የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘኍል 33:1-49

ዘኍል 33:1-49 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በሙ​ሴና በአ​ሮን እጅ ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የሰ​ፈ​ሩ​በት ይህ ነው። ሙሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ እንደ ተጓዙ የሰ​ፈ​ሩ​በ​ትን ጻፈ፥ እየ​ተ​ጓዙ ያደ​ሩ​በት ይህ ነው። በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን ከራ​ምሴ ተጓዙ፤ ከፋ​ሲካ በኋላ በነ​ጋው የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን ሁሉ ፊት ከፍ ባለች እጅ ወጡ። በዚ​ያም ጊዜ ግብ​ፃ​ው​ያን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የገ​ደ​ላ​ቸ​ውን በኵ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ይቀ​ብሩ ነበር፤ በአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈረ​ደ​ባ​ቸው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከራ​ምሴ ተጕ​ዘው በሱ​ኮት ሰፈሩ። ከሱ​ኮ​ትም ተጕ​ዘው በም​ድረ በዳ ዳርቻ ባለች በኤ​ታም ሰፈሩ። ከኤ​ታ​ምም ተጕ​ዘው በኤ​ል​ሴ​ፎን ፊት ወደ ነበ​ረች በኤ​ሮት በር፤ በመ​ግ​ደሎ ፊት ለፊት ሰፈሩ። ከኤ​ሮ​ትም ፊት ለፊት ተጕ​ዘው በባ​ሕሩ መካ​ከል ወደ ምድረ በዳ ተሻ​ገሩ፤ በኤ​ታ​ምም በረሃ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ሄደው በም​ረት ሰፈሩ። ከም​ረ​ትም ተጕ​ዘው ወደ ኤሊም መጡ፤ በኤ​ሊ​ምም ዐሥራ ሁለት የውኃ ምን​ጮች፥ ሰባ ዘን​ባ​ቦ​ችም ነበሩ፤ በዚ​ያም በውኃ አጠ​ገብ ሰፈሩ። ከኤ​ሊ​ምም ተጕ​ዘው በኤ​ር​ትራ ባሕር ዳር ሰፈሩ። ከኤ​ር​ት​ራም ባሕር ተጕ​ዘው በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ። ከሲና ምድረ በዳም ተጕ​ዘው በራ​ፋቃ ሰፈሩ። ከራ​ፋ​ቃም ተጕ​ዘው በኤ​ሉስ ሰፈሩ። ከኤ​ሉ​ስም ተጕ​ዘው በራ​ፊ​ድን ሰፈሩ፤ በዚ​ያም ሕዝቡ የሚ​ጠ​ጡት ውኃ አል​ነ​በ​ረም። ከራ​ፊ​ድ​ንም ተጕ​ዘው በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ። ከሲና ምድረ በዳም ተጕ​ዘው በም​ኞት መቃ​ብር ሰፈሩ። ከም​ኞት መቃ​ብ​ርም ተጕ​ዘው በአ​ቤ​ሮት ሰፈሩ። ከአ​ቤ​ሮ​ትም ተጕ​ዘው በራ​ታማ ሰፈሩ። ከራ​ታ​ማም ተጕ​ዘው በሬ​ሞት ዘፋ​ሬስ ሰፈሩ። ከሬ​ሞት ዘፋ​ሬ​ስም ተጕ​ዘው በል​ብና ሰፈሩ። ከል​ብ​ናም ተጕ​ዘው በሪሳ ሰፈሩ። ከሪ​ሳም ተጕ​ዘው በመ​ቄ​ላት ሰፈሩ። ከመ​ቄ​ላ​ትም ተጕ​ዘው በሳ​ፋር ሰፈሩ። ከሳ​ፋ​ርም ተጕ​ዘው በካ​ሬ​ደት ሰፈሩ። ከካ​ሬ​ደ​ትም ተጕ​ዘው በመ​ቄ​ሎት ሰፈሩ። ከመ​ቄ​ሎ​ትም ተጕ​ዘው በቀ​ጠ​አት ሰፈሩ። ከቀ​ጠ​አ​ትም ተጕ​ዘው በተ​ሪት ሰፈሩ። ከተ​ሪ​ትም ተጕ​ዘው በሚ​ትቃ ሰፈሩ። ከሚ​ት​ቃም ተጕ​ዘው በኤ​ሴ​ምና ሰፈሩ። ከኤ​ሴ​ም​ናም ተጕ​ዘው በመ​ሱ​ሩት ሰፈሩ። ከመ​ሱ​ሩ​ትም ተጕ​ዘው በብ​ን​ያ​ቅን ሰፈሩ። ከብ​ን​ያ​ቅ​ንም ተጕ​ዘው በገ​ድ​ገድ ተራራ ሰፈሩ። ከገ​ድ​ገ​ድም ተጕ​ዘው በአ​ጤ​ቤት ሰፈሩ። ከአ​ጤ​ቤ​ትም ተጕ​ዘው በኤ​ብ​ሮና ሰፈሩ። ከኤ​ብ​ሮ​ናም ተጕ​ዘው በጋ​ስ​ዮ​ን​ጋ​ቤር ሰፈሩ። ከጋ​ስ​ዮ​ን​ጋ​ቤ​ርም ተጕ​ዘው በጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ። ከጺን ምድረ በዳም ተጕ​ዘው በፋ​ራን ምድረ በዳ ሰፈሩ። ይህ​ችም ቃዴስ ናት። ከቃ​ዴ​ስም ተጕ​ዘው በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድር ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ ሰፈሩ። ካህ​ኑም አሮን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፤ በዚ​ያም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በአ​ር​ባ​ኛው ዓመት፥ በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር፥ ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ሞተ። አሮ​ንም በሖር ተራራ ላይ በሞተ ጊዜ ዕድ​ሜው መቶ ሃያ ሦስት ዓመት ነበረ። በከ​ነ​ዓን ምድ​ርም ተቀ​ምጦ የነ​በ​ረው ከነ​ዓ​ና​ዊው የዓ​ራድ ንጉሥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እንደ መጡ ሰማ። እነ​ር​ሱም ከሖር ተራራ ተጕ​ዘው በሴ​ል​ሞና ሰፈሩ። ከሴ​ል​ሞ​ናም ተጕ​ዘው በፌኖ ሰፈሩ። ከፌ​ኖም ተጕ​ዘው በአ​ቦት ሰፈሩ። ከአ​ቦ​ትም ተጕ​ዘው በሞ​ዓብ ዳርቻ ባለው በጋይ ሰፈሩ። ከጋ​ይም ተጕ​ዘው በዲ​ቦ​ን​ጋድ ሰፈሩ። ከዲ​ቦ​ን​ጋ​ድም ተጕ​ዘው በጌ​ል​ሞ​ን​ዲ​ብ​ላ​ታ​ይም ሰፈሩ። ከጌ​ል​ሞ​ን​ዲ​ብ​ላ​ታ​ይ​ምም ተጕ​ዘው በና​ባው ፊት ባሉት በአ​ባ​ሪም ተራ​ሮች ላይ ሰፈሩ። በና​ባው ፊት ካሉት ከአ​ባ​ሪም ተራ​ሮ​ችም ተጕ​ዘው በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ በኩል ባለው በሞ​ዓብ ምዕ​ራብ ሰፈሩ። በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም አጠ​ገብ በሞ​ዓብ ምዕ​ራብ ከአ​ሲ​ሞት መካ​ከል እስከ አቤ​ል​ሰ​ጢም ድረስ ሰፈሩ።

ዘኍል 33:1-49 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እስራኤላውያን በየነገዳቸው ተከፋፍለው በሙሴና በአሮን መሪነት ከግብፅ ወጥተው፣ በጕዞ ላይ ሳሉ የሰፈሩባቸው ቦታዎች እነዚህ ናቸው፤ ሙሴም በጕዟቸው ላይ ሳሉ የሰፈሩባቸውን ቦታዎች በእግዚአብሔር (ያህዌ) ትእዛዝ መዘገበ፤ በየቦታው እየሰፈሩ ያደረጉት ጕዞም ይህ ነው፤ እስራኤላውያን በመጀመሪያው ወር በዐሥራ አምስተኛውም ቀን በፋሲካ ማግስት ከራምሴ ተነሡ፤ ግብፃውያን ሁሉ እያዩአቸውም በልበ ሙሉነት ተጓዙ። በዚህ ጊዜ ግብፃውያን እግዚአብሔር (ያህዌ) ከመካከላቸው የገደለባቸውን በኵሮቻቸውን ይቀብሩ ነበር፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) በግብፅ አማልክት ላይ ፈርዶ ነበርና። እስራኤላውያን ከራምሴ ተነሥተው በሱኮት ሰፈሩ። ከሱኮትም ተነሥተው በምድረ በዳው ዳርቻ በምትገኘው በኤታም ሰፈሩ። ከኤታም ተነሥተው ከበኣልዛፎን በስተ ምሥራቅ ወዳለችው ወደ ፊሀሒሮት በመመለስ በሚግዶል አጠገብ ሰፈሩ። ከፊሀሒሮት ተነሥተው በባሕሩ ውስጥ በማለፍ ወደ ምድረ በዳው ሄዱ፤ ከዚያም በኤታም ምድረ በዳ ሦስት ቀን ተጕዘው በማራ ሰፈሩ። ከማራ ተነሥተው ዐሥራ ሁለት የውሃ ምንጮችና ሰባ የተምር ዛፎች ወደ ነበሩበት ወደ ኤሊም መጥተው በዚያ ሰፈሩ። ከኤሊም ተነሥተው በቀይ ባሕር አጠገብ ሰፈሩ። ከቀይ ባሕር ተነሥተው በሲን ምድረ በዳ ሰፈሩ። ከሲን ምድረ በዳ ተነሥተው በራፍቃ ሰፈሩ። ከራፍቃ ተነሥተው በኤሉስ ሰፈሩ። ከኤሉስ ተነሥተው በራፊዲም ሰፈሩ፤ በዚያም ሕዝቡ የሚጠጣው ውሃ አልበረም። ከራፊዲም ተነሥተው በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ። ከሲና ምድረ በዳ ተነሥተው በቂብሮት ሃታቫ ሰፈሩ። ከቂብሮት ሃታቫ ተነሥተው በሐጼሮት ሰፈሩ። ከሐጼሮት ተነሥተው በሪትማ ሰፈሩ። ከሪትማ ተነሥተው በሬሞን ዘፋሬስ ሰፈሩ። ከሬሞን ዘፋሬስ ተነሥተው በልብና ሰፈሩ። ከልብና ተነሥተው በሪሳ ሰፈሩ። ከሪሳ ተነሥተው በቀሄላታ ሰፈሩ። ከቀሄላታ ተነሥተው በሻፍር ተራራ ሰፈሩ። ከሻፍር ተራራ ተነሥተው በሐራዳ ሰፈሩ። ከሐራዳ ተነሥተው በማቅሄሎት ሰፈሩ። ከማቅሄሎት ተነሥተው በታሐት ሰፈሩ። ከታሐት ተነሥተው በታራ ሰፈሩ። ከታራ ተነሥተው በሚትቃ ሰፈሩ። ከሚትቃ ተነሥተው በሐሽሞና ሰፈሩ። ከሐሽሞና ተነሥተው በምሴሮት ሰፈሩ። ከምሴሮት ተነሥተው በብኔያዕቃን ሰፈሩ። ከብኔያዕቃን ተነሥተው በሖርሃጊድጋድ ሰፈሩ። ከሖርሃጊድጋድም ተነሥተው በዮጥባታ ሰፈሩ። ከዮጥባታ ተነሥተው በዔብሮና ሰፈሩ። ከዔብሮና ተነሥተው በዔጽዮንጋብር ሰፈሩ። ከዔጽዮንጋብር ተነሥተው በጺን ምድረ በዳ ባለችው በቃዴስ ሰፈሩ። ከቃዴስ ተነሥተው በኤዶም ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ ሰፈሩ። በእግዚአብሔር (ያህዌ) ትእዛዝ ካህኑ አሮን ወደ ሖር ተራራ ወጣ፤ እዚያም እስራኤላውያን ከግብፅ በወጡ በአርባኛው ዓመት፣ በአምስተኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ። አሮን በሖር ተራራ ላይ ሲሞት፣ ዕድሜው መቶ ሃያ ሦስት ዓመት ነበር። በከነዓን በምትገኘው በኔጌብ የሚኖረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ፣ የእስራኤላውያንን መምጣት ሰማ። እነርሱም ከሖር ተራራ ተነሥተው በሴልሞና ሰፈሩ። ከሴልሞና ተነሥተው በፋኖን ሰፈሩ። ከፋኖን ተነሥተው በአቦት ሰፈሩ። ከአቦት ተነሥተው በሞዓብ ዳርቻ በምትገኘው በኢየአባሪም ሰፈሩ። ከኢየአባሪም ተነሥተው በዲቦንጋድ ሰፈሩ። ከዲቦንጋድ ተነሥተው በዓልሞን ዲብላታይም ሰፈሩ። ከዓልሞንዲብላታይም ተነሥተው በናባው አጠገብ በሚገኙት በዓብሪም ተራራዎች ላይ ሰፈሩ። ከዓብሪም ተራራዎች ተነሥተው ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ባለው በሞዓብ ሜዳ ላይ ሰፈሩ። እዚያም በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ በሞዓብ ሜዳ ከቤት የሺሞት እስከ አቤልስጢም ባለው ስፍራ ሰፈሩ።

ዘኍል 33:1-49 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የእስራኤልም ልጆች ጕዞ ከሙሴና ከአሮን ልጅ በታች በጭፍሮቻቸው ከግብፅ በወጡ ጊዜ እንዲህ ነበረ። ሙሴም በእግዚአብሔር ትእዛዝ እንደ ጕዞአቸው አወጣጣቸውን ጻፈ፤ እንደ አወጣጣቸውም ጕዞአቸው እንዲህ ነበረ። በመጀመሪያው ወር ከወሩም በአሥራ አምስተኛው ቀን ከራምሴ ተጓዙ፤ ከፋሲካ በኋላ በነጋው የእስራኤል ልጆች ግብፃውያን ሁሉ እያዩ ከፍ ባለች እጅ ወጡ። በዚያም ጊዜ ግብፃውያን እግዚአብሔር የገደላቸውን በኵሮቻቸውን ይቀብሩ ነበር፤ በአማልክቶቻቸውም ደግሞ እግዚአብሔር ፈረደባቸው። የእስራኤልም ልጆች ከራምሴ ተጕዘው በሱኮት ሰፈሩ። ከሱኮትም ተጕዘው በምድረ በዳ ዳርቻ ባለች በኤታም ሰፈሩ። ከኤታምም ተጕዘው በበኣልዛፎን ፊት ወደ ነበረች ወደ ፊሀሒሮት ተመለሱ፤ በሚግዶልም ፊት ለፊት ሰፈሩ። ከፊሀሒሮትም ተጕዘው በባሕሩ ውስጥ ወደ ምድረ በዳ አለፉ፤ በኤታምም በረሀ የሦስት ቀን መንገድ ሄደው በማራ ሰፈሩ። ከማራም ተጕዘው ወደ ኤሊም መጡ፤ በኤሊምም አሥራ ሁለት የውኃ ምንጮች ሰባ ዘንባቦችም ነበሩ፤ በዚያም ሰፈሩ። ከኤሊምም ተጕዘው በኤርትራ ባሕር ዳር ሰፈሩ። ከኤርትራም ባሕር ተጕዘው በሲን ምድረ በዳ ሰፈሩ። ከሲን ምድረ በዳም ተጕዘው በራፋቃ ሰፈሩ። ከራፋቃም ተጕዘው በኤሉስ ሰፈሩ። ከኤሉስም ተጕዘው በራፊዲም ሰፈሩ በዚያም ሕዝቡ የሚጠጡት ውኃ አልነበረም። ከራፊዲምም ተጕዘው በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ። ከሲናም ምድረ በዳ ተጕዘው በምኞት መቃብር ሰፈሩ። ከምኞት መቃብርም ተጕዘው በሐጼሮት ሰፈሩ። ከሐጼሮትም ተጕዘው በሪትማ ሰፈሩ። ከሪትማም ተጕዘው በሬሞን ዘፋሬስ ሰፈሩ። ከሬሞን ዘፋሬስም ተጕዘው በልብና ሰፈሩ። ከልብናም ተጕዘው በሪሳ ሰፈሩ። ከሪሳም ተጕዘው በቀሄላታ ሰፈሩ። ከቀሄላታም ተጕዘው በሻፍር ተራራ ሰፈሩ። ከሻፍር ተራራም ተጕዘው በሐራዳ ሰፈሩ። ከሐራዳም ተጕዘው በመቅሄሎት ሰፈሩ። ከመቅሄሎትም ተጕዘው በታሐት ሰፈሩ። ከታሐትም ተጕዘው በታራ ሰፈሩ። ከታራም ተጕዘው በሚትቃ ሰፈሩ። ከሚትቃም ተጕዘው በሐሽሞና ሰፈሩ። ከሐሽሞናም ተጕዘው በሞሴሮት ሰፈሩ። ከሞሴሮትም ተጕዘው በብኔያዕቃን ሰፈሩ። ከብኔያዕቃንም ተጕዘው በሖርሃጊድጋድ ሰፈሩ። ከሆርሃጊድጋድም ተጕዘው በዮጥባታ ሰፈሩ። ከዮጥባታም ተጕዘው በዔብሮና ሰፈሩ። ከዔብሮናም ተጕዘው በዔጽዮንጋብር ሰፈሩ። ከዔጽዮንጋብርም ተጕዘው በጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ፤ ይህችም ቃዴስ ናት። ከቃዴስም ተጕዘው በኤዶምያስ ምድር ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ ሰፈሩ። ካህኑም አሮን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፥ በዚያም የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ። አሮንም በሖር ተራራ በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሀያ ሦስት ዓመት ነበር። በከነዓን ምድርም በደቡብ በኩል ተቀምጦ የነበረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ የእስራኤል ልጆች እንደ መጡ ሰማ። እነርሱም ከሖር ተራራ ተጕዘው በሴልሞና ሰፈሩ። ከሴልሞናም ተጕዘው በፉኖን ሰፈሩ። ከፋኖንም ተጕዘው በአቦት ሰፈሩ። ከአቦትም ተጕዘው በሞዓብ ዳርቻ ባለው በጋይ ሰፈሩ። ከጋይም ተጕዘው በዲቦንጋድ ሰፈሩ። ከዲቦንጋድም ተጕዘው በዓልሞንዲብላታይም ሰፈሩ። ከዓልሞንዲብላታይምም ተጕዘው በናባው ፊት ባሉ በዓብሪም ተራሮች ላይ ሰፈሩ። ከዓብሪምም ተራሮች ተጕዘው በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ባለው በሞዓብ ሜዳ ሰፈሩ። በዮርዳኖስም አጠገብ በሞዓብ ሜዳ ላይ ከቤትየሺሞት እስከ አቤልሰጢም ድረስ ሰፈሩ።

ዘኍል 33:1-49 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እስራኤላውያን በየነገዳቸው ተከፋፍለው በሙሴና በአሮን መሪነት ከግብጽ ከወጡ በኋላ በየጊዜው የሰፈሩባቸውን ቦታዎች የሚያስረዳው ታሪክ ይህ ነው፦ በየጊዜው የሰፈሩባቸውን ቦታዎች ስሞች ሙሴ በእግዚአብሔር ትእዛዝ መሠረት ጻፈ። የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር የወጡት የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን ማለትም በመጀመሪያው የፋሲካ በዓል ማግስት ነበር። ግብጻውያን ሁሉ ፊት ለፊት እያዩአቸው በእግዚአብሔር ጠባቂነት የራምሴን ከተማ ለቀው ወጡ፤ ግብጻውያን በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር መቅሠፍት የሞቱትን የበኲር ልጆቻቸውን ይቀብሩ ነበር፤ እግዚአብሔርም በአማልክታቸው ላይ እንኳ ፈርዶአል። እስራኤላውያን ከራምሴ ተነሥተው በመጓዝ በሱኮት ሰፈሩ፤ ከዚያም ተነሥተው በበረሓው ጫፍ በምትገኘው በኤታም ሰፈሩ፤ ከኤታም ተነሥተው በባዓልጸፎን በስተምሥራቅ ወደ ፒሃሒሮት በመመለስ በሚግዶል ፊት ለፊት ሰፈሩ፤ ከፒሃሒሮት ተነሥተው ቀይ ባሕርን በመሻገር ወደ ሱር በረሓ መጡ፤ ከሦስት ቀን ጒዞ በኋላ በማራ ሰፈሩ፤ ከዚያም ተነሥተው ዐሥራ ሁለት የውሃ ምንጮችና ሰባ የተምር ዛፎች ወደሚገኙባት ወደ ኤሊም ሄደው በዚያ ሰፈሩ። ከኤሊም ተነሥተው በቀይ ባሕር አጠገብ ሰፈሩ፤ ከቀይ ባሕር ተነሥተው በሲን ምድረ በዳ ሰፈሩ፤ ከሲን ምድረ በዳ ተነሥተው በዱፍቃ ሰፈሩ፤ ከዱፍቃም ተነሥተው በአሉሽ ሰፈሩ፤ ከአሉሽ ተነሥተው የመጠጥ ውሃ በሌለበት በረፊዲም ሰፈሩ። ከሬፊዲም ተነሥተው በመጓዝ በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ። ከሲና ምድረ በዳ ተነሥተው በመጓዝ በኪብሮት ሃትአዋ ሰፈሩ። ከኪብሮት ሃትአዋ ተነሥተው በመጓዝ በሐጼሮት ሰፈሩ። ከሐጼሮት ተነሥተው በመጓዝ በሪትማ ሰፈሩ። ከሪትማ ተነሥተው በመጓዝ በሪሞንፔሬዝ ሰፈሩ። ከሪሞንፔሬዝ ተነሥተው በመጓዝ በሊብና ሰፈሩ ከሊብና ተነሥተው በመጓዝ በሪሳ ሰፈሩ። ከሪሳ ተነሥተው በመጓዝ በቀሄላታ ሰፈሩ። ከቀሄላታ ተነሥተው በመጓዝ በሼፈር ተራራ ሰፈሩ። ከሼፌር ተራራ ተነሥተው በመጓዝ በሐራዳ ሰፈሩ። ከሐራዳ ተነሥተው በመጓዝ በማቅሔሎት ሰፈሩ። ከማቅሔሎት ተነሥተው በመጓዝ በታሐት ሰፈሩ፤ ከታሐት ተነሥተው በመጓዝ በታራ ሰፈሩ። ከታራ ተነሥተው በመጓዝ በሚትቃ ሰፈሩ። ከሚትቃ ተነሥተው በመጓዝ በሐሽሞና ሰፈሩ። ከሐሽሞና ተነሥተው በመጓዝ በሞሴሮት ሰፈሩ። ከሞሴሮት ተነሥተው በመጓዝ በቤኔያዕቃን ሰፈሩ። ከቤኔያዕቃን ተነሥተው በመጓዝ በሖርሃጊድጋድ ሰፈሩ። ከሖርሃጊድጋድ ተነሥተው በመጓዝ በዮጥባታ ሰፈሩ። ከዮጥባታ ተነሥተው በመጓዝ በዓብሮና ሰፈሩ። ከዓብሮና ተነሥተው በመጓዝ በዔጽዮንጋብር ሰፈሩ። ከዔጽዮንጋብር ተነሥተው በመጓዝ በጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ፤ ይህችም ቃዴስ ነች። ከቃዴስ ተነሥተው በመጓዝ በኤዶም ምድር ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ ሰፈሩ። ካህኑ አሮን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፤ በዚያም የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ። አሮንም በሖር ተራራ በሞተ ጊዜ ዕድሜው 123 ዓመት ነበር። በደቡብ ከነዓን በምትገኘው በዐራድ አገር የሚኖረው ከነዓናዊው የዐራድ ንጉሥ እስራኤላውያን መምጣታቸውን ሰማ። ከሖር ተራራ ተነሥተው በመጓዝ በጸልሞና ሰፈሩ። ከጸልሞና ተነሥተው በመጓዝ በፉኖን ሰፈሩ። ከፉኖን ተነሥተው በመጓዝ በኦቦት ሰፈሩ። ከኦቦት ተነሥተው በመጓዝ፥ በሞአብ ዳርቻ ባለው በዓባሪም ሰፈሩ። ከዓባሪም ተነሥተው በመጓዝ በዲቦንጋድ ሰፈሩ፤ ከዲቦን ጋድ ተነሥተው በመጓዝ በዓልሞንዲብላታይም ሰፈሩ። ከዓልሞንዲ ብላታይም ተነሥተው በመጓዝ በናባው ፊት ባሉት በዓብሪም ተራራዎች ላይ ሰፈሩ። ከዓብሪም ተራራዎች ተነሥተው በመጓዝ በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት ባለው በሞአብ ሜዳ ሰፈሩ። በዮርዳኖስም አጠገብ በሞአብ ሜዳ ላይ ከቤትየሺሞት እስከ አቤል ሹቲም ድረስ ሰፈሩ።

ዘኍል 33:1-49 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በሙሴና በአሮን ልጅ እየተመሩ በየሠራዊታቸው ሆነው ከግብጽ በወጡ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ያደረጉት ጉዞ ይህ ነበረ። ሙሴም በጌታ ትእዛዝ የጉዞአቸው መነሻ የሆኑትን ስፍራዎቻቸውን ጻፈ፤ እንደ መነሻ ስፍራዎቻቸው ጉዞአቸው እንዲህ ነበረ። በመጀመሪያው ወር ከወሩም በዓሥራ አምስተኛው ቀን ከራዓምሴ ተጓዙ፤ ከፋሲካ በኋላ በማግስቱ የእስራኤል ልጆች ግብፃውያን ሁሉ እያዩ ከፍ ባለች እጅ ወጡ። በዚያም ጊዜ ግብፃውያን ጌታ የገደላቸውን በኩሮቻቸውን ሁሉ ይቀብሩ ነበር፤ በአማልክቶቻቸውም ላይ ደግሞ ጌታ ፈረደባቸው። የእስራኤልም ልጆች ከራዓምሴ ተጉዘው በሱኮት ሰፈሩ። ከሱኮትም ተጉዘው በምድረ በዳ ዳርቻ ባለች በኤታም ሰፈሩ። ከኤታምም ተጉዘው በበኣልዛፎን ፊት ወደ ነበረች ወደ ፊሀሒሮት ተመለሱ፤ በሚግዶልም ፊት ለፊት ሰፈሩ። ከፊሀሒሮትም ተጉዘው ባሕሩን በመሻገር ወደ ምድረ በዳ አለፉ፤ በኤታምም በረሀ የሦስት ቀን መንገድ ሄደው በማራ ሰፈሩ። ከማራም ተጉዘው ወደ ኤሊም መጡ፤ በኤሊምም ዐሥራ ሁለት የውኃ ምንጮች ሰባ ዘንባቦችም ነበሩ፤ በዚያም ሰፈሩ። ከኤሊምም ተጉዘው በኤርትራ ባሕር ዳር ሰፈሩ። ከኤርትራም ባሕር ተጉዘው በሲን ምድረ በዳ ሰፈሩ። ከሲን ምድረ በዳም ተጉዘው በራፋቃ ሰፈሩ። ከራፋቃም ተጉዘው በኤሉስ ሰፈሩ። ከኤሉስም ተጉዘው በራፊዲም ሰፈሩ በዚያም ሕዝቡ የሚጠጡት ውኃ አልነበረም። ከራፊዲምም ተጉዘው በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ። ከሲናም ምድረ በዳ ተጉዘው በኬብሮን-ሐታማ ሰፈሩ። ከኬብሮን-ሐታማም ተጉዘው በሐጼሮት ሰፈሩ። ከሐጼሮትም ተጉዘው በሪትማ ሰፈሩ። ከሪትማም ተጉዘው በሬሞን ዘፋሬስ ሰፈሩ። ከሬሞን ዘፋሬስም ተጉዘው በልብና ሰፈሩ። ከልብናም ተጉዘው በሪሳ ሰፈሩ። ከሪሳም ተጉዘው በቀሄላታ ሰፈሩ። ከቀሄላታም ተጉዘው በሻፍር ተራራ ሰፈሩ። ከሻፍር ተራራም ተጉዘው በሐራዳ ሰፈሩ። ከሐራዳም ተጉዘው በመቅሄሎት ሰፈሩ። ከመቅሄሎትም ተጉዘው በታሐት ሰፈሩ። ከታሐትም ተጉዘው በታራ ሰፈሩ። ከታራም ተጉዘው በሚትቃ ሰፈሩ። ከሚትቃም ተጉዘው በሐሽሞና ሰፈሩ። ከሐሽሞናም ተጉዘው በሞሴሮት ሰፈሩ። ከሞሴሮትም ተጉዘው በብኔያዕቃን ሰፈሩ። ከብኔያዕቃንም ተጉዘው በሖርሃጊድጋድ ሰፈሩ። ከሖርሃጊድጋድም ተጉዘው በዮጥባታ ሰፈሩ። ከዮጥባታም ተጉዘው በዔብሮና ሰፈሩ። ከዔብሮናም ተጉዘው በዔጽዮንጋብር ሰፈሩ። ከዔጽዮንጋብርም ተጉዘው በጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ፤ ይህችም ቃዴስ ናት። ከቃዴስም ተጉዘው በኤዶምያስ ምድር ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ ሰፈሩ። ካህኑም አሮን በጌታ ትእዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፥ በዚያም የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ። አሮንም በሖር ተራራ በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሀያ ሦስት ዓመት ነበር። በከነዓን ምድርም በደቡብ በኩል ተቀምጦ የነበረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ የእስራኤል ልጆች እንደመጡ ሰማ። እነርሱም ከሖር ተራራ ተጉዘው በሴልሞና ሰፈሩ። ከሴልሞናም ተጉዘው በፉኖን ሰፈሩ። ከፋኖንም ተጉዘው በአቦት ሰፈሩ። ከአቦትም ተጉዘው በሞዓብ ዳርቻ ባለው በዒዬዓባሪም ሰፈሩ። በዒዬዓባሪም ተጉዘው በዲቦንጋድ ሰፈሩ። ከዲቦንጋድም ተጉዘው በዓልሞንዲብላታይም ሰፈሩ። ከዓልሞንዲብላታይምም ተጉዘው በናባው ፊት ባሉ በዓብሪም ተራሮች ላይ ሰፈሩ። ከዓብሪምም ተራሮች ተጉዘው በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ባለው በሞዓብ ሜዳ ሰፈሩ። በዮርዳኖስም አጠገብ በሞዓብ ሜዳ ላይ ከቤትየሺሞት እስከ አቤልሰጢም ድረስ ሰፈሩ።