የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ፊልጵስዩስ 1:20-26

ፊልጵስዩስ 1:20-26 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በም​ንም እን​ደ​ማ​ላ​ፍር ተስፋ እንደ አደ​ረ​ግ​ሁና እን​ደ​ታ​መ​ንሁ እንደ ወት​ሮው በልብ ደስታ በግ​ል​ጥ​ነት፥ አሁ​ንም የክ​ር​ስ​ቶስ ክብር በሕ​ይ​ወ​ቴም ቢሆን፥ በሞ​ቴም ቢሆን በሰ​ው​ነቴ ይገ​ለ​ጣል። እኔ በሕ​ይ​ወት ብኖ​ርም ክር​ስ​ቶ​ስን ለማ​ገ​ል​ገል ነው፤ ብሞ​ትም ዋጋ አለኝ። ነገር ግን በሥጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆ​ንም ምን እን​ደ​ም​መ​ርጥ አላ​ው​ቅም። በእ​ነ​ዚህ በሁ​ለቱ እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤ እኔስ ከዚህ ዓለም ልለይ፥ በከ​ክ​ር​ስ​ቶ​ስም ዘንድ ልኖር እወ​ዳ​ለሁ፤ ይል​ቁ​ንም ለእኔ ይህ ይሻ​ለ​ኛል፤ ይበ​ል​ጥ​ብ​ኛ​ልም። ደግ​ሞም ስለ እና​ንተ በሕ​ይ​ወተ ሥጋ ብኖር ይሻ​ላል። ይህ​ንም ዐውቄ ለማ​ደ​ጋ​ች​ሁና በሃ​ይ​ማ​ኖ​ትም ለም​ታ​ገ​ኙት ደስታ እን​ደ​ም​ኖር አም​ና​ለሁ። ዳግ​መኛ ወደ እና​ንተ በመ​ም​ጣቴ በእኔ ምክ​ን​ያት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የም​ታ​ገ​ኙት ክብር ይበ​ዛ​ላ​ችሁ ዘንድ።

ፊልጵስዩስ 1:20-26 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በፍጹም እንደማላፍር በተስፋ እጠባበቃለሁ፤ ነገር ግን ዘወትር እንደማደርገውና ዛሬ በሕይወት ብኖር ወይም ብሞት ክርስቶስ በሰውነቴ ይከብራል ብዬ በድፍረት እናገራለሁ። ስለዚህ ለእኔ ሕይወት ማለት በክርስቶስ መኖር ነው፤ ሞትም ማለት ጥቅም የሚገኝበት ነገር ነው። ይሁን እንጂ በዚሁ ሥጋዊ አካሌ ቀጥዬ የምኖር ብሆን ፍሬ የሚሰጥ ሥራ መሥራት ማለት ነው፤ ሆኖም ግን ቀጥዬ ከመኖርና ከመሞት የትኛውን እንደምመርጥ አላውቅም። በእነዚህ በሁለቱ ሐሳቦች መካከል ተይዤአለሁ፤ በአንድ በኩል ከክርስቶስ ጋር መሆን ከሁሉ የሚበልጥ ነገር ስለ ሆነ ከዚህ ሕይወት ተለይቼ ከክርስቶስ ጋር መሆንን እፈልጋለሁ ይኸውም ከክርስቶስ ጋር መኖር እጅግ የተሻለ ስለ ሆነ ነው። በሌላ በኩል በሕይወት መኖሬ ለእናንተ የበለጠ አስፈላጊ ነው። በዚህ በመተማመን እኔ ከሞት ተርፌ እምነታችሁ እንዲያድግና ደስታን እንድታገኙ ከሁላችሁም ጋር እንድቈይ ዐውቃለሁ። እኔም እንደገና ወደ እናንተ ስመጣ በእኔ ምክንያት ያላችሁ ትምክሕት በኢየሱስ ክርስቶስ ይበዛል።