ዘኍልቍ 31:1-24

ዘኍልቍ 31:1-24 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በቀል ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንን ተበ​ቀል፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ወገ​ኖ​ችህ ትጨ​መ​ራ​ለህ።” ሙሴም ለሕ​ዝቡ እን​ዲህ ብሎ ነገ​ራ​ቸው፥ “ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ሰዎ​ችን አስ​ታ​ጥቁ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ምድ​ያ​ምን ይበ​ቀሉ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከም​ድ​ያም ጋር ይሰ​ለፉ። ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ሁሉ ከየ​ነ​ገዱ አንድ አንድ ሺህ ሰው ወደ ጦር​ነት ስደዱ፤” ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አእ​ላ​ፋት፥ ከየ​ነ​ገዱ አንድ አንድ ሺህ ቈጠሩ፤ ለጦ​ር​ነት የተ​ሰ​ለ​ፉ​ትም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሆኑ። ሙሴም ከየ​ነ​ገዱ አንድ ሺህ ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸ​ውና ከካ​ህኑ ከአ​ሮን ልጅ ከአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ከፊ​ን​ሐስ ጋር ሰደደ፤ ንዋ​ያተ ቅድ​ሳ​ቱና ምል​ክት መስጫ መለ​ከ​ቶ​ችም በእ​ጆ​ቻ​ቸው ነበሩ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ ከም​ድ​ያም ጋር ተዋጉ፤ ወን​ዶ​ች​ንም ሁሉ ገደሉ። የም​ድ​ያ​ም​ንም ነገ​ሥ​ታት በዚ​ያው ጦር​ነት በአ​ን​ድ​ነት ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ አም​ስ​ቱም የም​ድ​ያም ነገ​ሥ​ታት ኤዊ፥ ሮቆም፥ ሱር፥ ሑር፥ ሮባቅ ነበሩ፤ የቢ​ዖ​ር​ንም ልጅ በለ​ዓ​ምን ደግሞ በዚ​ያው ጦር​ነት በሰ​ይፍ ገደ​ሉት። የም​ድ​ያ​ም​ንም ሴቶ​ችና ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ማረኩ፤ እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ዕቃ​ቸ​ውን፥ ንብ​ረ​ታ​ቸ​ው​ንና ኀይ​ላ​ቸ​ውን በዘ​በዙ። የተ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ውን ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ፥ ሰፈ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ በእ​ሳት አቃ​ጠሉ። ከሰው እስከ እን​ስሳ ምር​ኮ​አ​ቸ​ው​ንና ብዝ​በ​ዛ​ቸ​ውን ሁሉ ወሰዱ። የማ​ረ​ኩ​ትን ምር​ኮ​ው​ንና የዘ​ረ​ፉ​ትን ወደ ሙሴና ወደ ካህኑ ወደ አል​ዓ​ዛር፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት በሞ​ዓብ ሜዳ ወዳ​ለው ሰፈር አመጡ። ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርም፥ የማ​ኅ​በ​ሩም አለ​ቆች ሁሉ ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ ሊገ​ና​ኙ​አ​ቸው ወጡ። ሙሴም ከዘ​መቻ በተ​መ​ለ​ሱት በጭ​ፍራ አለ​ቆች፥ በሻ​ለ​ቆ​ችና በመቶ አለ​ቆች ላይ ተቈጣ። ሙሴም አላ​ቸው፥ “ሴቶ​ችን ሁሉ ለምን አዳ​ና​ች​ኋ​ቸው? እነ​ርሱ በበ​ለ​ዓም ምክር በፌ​ጎር ምክ​ን​ያት የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች የሚ​ያ​ስቱ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል እን​ዲ​ስቱ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ዕን​ቅ​ፋ​ቶች ናቸ​ውና፤ ስለ​ዚ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማኅ​በር ላይ መቅ​ሠ​ፍት ሆኖ​አል፤ አሁ​ንም እን​ግ​ዲህ ወን​ዱን ሁሉ በአ​ለ​በት ግደሉ፥ ወን​ድ​ንም የም​ታ​ው​ቀ​ውን ሴት ሁሉ ግደሉ። ወን​ድን የማ​ያ​ው​ቁ​ትን ሴቶች ልጆ​ችን ሁሉ ግን አድ​ኑ​አ​ቸው። እና​ን​ተም ከሰ​ፈሩ ውጭ ሰባት ቀን ስፈሩ፤ ሰውን የገ​ደለ ሁሉ፥ የተ​ገ​ደ​ለ​ው​ንም የዳ​ሰሰ ሁሉ፥ እና​ን​ተና የማ​ረ​ካ​ች​ኋ​ቸ​ውም በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውና በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ንጹሕ አድ​ርጉ። ልብ​ስ​ንም፥ ከቁ​ር​በ​ትም የተ​ዘ​ጋ​ጀ​ውን ሁሉ፥ ከፍ​የ​ልም ጠጕር፥ ከዕ​ን​ጨ​ትም የተ​ሠ​ራ​ውን ሁሉ ንጹሕ አድ​ርጉ።” ካህ​ኑም አል​ዓ​ዛር ከሰ​ልፍ የመ​ጡ​ትን ሰዎች አላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን ያዘ​ዘው የሕጉ ሥር​ዐት ይህ ነው፤ ወር​ቁና ብሩ፥ ናሱም፥ ብረ​ቱም፥ ቆር​ቆ​ሮ​ውም፥ እር​ሳ​ሱም፥ በእ​ሳት ለማ​ለፍ የሚ​ች​ለው ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ ይሆ​ናል፤ ነገር ግን በማ​ን​ጻት ውኃ ደግሞ ይጠ​ራል። በእ​ሳ​ትም ለማ​ለፍ የማ​ይ​ች​ለ​ውን በውኃ ታሳ​ል​ፉ​ታ​ላ​ችሁ። በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ልብ​ሳ​ች​ሁን እጠቡ፤ ንጹ​ሓ​ንም ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ትቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።”

ዘኍልቍ 31:1-24 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔር ሙሴን፣ “ለእስራኤላውያን ምድያማውያንን ተበቀልላቸው፤ ከዚያም ወደ ወገኖችህ ትከማቻለህ” አለው። ስለዚህ ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፤ “ምድያማውያንን ለመውጋት እንዲሄዱና ስለ እግዚአብሔርም እንዲበቀሏቸው ከሰዎቻችሁ ጥቂቶቹን ለጦርነት አዘጋጁ። ከእያንዳንዱም የእስራኤል ነገድ አንዳንድ ሺሕ ሰው ለጦርነቱ ላኩ።” ስለዚህ ከእስራኤል ጐሣዎች ተወጣጥቶ ከእያንዳንዱ ነገድ አንድ ሺሕ፣ በአጠቃላይ ዐሥራ ሁለት ሺሕ ሰው ለጦርነት ተዘጋጀ። ሙሴም የቤተ መቅደሱን ንዋየ ቅድሳትና ምልክት መስጫ የሆኑትን መለከቶች ከያዘው ከካህኑ ከአልዓዛር ልጅ ከፊንሐስ ጋራ ከየነገዱ አንዳንድ ሺሕ ሰው ለጦርነት ላከ። እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ከምድያም ጋራ ተዋጉ፤ ወንዱንም በሙሉ ፈጁት፤ ከተገደሉትም መካከል ዐምስቱ የምድያም ነገሥታት ኤዊ፣ ሮቆም፣ ሱር፣ ሑርና ሪባ ይገኙባቸዋል፤ የቢዖርን ልጅ በለዓምንም በሰይፍ ገደሉት። ከዚያም እስራኤላውያን የምድያማውያንን ሴቶችና ሕፃናት ማረኩ፤ የቀንድ ከብቶቻቸውን፣ የበግና የፍየል መንጋዎቻቸውን ሁሉ ነዱ፤ ሀብታቸውንም በሙሉ ወሰዱ። ምድያማውያኑ የሚኖሩባቸውን ከተሞች ሁሉ ሰፈሮቻቸውንም በሙሉ አቃጠሉ። ሰውና እንስሳትን ጨምሮ የማረኩትንና የዘረፉትን ሁሉ እንዳለ አጋዙት። የማረኳቸውን ሰዎች፣ የነዷቸውን እንስሳትና የዘረፉትን ሀብት በሙሉ፣ ከኢያሪኮ ማዶ፣ በዮርዳኖስ አጠገብ፣ በሞዓብ ወዳለው፣ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር እንዲሁም መላው የእስራኤላውያን ማኅበር ወዳሉበት ሰፈራቸው አመጧቸው። ሙሴ፣ ካህኑ አልዓዛርና የማኅበረ ሰቡ መሪዎች በሙሉ ሊቀበሏቸው ከሰፈር ወጡ። ሙሴም ከጦርነት በተመለሱት በሰራዊቱ አዛዦች፣ ማለትም በሻለቆችና በመቶ አለቆች ላይ ተቈጣ። ሙሴም እንዲህ አላቸው፤ “ሴቶችን ሁሉ እንዴት በሕይወት ትተዉአቸዋላችሁ? የበለዓምን ምክር ተቀብለው በፌጎር በተፈጸመው ድርጊት እስራኤላውያን ከእግዚአብሔር እንዲመለሱና የእግዚአብሔርም ሕዝብ እንዲቀሠፍ ያደረጉት እነርሱ ናቸው። አሁንም ወንዶቹን ልጆች ሁሉ፣ ወንድ ያወቁትንም ሴቶች በሙሉ ግደሏቸው፤ ነገር ግን ወንድ ያላወቁትን ልጃገረዶች ሁሉ ለራሳችሁ አስቀሯቸው። “ከእናንተ መካከል ሰው የገደለ ወይም የተገደለውን የነካ ሁሉ ከሰፈር ውጭ ሰባት ቀን ይቈይ። በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ራሳችሁንና ምርኮኞቻችሁን አንጹ። ማንኛውንም ልብስ እንዲሁም ከቈዳ፣ ከፍየል ጠጕር ወይም ከዕንጨት የተሠራ ማንኛውንም ነገር አንጹ።” ከዚያም ካህኑ አልዓዛር ወደ ጦርነት ሄደው የነበሩትን ወታደሮች እንዲህ አላቸው፤ “እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠው የሕጉ ሥርዐት ይህ ነው፤ ወርቅ፣ ብር፣ ናስ፣ ብረት፣ ቈርቈሮ፣ እርሳስ እንዲሁም እሳትን መቋቋም የሚችል ማንኛውም ነገር በእሳት ውስጥ ማለፍ አለበት፤ ከዚያም ንጹሕ ይሆናል፤ ይህም ሆኖ መንጻት አለበት። እሳትን መቋቋም የማይችል ማንኛውም ነገር በዚሁ ውሃ ውስጥ ማለፍ አለበት። በሰባተኛው ቀን ልብሳችሁን ዕጠቡ፤ ትነጻላችሁም፤ ከዚያም ወደ ሰፈር መግባት ትችላላችሁ።”

ዘኍልቍ 31:1-24 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ ስለ እስራኤል ልጆች በቀል ምድያማውያንን ተበቀል፤ ከዚያም በኋላ ወደ ወገኖችህ ትከማቻለህ። ሙሴም ሕዝቡን፦ ከእናንተ መካከል ሰዎች ለጦርነት ይሰለፉ፤ ስለ እግዚአብሔር በቀል ምድያምን ይበቀሉ ዘንድ በምድያም ላይ ይሂዱ፤ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ከየነገዱ አንድ ሺህ ሰው ወደ ጦርነት ስደዱ ብሎ ተናገራቸው። ከእስራኤልም አእላፋት አሥራ ሁለት ሺህ፥ ከየነገዱ አንድ አንድ ሺህ፥ ለጦርነት የተሰለፉ ሰዎች ተሰጡ። ሙሴም ከየነገዱ አንድ አንድ ሺህ ወደ ጦርነት ሰደደ፤ እነርሱንና የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ወደ ጦርነት ሰደዳቸው፤ የመቅደሱንም ዕቃ የሚነፋውንም መለከት በእጁ ሰጠው። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘ ከምድያም ጋር ተዋጉ፥ ወንዶችንም ሁሉ ገደሉ። ከተገደሉትም ጋር የምድያምን ነገሥታት ገደሉአቸው፤ አምስቱም የምድያም ነገሥታት ኤዊ፥ ሮቆም፥ ሱር፥ ሑር፥ ሪባ ነበሩ፤ የቢዖርንም ልጅ በለዓምን ደግሞ በሰይፍ ገደሉት። የእስራኤልም ልጆች የምድያምን ሴቶችና ልጆቻቸውን ማረኩ፤ እንስሶቻቸውንና መንጎቻቸውንም ዕቃቸውንም ሁሉ በዘበዙ። የተቀመጡባቸውን ከተሞቻቸውን ሁሉ ሰፈሮቻቸውንም ሁሉ በእሳት አቃጠሉ። የሰውንና የእንስሳን ምርኮና ብዝበዛ ሁሉ ወሰዱ። የማረኩአቸውንም ሰዎች ምርኮውንና ብዝበዛውን ወደ ሙሴና ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር፥ በዮርዳኖስም አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ወዳለው ሰፈር አመጡ። ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም የማኅበሩም አለቆች ሁሉ ከሰፈሩ ወደ ውጭ ሊገናኙአቸው ወጡ። ሙሴም ከዘመቻ በተመለሱት በጭፍራ አለቆች፥ በሻለቆችና በመቶ አለቆች ላይ ተቈጣ። ሙሴም አላቸው፦ በውኑ ሴቶችን ሁሉ አዳናችኋቸውን? እነሆ፥ እነዚህ በፌጎር ምክንያት በበለዓም ምክር እግዚአብሔርን ይበድሉ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ዕንቅፋት ሆኑ፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር ማኅበር ላይ መቅሠፍት ሆነ። አሁን እንግዲህ ከልጆቹ ወንዱን ሁሉ ግደሉ፥ ወንድንም በመኝታ የሚያውቁትን ሴቶች ሁሉ ግደሉ። ወንድን የማያውቁትን ሴቶች ልጆችን ሁሉ ግን ለራሳችሁ አድኑአቸው። ከሰፈሩም ውጭ ሰባት ቀን ስፈሩ፤ ሰውን የገደለ ሁሉ የተገደለውንም የዳሰሰ ሁሉ፥ እናንተ የማረካችኋቸውም በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሰውነታችሁን ንጹሕ አድርጉ። ልብስንም፥ ከቁርበትም የተዘጋጀውን ሁሉ፥ ከፍየልም ጠጕር ከእንጨትም የተሠራውን ሁሉ ንጹሕ አድርጉ። ካህኑም አልዓዛር ከሰልፍ የመጡትን ሰዎች አላቸው፦ እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘው የሕጉ ሥርዓት ይህ ነው፤ ወርቁንና ብሩን፥ ናሱንም፥ ብረቱንም፥ ቆርቆሮውንም፥ አረሩንም፥ በእሳት ለማለፍ የሚችለውን ሁሉ በእሳት ታሳልፉታላችሁ፥ ንጹሕም ይሆናል፤ ነገር ግን በማንጻት ውኃ ደግሞ ይጠራል። በእሳትም ለማለፍ የማይችለውን በውኃ ታሳልፉታላችሁ። በሰባተኛውም ቀን ልብሳችሁን እጠቡ፥ ንጹሕም ትሆናላችሁ፤ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ትቀርባላችሁ።

ዘኍልቍ 31:1-24 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በእስራኤል ሕዝብ ላይ ስለ ፈጸሙት በደል ምድያማውያንን ቅጣ፤ ይህንንም ካደረግህ በኋላ አንተ ትሞታለህ።” ስለዚህ ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አለ፦ “ምድያማውያን በእግዚአብሔር ላይ ስለ ፈጸሙት በደል አደጋ ጥላችሁ ትበቀሉአቸው ዘንድ ለጦርነት ተዘጋጁ፤ ከእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ አንዳንድ ሺህ ወንዶችን መርጣችሁ ወደ ጦርነቱ ላኩ።” ስለዚህ ከብዙ ሺህ እስራኤላውያን መካከል ከያንዳንዱ ነገድ አንዳንድ ሺህ ተውጣጥቶ ዐሥራ ሁለት ሺህ የታጠቀ ሠራዊት ለጦርነት ተዘጋጀ። ሙሴም ከየነገዱ አንዳንድ ሺህ ሰው በካህኑ በአልዓዛር ልጅ በፊንሐስ መሪነት ወደ ጦርነት ላካቸው፤ ፊንሐስም ከመቅደሱ አንዳንድ ንዋየ ቅድሳትንና ለጦርነት መቀስቀሻ (ክተት) የሚሆን መለከት በእጁ ይዞ ነበር። እነርሱም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በምድያማውያን ላይ አደጋ ጥለው ወንዶቹን በሙሉ ገደሉ። አምስቱንም የምድያም ነገሥታት ኤዊን፥ ሬቄምን፥ ጹርን፥ ሑርንና ሬባዕን ገደሉ፤ የቢዖርን ልጅ በለዓምንም ገደሉት። የእስራኤል ሕዝብ ምድያማውያን ሴቶችንና ሕፃናትን ማረኩ፤ የከብት፥ የበግና የፍየል መንጋዎቻቸውን ወሰዱ፤ ሀብታቸውን ሁሉ በዘበዙ፤ ከተሞቻቸውንና የሰፈሩበትን ቦታ ሁሉ አቃጠሉ፤ እስረኞችንና እንስሶችን ሳይቀር የማረኩትን ነገር ሁሉ ሰብስበው ከዮርዳኖስ ማዶ በኢያሪኮ ትይዩ በሞአብ ሜዳ ላይ ሰፍረው ወደነበሩት ወደ ሙሴና ወደ አልዓዛር እንዲሁም ወደ መላው ማኅበር አመጡአቸው። ሙሴ፥ አልዓዛርና ሌሎቹም የማኅበሩ መሪዎች ሠራዊቱን ለመቀበል ከሰፈር ወጡ፤ ሙሴ ግን ከጦርነት በተመለሱት በጭፍራ አለቆች፥ በሻለቆችና በመቶ አለቆች ላይ ተቈጣ፤ እንዲህም ሲል ጠየቃቸው፦ “ሴቶችን በሙሉ በሕይወት ያስቀራችሁት ለምንድን ነው? በፔዖር ሳለን የበለዓምን ምክር ተቀብለው ሕዝቡ በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን እምነት እንዲተዉ ያደረጉ ሴቶች መሆናቸውን ዘነጋችሁን? በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ የአባር ቸነፈር መቅሠፍት ያመጣም ያ ስሕተት ነበር። ስለዚህ አሁን እያንዳንዱን ወንድ ልጅና እያንዳንዲቱን ከወንድ ጋር የተገናኘች ሴት ግደሉ። ነገር ግን ከወንድ ጋር ያልተገናኙትን ልጃገረዶቹን በሕይወት እንዲኖሩ አድርጋችሁ ለራሳችሁ አስቀሩ። ከእናንተ መካከል ሰው የገደለ ወይም ሬሳ የነካ ሁሉ ለሰባት ቀን ከሰፈር ውጪ ይቈይ፤ በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ራሳችሁንና የማረካችኋቸውን ሴቶች አንጹ። እንዲሁም ማንኛውንም ልብስ ወይም ከቈዳ፥ ከፍየል ጠጒር ወይም ከእንጨት የተሠራ ነገር ሁሉ አጽዱ።” ካህኑ አልዓዛር ከዘመቻ ለተመለሱት ወንዶች እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠው የሕጉ ሥርዓት መመሪያዎች እነዚህ ናቸው፦ እንደ ወርቅ፥ ብር፥ ነሐስ፥ ብረት፥ ቆርቆሮ ወይም እርሳስ የመሳሰሉ እሳት የማይጐዳቸው ነገሮች በእሳት ውስጥ አልፈው መጥራት ይኖርባቸዋል፤ እሳት መቋቋም የማይችለውን ነገር ሁሉ ለመንጻት ሥርዓት በተመደበው ውሃ ታጠሩታላችሁ። በሰባተኛው ቀን ልብሳችሁን ታጥባላችሁ፤ ከዚያም በኋላ የነጻችሁ ስለምትሆኑ ወደ ሰፈር መግባት ይፈቀድላችኋል።”

ዘኍልቍ 31:1-24 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ስለ እስራኤል ልጆች በቀል ምድያማውያንን ተበቀል፤ ከዚያም በኋላ ወደ ወገኖችህ ትከማቻለህ።” ሙሴም ሕዝቡን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ “ከእናንተ መካከል ሰዎች ለጦርነት የተዘጋጁ ይሁኑ፤ ስለ ጌታ በቀል ምድያምን እንዲበቀሉ በምድያም ላይ ይዝመቱ፤ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ከየነገዱ አንድ ሺህ ሰው ወደ ጦርነት ላኩ።” ከብዙ ሺህ እስራኤላውያን መካከል ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከየነገዱ አንድ አንድ ሺህ፥ ለጦርነት የተዘጋጁ ሰዎች ተመለመሉ። ሙሴም ከየነገዱ አንድ አንድ ሺህ ወደ ጦርነት ላከ፤ እነርሱንና የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ወደ ጦርነት ላካቸው፤ የመቅደሱንም ዕቃ የሚነፋውንም የማስጠንቀቂያ መለከት በእጁ ሰጠው። ጌታም ሙሴን እንዳዘዘ ከምድያም ጋር ተዋጉ፥ ወንዶችንም ሁሉ ገደሉ። ከተገደሉትም ጋር የምድያምን ነገሥታት ገደሉአቸው፤ አምስቱም የምድያም ነገሥታት ኤዊ፥ ሮቆም፥ ሱር፥ ሑር፥ ሪባ ነበሩ፤ የቢዖርንም ልጅ በለዓምን ደግሞ በሰይፍ ገደሉት። የእስራኤልም ልጆች የምድያምን ሴቶችና ልጆቻቸውን ማረኩ፤ እንስሶቻቸውንና መንጎቻቸውንም ዕቃቸውንም ሁሉ በዘበዙ። የተቀመጡባቸውን ከተሞቻቸውን ሁሉ ሰፈሮቻቸውንም ሁሉ በእሳት አቃጠሉ። የሰውንና የእንስሳን ምርኮና ብዝበዛ ሁሉ ወሰዱ። የማረኩአቸውንም ሰዎች ምርኮውንና ብዝበዛውን፥ በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ወዳለው ሰፈር፥ ወደ ሙሴና ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር አመጡ። ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም የማኅበሩም አለቆች ሁሉ ከሰፈሩ ወደ ውጭ ሊገናኙአቸው ወጡ። ሙሴም ከዘመቻ በተመለሱት በጦሩ አዛዦች፥ በሻለቆችና በመቶ አለቆች ላይ ተቈጣ። ሙሴም አላቸው፦ “በውኑ ሴቶችን ሁሉ በሕይወት እንዲኖሩ ፈቀዳችሁላቸውን? እነሆ፥ እነዚህ በፌጎር ምክንያት በበለዓም ምክር ጌታን አታልለው ለእስራኤል ልጆች ዕንቅፋት ሆኑ፤ በዚህም ምክንያት በጌታ ማኅበር ላይ መቅሠፍት ሆነ። አሁን እንግዲህ ከልጆቹ ወንዱን ሁሉ ግደሉ፥ ወንድንም በመኝታ የሚያውቁትን ሴቶች ሁሉ ግደሉ። ወንድን በመኝታ የማያውቁትን ሴቶች ልጆችን ሁሉ ግን ለራሳችሁ በሕይወት አቆዩዋቸው። ከሰፈሩም ውጭ ሰባት ቀን ስፈሩ፤ ከእናንተም ሰውን የገደለ ሁሉ የተገደለውንም የነካ ሁሉ፥ በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ራሳችሁንና እናንተ የማረካችኋቸውን አንጹ። ልብስንም፥ ከቁርበትም የተዘጋጀውን ሁሉ፥ ከፍየልም ጠጉር ከእንጨትም የተሠራውን ሁሉ አንጹ።” ካህኑም አልዓዛር ከጦርነት የተመለሱትን ወታደሮች እንዲህ አለ፦ “ጌታ ሙሴን ያዘዘው የሕጉ ሥርዓት ይህ ነው፤ ወርቁንና ብሩን፥ ናሱንም፥ ብረቱንም፥ ቆርቆሮውንም፥ እርሳሱንም፥ በእሳት ለማለፍ የሚችለውን ሁሉ በእሳት ታሳልፉታላችሁ፥ ንጹሕም ይሆናል፤ ነገር ግን በማንጻት ውኃ ደግሞ ይጠራል። በእሳትም ለማለፍ የማይችለውን በውኃ ታሳልፉታላችሁ። በሰባተኛውም ቀን ልብሳችሁን ታጥባላችሁ፥ ንጹሕም ትሆናላችሁ፤ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ትገባላችሁ።”