መዝሙር 118:22-26
መዝሙር 118:22-26 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ትእዛዝህን ፈልጌአለሁና ስድብንና ነውርን ከእኔ አርቅ። አለቆች ደግሞ ተቀምጠው እኔን አሙኝ፤ ባሪያህ ግን ፍርድህን ያሰላስል ነበር። ምስክርህም ትምህርቴ ነው፥ ሥርዐትህም መካሬ ነው። ሰውነቴ ወደ ምድር ተጣበቀች፤ እንደ ቃልህ ሕያው አድርገኝ። መንገድህንና ምስክርህን ነገርሁ፥ ፍርድህን አስተምረኝ።
Share
መዝሙር 118 ያንብቡመዝሙር 118:22-26 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ። እግዚአብሔር ይህን አደረገ፤ ለዐይናችንም ድንቅ ናት። እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ በእርሷ ሐሤት እናድርግ፤ ደስም ይበለን። እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህ አድነን፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህ አሳካልን። በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው። ከእግዚአብሔር ቤት ባረክናችሁ።
Share
መዝሙር 118 ያንብቡመዝሙር 118:22-26 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ ዋና የማእዘን ራስ ሆነ። ይህም የእግዚአብሔር ሥራ ነው፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው። ይህ እግዚአብሔር የሠራው የድል ቀን ነው፤ በእርሱ ደስ ይበለን፤ ሐሴትም እናድርግ! እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ አድነን! እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ ሁሉ ነገር የተሟላ እንዲሆን አድርግልን! በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ይሁን! በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሆነን እንባርካችኋለን።
Share
መዝሙር 118 ያንብቡ