ምሳሌ 4:5-9
ምሳሌ 4:5-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የአፌንም ቃል ቸል አትበል። አትተዋት፥ ትደግፍህማለች፤ ውደዳት፥ ትጠብቅህማለች። ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን አግኝ፤ ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ። ጠብቃት፥ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ አክብራት፥ እርስዋም ታቅፍሃለች። ለራስህ የሞገስ አክሊልን ትሰጥሃለች፥ በደስታ አክሊልም ትጠብቅሃለች።
Share
ምሳሌ 4 ያንብቡምሳሌ 4:5-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ጥበብን አግኛት፤ ማስተዋልን ያዛት፤ ቃሌን አትርሳ፤ ከእርሷም ዘወር አትበል። ጥበብን አትተዋት፤ እርሷም ከለላ ትሆንሃለች፤ አፍቅራት፤ እርሷም ትጠብቅሃለች። ጥበብ ታላቅ ነገር ናት፤ ስለዚህ ጥበብን አግኛት፤ ያለህን ሁሉ ብታስከፍልህም ማስተዋልን ገንዘብህ አድርጋት። ክብርን ስጣት፤ ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ ዕቀፋት፤ ታከብርሃለች፤ በራስህ ላይ ሞገሳማ አክሊል ትደፋልሃለች፤” የክብር ዘውድም ታበረክትልሃለች።
Share
ምሳሌ 4 ያንብቡምሳሌ 4:5-9 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ጥበብንና ማስተዋልን ለማግኘት ትጋ፤ እኔ የምልህን አትርሳ፤ ቸልም አትበለው። ጥበብን አትተዋት፤ እርስዋም ትጠብቅሃለች፤ ውደዳት፤ እርስዋም ከአደጋ ሁሉ ትከላከልልሃለች። ጥበብ ከሁሉ በላይ ስለ ሆነች እርስዋን ገንዘብ አድርግ፤ ያለህን ሁሉ ቢያስከፍልህም ማስተዋልን ለማግኘት ትጋ። ጥበብን አክብራት፤ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ አጥብቀህም ብትይዛት፥ ክብርን ትሰጥሃለች። የክብርን አክሊል ታቀዳጅሃለች፤ የተዋበውንም ዘውድ ትሰጥሃለች።”
Share
ምሳሌ 4 ያንብቡ