የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘኍል 33:50-56

ዘኍል 33:50-56 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ በኩል በሞ​ዓብ ምዕ​ራብ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው። “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ወደ ከነ​ዓን ምድር ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ራ​ላ​ችሁ፤ በዚ​ያ​ችም ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ከፊ​ታ​ችሁ አጥ​ፉ​አ​ቸው፤ የተ​ቀ​ረ​ጹ​ት​ንም ድን​ጋ​ዮ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ ታጠ​ፋ​ላ​ችሁ፤ ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ ታጠ​ፋ​ላ​ችሁ፤ በኮ​ረ​ብታ ላይ ያሉ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ታፈ​ር​ሳ​ላ​ችሁ፤ በዚ​ያች ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም አጥ​ፍ​ታ​ችሁ በው​ስ​ጥዋ ኑሩ። ምድ​ሪ​ቱን ለእ​ና​ንተ ርስት አድ​ርጌ ሰጥ​ቼ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና። ምድ​ሪ​ቱ​ንም ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ፤ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ች​ሁም ትከ​ፋ​ፈ​ሏ​ታ​ላ​ችሁ፤ ለብ​ዙ​ዎች ድር​ሻ​ቸ​ውን አብ​ዙ​ላ​ቸው፤ ለጥ​ቂ​ቶ​ችም ድር​ሻ​ቸ​ውን ጥቂት አድ​ርጉ፤ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሁሉ ዕጣ እንደ ወደ​ቀ​ለት በዚያ ርስቱ ይሆ​ናል፤ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ነገ​ዶች ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ። የሀ​ገ​ሩ​ንም ስዎች ከፊ​ታ​ችሁ ባታ​ሳ​ድዱ፥ ያስ​ቀ​ራ​ች​ኋ​ቸው ለዐ​ይ​ና​ችሁ እንደ እሾህ፥ ለጐ​ና​ች​ሁም እንደ አሜ​ከላ ይሆ​ኑ​ባ​ች​ኋል፤ በም​ት​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትም ምድር ያስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ች​ኋል። እኔም በእ​ነ​ርሱ አደ​ር​ገው ዘንድ ያሰ​ብ​ሁ​ትን በእ​ና​ንተ አደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ።”

ዘኍል 33:50-56 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው በሞዓብ ሜዳ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘ወደ ከነዓን ለመግባት ዮርዳኖስን ስትሻገሩ፣ የምድሪቱን ነዋሪዎች በሙሉ ከፊታችሁ አሳድዳችሁ አስወጧቸው፤ የተቀረጹ ምስሎቻቸውንና ቀልጠው የተሠሩ ጣዖቶቻቸውን በሙሉ አጥፉ፤ እንዲሁም በኰረብታ ላይ የተሠሩትን መስገጃዎቻቸውን ሁሉ አፈራርሱ። ምድሪቱን ርስት አድርጌ ሰጥቻችኋለሁና ውረሷት፤ ኑሩባትም። ምድሪቱንም በየጐሣዎቻችሁ በዕጣ ተከፋፈሉ። ከፍ ያለ ቍጥር ላለው ሰፋ ያለውን፣ ዝቅተኛ ቍጥር ላለው ደግሞ አነስተኛውን ስጡ፤ ምንም ይሁን ምን በዕጣ የወጣላቸው፣ የየራሳቸው ርስት ይሆናል። አከፋፈሉም በየአባቶቻችሁ ነገዶች አንጻር ይሁን። “ ‘የምድሪቱን ነዋሪዎች አሳድዳችሁ ሳታስወጧቸው ብትቀሩ ግን፣ እንዲኖሩ የተዋችኋቸው ሰዎች ለዐይናችሁ ስንጥር፣ ለጐናችሁም እሾኽ ይሆኑባችኋል፤ በምትኖሩበትም ምድር ችግር ይፈጥሩባችኋል። እኔም በእነርሱ ላይ ለማድረግ ያሰብሁትን በእናንተ ላይ አደርግባችኋለሁ።’ ”

ዘኍል 33:50-56 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እግዚአብሔርም ሙሴን በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ላይ እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ወደ ከነዓን ምድር ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ፥ የአገሩን ሰዎች ሁሉ ከፊታችሁ ታሳድዳላችሁ፥ የተቀረጹትንም ድንጋዮቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ በኮረብታ ላይ ያሉትን መስገጃዎቻቸውንም ታፈርሳላችሁ፤ ምድሪቱንም ለእናንተ ርስት አድርጌ ሰጥቼአችኋለሁና ምድሪቱን ትወርሱአታላችሁ ትቀመጡባታላችሁም። ምድሪቱንም በየወገኖቻችሁ በዕጣ ትወርሳላችሁ፤ ለብዙዎች እንደ ብዛታቸው ለጥቂቶቹም እንደ ጥቂትነታቸው መጠን ርስትን ትሰጣላችሁ፤ እያዳንዱ ሁሉ ዕጣ እንደ ወደቀለት በዚያ ርስቱ ይሆናል፤ በየአባቶቻችሁ ነገዶች ትወርሳላችሁ። የአገሩንም ሰዎች ከፊታችሁ ባታሳድዱ፥ ያስቀራችኋቸው ለዓይናችሁ እንደ እሾህ ለጎናችሁም እንደሚወጋ ነገር ይሆኑባችኋል፥ በምትቀመጡባትም ምድር ያስጨንቁአችኋል። እኔም በእነርሱ አደርገው ዘንድ ያሰብሁትን በእናንተ አደርግባችኋለሁ።

ዘኍል 33:50-56 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በኢያሪኮ ትይዩ ከዮርዳኖስ ማዶ በሞአብ ሜዳ ላይ ሳሉ ለእስራኤል ሕዝብ ይነግራቸው ዘንድ እግዚአብሔር ለሙሴ የሚከተለውን መመሪያ ሰጠው፤ ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ “ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ወደ ከነዓን ምድር ስትገቡ፥ በምድሪቱ ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ ከፊታችሁ አስወጡአቸው፤ ከድንጋይና ከብረት የተሠሩትን ጣዖቶቻቸውንም ሰባበሩ፤ በኮረብታ ላይ ያሉ መስገጃዎቻቸውንም አፈራርሱ። ለእናንተ የሰጠኋት ስለ ሆነ፥ ምድሪቱን ወርሳችሁ በእርስዋ ኑሩ። ምድሪቱንም በተለያዩት ነገዶችና ጐሣዎች መካከል በዕጣ ተከፋፈሉ፤ የጐሣው ቊጥር ከፍ ላለው ሰፊ መሬት ይሰጠው፤ የጐሣው ቊጥር አነስተኛ ለሆነው ደግሞ ጠበብ ያለ መሬት ይሰጠው። እያንዳንዱ ሁሉ ዕጣው እንደ ወጣለት በዚያ ርስቱ ይሆናል፤ በየአባቶቻችሁ ነገዶች ምድሪቱን በርስትነት ትረከባላችሁ። በምድሪቱ ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ አሳዳችሁ ካላጠፋችሁ ግን ያስቀራችኋቸው ለዐይናችሁ እንደ ስንጥር ለጐናችሁም እንደ እሾኽ በመሆን ያስቸግሩአችኋል፤ በምትቀመጡባትም ምድር ዘወትር ጦርነት በማስነሣት ያስጨንቁአችኋል። ያለበለዚያ እነርሱን ለማጥፋት እንዳቀድኩት ሁሉ እናንተን አጠፋለሁ።”

ዘኍል 33:50-56 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ጌታም ሙሴን በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ላይ እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ለእነርሱ ተናገር፦ ወደ ከነዓን ምድር ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ፥ የአገሩን ሰዎች ሁሉ ከፊታችሁ ታሳድዳላችሁ፥ የተቀረጹትንም ድንጋዮቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ በኮረብታ ላይ ያሉትን መስገጃዎቻቸውንም ታፈርሳላችሁ፤ ምድሪቱንም ለእናንተ ርስት አድርጌ ሰጥቼአችኋለሁና ምድሪቱን ትወርሱአታላችሁ ትቀመጡባታላችሁም። ምድሪቱንም በየወገኖቻችሁ በዕጣ ትወርሳላችሁ፤ ለብዙዎች እንደ ብዛታቸው ለጥቂቶቹም እንደ ጥቂትነታቸው መጠን ርስትን ትሰጣላችሁ፤ እያንዳንዱ ሁሉ ዕጣው እንደ ወጣለት በዚያ ርስቱ ይሆናል፤ በየአባቶቻችሁ ነገዶች ትወርሳላችሁ። የአገሩንም ሰዎች ከፊታችሁ ባታሳድዱ፥ ያስቀራችኋቸው ለዓይናችሁ እንደ ስንጥር ለጎናችሁም እንደ እሾህ ይሆኑባችኋል፥ በምትቀመጡባትም ምድር ያስጨንቁአችኋል። እኔም በእነርሱ ላይ ለማድረግ ያሰብሁትን በእናንተ ላይ አደርግባችኋለሁ።”