ፊልጵስዩስ 3:17-21

ፊልጵስዩስ 3:17-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እኔን ምሰሉ፤ እን​ዲህ ባለ መን​ገድ የሚ​ሄ​ዱ​ት​ንም እኛን ታዩ እንደ ነበ​ረ​በት ጊዜ ተጠ​ባ​በ​ቋ​ቸው። ዘወ​ትር እን​ደ​ም​ነ​ግ​ራ​ችሁ፥ ልዩ አካ​ሄድ የሚ​ሄዱ ብዙ​ዎች አሉና፤ አሁ​ንም እነ​ርሱ የክ​ር​ስ​ቶስ የመ​ስ​ቀሉ ጠላ​ቶች እንደ ሆኑ በግ​ልጥ እያ​ለ​ቀ​ስሁ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ። እነ​ዚ​ህም ፍጻ​ሜ​ያ​ቸው ለጥ​ፋት የሆነ፥ ሆዳ​ቸ​ውን የሚ​ያ​መ​ልኩ፥ ክብ​ራ​ቸ​ውም ውር​ደት የሆ​ነ​ባ​ቸው፥ ምድ​ራ​ዊ​ዉ​ንም የሚ​ያ​ስቡ ናቸው። እኛስ ሀገ​ራ​ችን በሰ​ማይ ያለ​ችው ናት፤ ከዚ​ያም እር​ሱን ጌታ​ችን መድ​ኀ​ኒ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን እን​ጠ​ባ​በ​ቃ​ለን። እር​ሱም እንደ ከሃ​ሊ​ነቱ ረዳ​ት​ነት መጠን የተ​ዋ​ረ​ደ​ውን ሥጋ​ች​ንን የሚ​ያ​ድ​ሰው፥ ክቡር ሥጋ​ዉ​ንም እን​ዲ​መ​ስል የሚ​ያ​ደ​ር​ገው፥ የሚ​ያ​ስ​መ​ስ​ለ​ውም፥ ሁሉም የሚ​ገ​ዛ​ለት ነው።