የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 118:15-29

መዝሙር 118:15-29 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በጻድቃን ድንኳን የእልልታና የሆታ ድምፅ፣ እንዲህ እያለ ያስተጋባል፤ “የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ብርቱ ሥራ ሠራች፤ የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አለች፤ የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ብርቱ ሥራ ሠራች።” ተርፌ በሕይወት እኖራለሁ እንጂ አልሞትም፤ የእግዚአብሔርንም ሥራ ገና እናገራለሁ። መገሠጹን እግዚአብሔር እጅግ ገሥጾኛል፤ ነገር ግን ለሞት አሳልፎ አልሰጠኝም። የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ፤ በዚያ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት፤ ጻድቃን በርሷ በኩል ይገባሉ። ሰምተህ መልሰህልኛልና፣ አዳኝም ሆነህልኛልና አመሰግንሃለሁ። ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ። እግዚአብሔር ይህን አድርጓል፤ ይህም ለዐይናችን ድንቅ ነው። እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ በርሷ ሐሤት እናድርግ፤ ደስም ይበለን። እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህ አድነን፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህ አሳካልን። በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው። ከእግዚአብሔር ቤት ባረክናችሁ። እግዚአብሔር አምላክ ነው፤ ብርሃኑንም በላያችን አበራ፤ እስከ መሠዊያው ቀንዶች ድረስ በመውጣት፣ ዝንጣፊ ይዛችሁ በዓሉን ከሚያከብሩት ጋራ ተቀላቀሉ። አንተ አምላኬ ነህ፤ አመሰግንሃለሁ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ። ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።

መዝሙር 118:15-29 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በጻድቃን ድንኳን ውስጥ እንዲህ የሚል የድል አድራጊነት ድምፅ ይሰማል፦ “የእግዚአብሔር ኀይል ያሸንፋል!” የእግዚአብሔር ኀይል ከፍ ከፍ አለ፤ ኀይሉም ድል አድራጊ ነው። በሕይወት እኖራለሁ እንጂ አልሞትም፤ የእግዚአብሔርንም ድንቅ ሥራ ዐውጃለሁ። በብርቱ ቀጥቶኛል፤ ነገር ግን እንድሞት አላደረገኝም። ወደ ውስጥ ገብቼ እግዚአብሔርን እንዳመሰግን የቤተ መቅደስን በሮች ከፈቱልኝ። ይህ የእግዚአብሔር በር ነው፤ ጻድቃን በእርሱ ይገባሉ። እግዚአብሔር ሆይ! ስለ ሰማኸኝና ስላዳንከኝ አመሰግንሃለሁ። ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ ዋና የማእዘን ራስ ሆነ። ይህም የእግዚአብሔር ሥራ ነው፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው። ይህ እግዚአብሔር የሠራው የድል ቀን ነው፤ በእርሱ ደስ ይበለን፤ ሐሴትም እናድርግ! እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ አድነን! እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ ሁሉ ነገር የተሟላ እንዲሆን አድርግልን! በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ይሁን! በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሆነን እንባርካችኋለን። እግዚአብሔር አምላክ ነው፤ ብርሃንን ሰጥቶናል፤ ለምለም የሆኑ ቅርንጫፎችን ይዘን በዓል ለማክበር ወደ መሠዊያው እንሂድ። አንተ አምላኬ ስለ ሆንክ አመሰግንሃለሁ፤ ታላቅነትህንም ዐውጃለሁ። ቸር ስለ ሆነና ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑት።

መዝሙር 118:15-29 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ትእ​ዛ​ዝ​ህን አሰ​ላ​ሰ​ልሁ፥ መን​ገ​ድ​ህ​ንም እፈ​ል​ጋ​ለሁ። ትእ​ዛ​ዞ​ች​ህን አነ​ብ​ባ​ለሁ፤ ቃል​ህ​ንም አል​ረ​ሳም። ሕያው እን​ድ​ሆን ቃል​ህ​ንም እን​ድ​ጠ​ብቅ ለባ​ሪ​ያህ ስጠው። ዓይ​ኖ​ችን ክፈት፥ ከሕ​ግ​ህም ድንቅ ነገ​ርን አያ​ለሁ። እኔ በም​ድር ስደ​ተኛ ነኝ፤ ትእ​ዛ​ዛ​ት​ህን ከእኔ አት​ሰ​ውር። ነፍሴ ሁል​ጊዜ ፍር​ድ​ህን እጅግ ናፈ​ቀች። ትዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችን ገሠ​ጽ​ኻ​ቸው፥ ከት​እ​ዛ​ዛ​ትህ የሚ​ርቁ ርጉ​ማን ናቸው። ትእ​ዛ​ዝ​ህን ፈል​ጌ​አ​ለ​ሁና ስድ​ብ​ንና ነው​ርን ከእኔ አርቅ። አለ​ቆች ደግሞ ተቀ​ም​ጠው እኔን አሙኝ፤ ባሪ​ያህ ግን ፍር​ድ​ህን ያሰ​ላ​ስል ነበር። ምስ​ክ​ር​ህም ትም​ህ​ርቴ ነው፥ ሥር​ዐ​ት​ህም መካሬ ነው። ሰው​ነቴ ወደ ምድር ተጣ​በ​ቀች፤ እንደ ቃልህ ሕያው አድ​ር​ገኝ። መን​ገ​ድ​ህ​ንና ምስ​ክ​ር​ህን ነገ​ርሁ፥ ፍር​ድ​ህን አስ​ተ​ም​ረኝ። የእ​ው​ነ​ት​ህን መን​ገድ እን​ዳ​ስ​ተ​ውል አድ​ር​ገኝ፥ ተአ​ም​ራ​ት​ህ​ንም አሰ​ላ​ስ​ላ​ለሁ። ከኀ​ዘን የተ​ነሣ ሰው​ነቴ አን​ቀ​ላ​ፋች፤ በቃ​ልህ አጠ​ን​ክ​ረኝ። የዐ​መ​ፃን መን​ገድ ከእኔ አርቅ፥ በሕ​ግ​ህም ይቅር በለኝ፤

መዝሙር 118:15-29 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የእልልታና የመዳን ድምፅ በጻድቃን ድንኳን ነው፥ የጌታ ቀኝ እጅ ኃይሉን አከናወነ። የጌታ ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አደረገችኝ፥ የጌታ ቀኝ እጅ ኃይሉን አከናወነ። አልሞትም፥ በሕይወት እኖራለሁ እንጂ፥ የጌታንም ሥራ እናገራለሁ። መገሠጽስ ጌታ ገሠጸኝ፥ ለሞት ግን አልሰጠኝም። የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ፥ ወደ እነርሱ ገብቼ ጌታን አመሰግናለሁ። ይህች የጌታ ደጅ ናት፥ ወደ እርሷ ጻድቃን ይገባሉ። ሰምተኸኛልና፥ መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ። ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፥ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፥ ይህች ከጌታ ዘንድ ሆነች፥ ለዓይናችንም ድንቅ ናት። ጌታ የሠራት ቀን ይህች ናት፥ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርሷም ደስ ይበለን። አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን፥ አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አቅና። በጌታ ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፥ ከጌታ ቤት መረቅናችሁ። ጌታ አምላክ ነው፥ ለእኛም አበራልን፥ እስከ መሠዊያው ቀንዶች ድረስ፥ ቅርንጫፎች ይዘን፥ ለበዓሉ ዑደት እናድርግ አንተ አምላኬ ነህ አመሰግንሃለሁ። አንተ አምላኬ ነህ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፥ ሰምተኸኛልና፥ መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ። ጌታን አመስግኑ፥ ቸር ነውና፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና።