የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ምሳሌ 3:11-20

ምሳሌ 3:11-20 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ልጄ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ ቸል አትበል፥ በመገሠጹም ከእርሱ የተነሣ አትመረር። አባት የሚወድደውን ልጁን እንደሚገሥጽ እግዚአብሔር የሚወድደውን ይገሥጻል፥ የሚቀበላቸውን ልጆቹን ይገርፋልና። ጥበብን የሚያገኝ፥ ማስተዋልንም የሚያውቅ መዋቲ ሰው ብፁዕ ነው። በወርቅና በብር፥ በብዙም መዛግብት ከመነገድ ይልቅ በእርስዋ መነገድ ይሻላልና። ዋጋው ብዙ ከሆነ ዕንቍም የከበረች ናት። ክፉ ነገር አይቃወማትም፥ ለሚቀርቧትም መልካም ናት። ክብርም ሁሉ አይተካከላትም። ረጅም ዕድሜና የሕይወት ዘመን በቀኝዋ ነው። ባለጠግነትና ክብርም በግራዋ፥ ከአፏ ጽድቅ ይወጣል። ሕግንና ምጽዋትንም በአንደበትWa ትለብሳለች። መንገዶችዋ መልካም መንገዶች ናቸው። ጎዳናዋም ሁሉ ሰላም ነው። እርስዋ ለሚመረኰዛት ሁሉ የሕይወት ዛፍ ናት፥ የሚታመኑባትም በእግዚአብሔር እንደ ጸና ሰው ናቸው። እግዚአብሔር በጥበብ ምድርን መሠረተ፥ በማስተዋልም ሰማያትን አዘጋጀ። በዕውቀቱ ቀላያት መነጩ፥ ደመናትም ጠልን ያንጠባጥባሉ።