መዝሙር 103:1-2
መዝሙር 103:1-2 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ነፍሴ እግዚአብሔርን ታመሰግነዋለች፤ አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ፤ መታመንንና የጌትነትን ክብር ለበስህ። ብርሃንን እንደ ልብስ ተጐናጸፍህ፤ ሰማይንም እንደ መጋረጃ ዘረጋህ፤
መዝሙር 103:1-2 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ የውስጥ ሰውነቴም ሁሉ ቅዱስ ስሙን ባርኪ። ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ ውለታውንም ሁሉ አትርሺ፤