር 22:1-3 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
አምላኬ! አምላኬ! ለምን ተውከኝ? እኔን ከማዳን የራቅኸው ለምንድን ነው? ከመቃተት ድምፄስ የራቅኸው ለምንድን ነው? አምላኬ ሆይ! በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ አንተ ግን አትሰማኝም፤ በሌሊት እጣራለሁ፤ ዕረፍትም የለኝም። ሆኖም አንተ በእስራኤል የተመሰገንክ፥ በዙፋንህ ላይ ተቀምጠህ የምትገዛ ቅዱስ አምላክ ነህ።
ያጋሩ
መዝሙር 22 ያንብቡ