ምሳሌ 26:13-16
ምሳሌ 26:13-16 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ሰነፍ፣ “በመንገድ ላይ አንበሳ አለ፤ አስፈሪ አንበሳ በአውራ ጐዳና ላይ ይጐማለላል” ይላል። መዝጊያ በማጠፊያው ላይ እንደሚዞር፣ ሰነፍም በዐልጋው ላይ ይገላበጣል። ሰነፍ እጁን ወጭት ውስጥ ያጠልቃል፤ ወደ አፉ ለመመለስ ግን እጅግ ይታክታል። በማስተዋል መልስ ከሚሰጡ ከሰባት ሰዎች ይልቅ፣ ሰነፍ ራሱን ጠቢብ አድርጎ ይቈጥራል።
Share
ምሳሌ 26 ያንብቡ