የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘኍል 26:1-51

ዘኍል 26:1-51 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እን​ዲ​ህም ሆነ፦ መቅ​ሠ​ፍቱ ከሆነ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴ​ንና ካህ​ኑን አል​ዓ​ዛ​ርን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ “ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለ​ውን፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጣ​ውን ሁሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ቍጠሩ።” ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርም በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት በሞ​ዓብ ሜዳ ላይ እን​ዲህ ብለው ነገ​ሩ​አ​ቸው፦ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ከሃያ ዓመት ጀምሮ፥ ከዚ​ያም በላይ ያለ​ውን ሕዝብ ቍጠሩ።” ከግ​ብፅ ምድር የወጡ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እነ​ዚህ ናቸው። የእ​ስ​ራ​ኤል በኵር ሮቤል፤ የሮ​ቤል ልጆች፤ ከሄ​ኖኅ የሄ​ኖ​ኃ​ው​ያን ወገን፤ ከፈ​ሉስ የፈ​ሉ​ሳ​ው​ያን ወገን። ከአ​ስ​ሮን የአ​ስ​ሮ​ና​ው​ያን ወገን፤ ከከ​ርሚ የከ​ር​ማ​ው​ያን ወገን። እነ​ዚህ የሮ​ቤ​ላ​ው​ያን ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት አርባ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ። የፈ​ሉ​ስም ልጆች፤ ኤል​ያብ። የኤ​ል​ያ​ብም ልጆች፥ ናሙ​ኤል፥ ዳታን፥ አቤ​ሮን፤ እነ​ዚ​ህም ከማ​ኅ​በሩ የተ​መ​ረጡ ነበሩ፤ ከቆሬ ወገን ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ባመፁ ጊዜ ሙሴ​ንና አሮ​ንን ተጣሉ፤ ማኅ​በ​ሩም በሞቱ ጊዜ ምድ​ሪቱ አፍ​ዋን ከፍታ ከቆሬ ጋር ዋጠ​ቻ​ቸው፤ በዚ​ያም ጊዜ እሳ​ቲቱ ሁለት መቶ አም​ሳ​ውን ሰዎች አቃ​ጠ​ለ​ቻ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ለም​ል​ክት ሆኑ። የቆሬ ልጆች ግን አል​ሞ​ቱም። የስ​ም​ዖ​ንም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ከና​ሙ​ሄል የና​ሙ​ሄ​ላ​ው​ያን ወገን፥ ከኢ​ያ​ሚን የኢ​ያ​ሚ​ና​ው​ያን ልጆች ወገን፥ ከያ​ክን የያ​ክ​ና​ው​ያን ልጆች ወገን፥ ከዛራ የዛ​ራ​ው​ያን ልጆች ወገን፥ ከሳ​ው​ኡል የሳ​ው​ኡ​ላ​ው​ያን ወገን። እነ​ዚህ የስ​ም​ዖ​ና​ው​ያን ወገ​ኖች ናቸው፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ውም ሃያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። የይ​ሁዳ ልጆች ኤርና አው​ናን፥ ሴሎ​ምና ፋሬስ ዛራም፤ ዔርና አው​ና​ንም በከ​ነ​ዓን ምድር ሞቱ። የይ​ሁ​ዳም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ከሴ​ሎም የሴ​ሎ​ማ​ው​ያን ወገን፥ ከፋ​ሬስ የፋ​ሬ​ሳ​ው​ያን ወገን፥ ከዛራ የዛ​ራ​ው​ያን ወገን። የፋ​ሬ​ስም ልጆች፤ ከኤ​ስ​ሮም የኤ​ስ​ሮ​ማ​ው​ያን ወገን፥ ከያ​ሙ​ሔል የያ​ሙ​ሔ​ላ​ው​ያን ወገን። እነ​ዚህ የይ​ሁዳ ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሰባ ስድ​ስት ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ። የይ​ሳ​ኮር ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ከቶላ የቶ​ላ​ው​ያን ወገን፥ ከፉሓ የፉ​ሓ​ው​ያን ወገን፤ ከያ​ሱብ የያ​ሱ​ባ​ው​ያን ወገን፥ ከሥ​ምራ የሥ​ም​ራ​ው​ያን ወገን። እነ​ዚህ የይ​ሳ​ኮር ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት ስድሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። የዛ​ብ​ሎን ወገ​ኖች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ ከሳ​ሬድ የሳ​ሬ​ዳ​ው​ያን ወገን፥ ከኤ​ሎኒ የኤ​ሎ​ኒ​ያ​ው​ያን ወገን፥ ከያ​ሕ​ል​ኤል የያ​ሕ​ል​ኤ​ላ​ው​ያን ወገን። እነ​ዚህ የዛ​ብ​ሎን ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት ስድሳ ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ። የጋድ ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ከሳ​ፎን የሳ​ፎ​ና​ው​ያን ወገን፥ ከሐጊ የሐ​ጋ​ው​ያን ወገን፥ ከሱኒ የሱ​ኒ​ያ​ው​ያን ወገን፤ ከኤ​ዜን የኤ​ዜ​ና​ው​ያን ወገን፥ ከሳ​ድፍ የሳ​ዳ​ፋ​ው​ያን ወገን፤ ከአ​ሮ​ሐድ የአ​ሮ​ሐ​ዳ​ው​ያን ወገን፥ ከአ​ሩ​ሔል የአ​ሩ​ሔ​ላ​ው​ያን ወገን። እነ​ዚህ የጋድ ልጆች ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት አርባ አራት ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ። የአ​ሴር ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ከኢ​ያ​ምን የኢ​ያ​ም​ና​ው​ያን ወገን፥ ከኢ​ያሱ የኢ​ያ​ሱ​ያ​ው​ያን ወገን፥ ከበ​ርያ የበ​ር​ያ​ው​ያን ወገን። ከኮ​ቤር ልጆች፤ ከከ​ቤር የከ​ቤ​ራ​ው​ያን ወገን፥ ከሜ​ል​ክ​ያል የሜ​ል​ክ​ያ​ላ​ው​ያን ወገን። የአ​ሴ​ርም የሴት ልጁ ስም ሳራ ነበረ። እነ​ዚህ የአ​ሴር ልጆች ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት አርባ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። የዮ​ሴፍ ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ምና​ሴና ኤፍ​ሬም። የም​ናሴ ልጆች፤ ከማ​ኪር የማ​ኪ​ራ​ው​ያን ወገን፤ ማኪ​ርም ገለ​ዓ​ድን ወለደ፤ ከገ​ለ​ዓድ የገ​ለ​ዓ​ዳ​ው​ያን ወገን። የገ​ለ​ዓድ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ከአ​ክ​ያ​ዝር የአ​ክ​ያ​ዝ​ራ​ው​ያን ወገን፥ ከኬ​ሌግ የኬ​ሌ​ጋ​ው​ያን ወገን፥ ከኢ​ሳ​ር​ያል የኢ​ሳ​ር​ያ​ላ​ው​ያን ወገን፥ ከሴ​ኬም የሴ​ኬ​ማ​ው​ያን ወገን፥ ከሲ​ማ​ኤር የሲ​ማ​ኤ​ራ​ው​ያን ወገን፥ ከኦ​ፌር የኦ​ፌ​ራ​ው​ያን ወገን። የኦ​ፌ​ርም ልጅ ሰለ​ጰ​ዓድ ሴቶች ልጆች እንጂ ወን​ዶች ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​ትም፤ የሰ​ለ​ጰ​ዓ​ድም የሴ​ቶች ልጆቹ ስም መሐላ፥ ኑኃ፥ ሄግላ፥ ሚልካ፥ ቴርሳ ነበረ። እነ​ዚ​ህም የም​ናሴ ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት አምሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የኤ​ፍ​ሬም ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ከሱ​ቱላ የሱ​ቱ​ላ​ው​ያን ወገን ከጣ​ናህ የጣ​ና​ሃ​ው​ያን ወገን። እነ​ዚህ የሱ​ቱላ ልጆች ናቸው፤ ከዔ​ዴን የዔ​ዴ​ና​ው​ያን ወገን። እነ​ዚህ የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ወገ​ኖች ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሠላሳ ሁለት ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ። በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የዮ​ሴፍ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው። የብ​ን​ያም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ከበ​ዓሌ የበ​ዓ​ላ​ው​ያን ወገን፥ ከአ​ሲ​ቤር የአ​ሲ​ቤ​ራ​ው​ያን ወገን፥ ከአ​ኪ​ራን የአ​ኪ​ራ​ና​ው​ያን ወገን፥ ከሶ​ፋን የሶ​ፋ​ና​ው​ያን ወገን፥ የበ​ዓ​ሌም ልጆች አዴ​ርና ኖሐ​ማን፤ ከአ​ዴር የአ​ዴ​ራ​ው​ያን ወገን፥ ከኖ​ሐ​ማን የኖ​ሐ​ማ​ና​ው​ያን ወገን። በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የብ​ን​ያም ልጆች እነ​ዚህ ናቸው። ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት አርባ አም​ስት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበሩ። በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የዳን ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ከሰ​ምዒ፥ የሰ​ም​ዒ​ያ​ው​ያን ወገን፤ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የዳን ወገ​ኖች እነ​ዚህ ናቸው። የሰ​ም​ዒ​ያ​ው​ያን ወገ​ኖች ሁሉ ቍጥ​ራ​ቸው ስድሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። የን​ፍ​ታ​ሌም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ከአ​ሴ​ሔል የአ​ሴ​ሔ​ላ​ው​ያን ወገን፥ ከጎ​ሄኒ የጎ​ሄ​ና​ው​ያን ወገን፥ ከየ​ሴር የየ​ሴ​ራ​ው​ያን ወገን፥ ከሴ​ሌም የሴ​ሌ​ማ​ው​ያን ወገን። በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የን​ፍ​ታ​ሌም ወገ​ኖች እነ​ዚህ ናቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠ​ሩት አርባ አም​ስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የተ​ቈ​ጠ​ሩት እነ​ዚህ ናቸው፤ ስድ​ስት መቶ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ።

ዘኍል 26:1-51 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከመቅሠፍቱ በኋላ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴንና የካህኑን የአሮንን ልጅ አልዓዛርን እንዲህ አላቸው፤ “ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸውን፣ በእስራኤልም ጦር ሰራዊት ውስጥ ለማገልገል ብቃት ያላቸውን ሁሉ ከመላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ ከየቤተ ሰቡ ቍጠሩ።” ስለዚህ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው በሞዓብ ሜዳ ለሕዝቡ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፤ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ባዘዘው መሠረት ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ የሆነውን ቍጠሩ።” ከግብፅ የወጡት እስራኤላውያንም እነዚህ ነበሩ፤ የእስራኤል የበኵር ልጅ የሆነው የሮቤል ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤ በሄኖኀ በኩል፣ የሄኖኀውያን ጐሣ፤ በፈሉስ በኩል፣ የፈሉሳውያን ጐሣ፤ በአስሮን በኩል፣ የአስሮናውያን ጐሣ፤ በከርሚ በኩል፣ የከርማውያን ጐሣ፤ እነዚህ የሮቤል ጐሣዎች ሲሆኑ፤ ከእነዚህም የተቈጠሩት አርባ ሦስት ሺሕ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ። የፈሉስ ልጅ ኤልያብ ሲሆን፣ የኤልያብ ልጆች ደግሞ፣ ነሙኤል ዳታንና አቤሮን ነበሩ። እነዚሁ ዳታንና አቤሮን በሙሴና በአሮን ላይ ያመፁ የማኅበሩ ሹማምት ሲሆኑ፣ ቆሬና ተከታዮቹ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ላይ ባመፁ ጊዜ እነርሱም በነገሩ ነበሩበት። ሁለት መቶ አምሳዎቹን ሰዎች እሳት በበላቻቸው ጊዜ የቆሬ ተከታዮች ሲሞቱ እነዚህን ደግሞ ምድር ተከፍታ ከእርሱ ጋር ዋጠቻቸው፤ መቀጣጫም ሆኑ፤ የቆሬ የዘር ሐረግ ግን አልጠፋም። የስምዖን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በነሙኤል በኩል፣ የነሙኤላውያን ጐሣ፤ በያሚን በኩል፣ የያሚናውያን ጐሣ፤ በያኪን በኩል፣ የያኪናውያን ጐሣ፤ በዛራ በኩል፣ የዛራውያን ጐሣ፤ በሳኡል በኩል፣ የሳኡላውያን ጐሣ፤ እነዚህ የስምዖን ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩትም ሃያ ሁለት ሺሕ ሁለት መቶ ነበሩ። የጋድ ዘሮች በየጐሣዎቻቸው እነዚህ ነበሩ፤ በጽፎን በኩል፣ የጽፎናውያን ጐሣ፤ በሐጊ በኩል፣ የሐጋውያን ጐሣ፤ በሹኒ በኩል፣ የሹናውያን ጐሣ፤ በኤስና በኩል፣ የኤስናናውያን ጐሣ፤ በዔሪ በኩል፣ የዔራውያን ጐሣ፤ በአሮዲ በኩል፣ የአሮዳውያን ጐሣ፤ በአርኤሊ በኩል፣ የአርኤላውያን ጐሣ፤ እነዚህ የጋድ ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት አርባ ሺሕ አምስት መቶ ነበሩ። ዔርና አውናን የይሁዳ ልጆች ነበሩ፤ ነገር ግን በከነዓን ምድር ሞተዋል። የይሁዳ ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በሴሎም በኩል፣ የሴሎማውያን ጐሣ፤ በፋሬስ በኩል፣ የፋሬሳውያን ጐሣ፤ በዛራ በኩል፣ የዛራውያን ጐሣ፤ የፋሬስ ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በኤስሮም በኩል፣ የኤስሮማውያን ጐሣ፤ በሐሙል በኩል፣ የሐሙላውያን ጐሣ፤ እነዚህ የይሁዳ ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሰባ ስድስት ሺሕ አምስት መቶ ነበሩ። የይሳኮር ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በቶላ በኩል፣ የቶላውያን ጐሣ፣ በፋዋ በኩል፣ የፋዋውያን ጐሣ፣ በያሱብ በኩል፣ የያሱባውያን ጐሣ፣ በሺምሮን በኩል፣ የሺምሮናውያን ጐሣ፤ እነዚህ የይሳኮር ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ስድሳ አራት ሺሕ ሦስት መቶ ነበሩ። የዛብሎን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በሴሬድ በኩል፣ የሴሬዳውያን ጐሣ፤ በኤሎን በኩል፣ የኤሎናውያን ጐሣ፣ በያሕልኤል በኩል፣ የያሕልኤላውያን ጐሣ፤ እነዚህ የዛብሎን ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ስድሳ ሺሕ አምስት መቶ ነበሩ። የዮሴፍ ዘሮች በምናሴና በኤፍሬም በኩል ያሉት በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ የምናሴ ዘሮች፤ በማኪር በኩል፣ የማኪራውያን ጐሣ፤ ማኪርም የገለዓድ አባት ነው፤ በገለዓድ በኩል፣ የገለዓዳውያን ጐሣ፤ የገለዓድ ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤ በኢዔዝር በኩል፣ የኢዓዝራውያን ጐሣ፣ በኬሌግ በኩል፣ የኬሌጋውያን ጐሣ፣ በአሥሪኤል በኩል፣ የአሥሪኤላውያን ጐሣ፣ በሴኬም በኩል፣ የሴኬማውያን ጐሣ፣ በሸሚዳ በኩል፣ የሸሚዳውያን ጐሣ፣ በኦፌር በኩል፣ የኦፌራውያን ጐሣ፣ የኦፌር ልጅ ሰለጰዓድ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ ልጆቹ ሴቶች ብቻ ነበሩ፤ እነርሱም ማህለህ፣ ኑዓ፣ ዔግላ፣ ሚልካና ቲርጻ ይባላሉ። እነዚህ የምናሴ ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት አምሳ ሁለት ሺሕ ሰባት መቶ ነበሩ። የኤፍሬም ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በሱቱላ በኩል፣ የሱቱላውያን ጐሣ፣ በቤኬር በኩል፣ የቤኬራውያን ጐሣ፣ በታሐን በኩል፣ የታሐናውያን ጐሣ፤ የሱቱላ ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤ በዔዴን በኩል፣ የዔዴናውያን ጐሣ፤ እነዚህ የኤፍሬም ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሠላሳ ሁለት ሺሕ አምስት መቶ ነበሩ። እነዚህም በየጐሣቸው የተቈጠሩ የዮሴፍ ዘሮች ነበሩ። የብንያም ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በቤላ በኩል፣ የቤላውያን ጐሣ፣ በአስቤል በኩል፣ የአስቤላውያን ጐሣ፣ በአኪራን በኩል፣ የአኪራናውያን ጐሣ፣ በሶፋን በኩል፣ የሶፋናውያን ጐሣ፣ በሑፋም በኩል፣ የሑፋማውያን ጐሣ፤ የቤላ ዘሮች በአርድና በናዕማን በኩል፤ በአርድ በኩል፣ የአርዳውያን ጐሣ፣ በናዕማን በኩል፣ የናዕማናውያን ጐሣ፤ እነዚህ የብንያም ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህም የተቈጠሩት አርባ አምስት ሺሕ ስድስት መቶ ነበሩ። የዳን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በስምዔ በኩል፣ የሰምዔያውያን ጐሣዎች። እነዚህ እንግዲህ የዳን ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ሁሉም የሰምዔያውያን ጐሣዎች ነበሩ፤ ከእነዚህ የተቈጠሩት ደግሞ ስድሳ አራት ሺሕ አራት መቶ ነበሩ። የአሴር ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በዩምና በኩል፣ የዩምናውያን ጐሣ፣ በየሱዋ በኩል፣ የየሱዋውያን ጐሣ፣ በበሪዓ በኩል፣ የበሪዓውያን ጐሣ፤ እንዲሁም በበሪዓ ዘሮች በኩል፣ በሔቤር በኩል፣ የሔቤራውያን ጐሣ፣ በመልኪኤል በኩል፣ የመልኪኤላውያን ጐሣ። አሴር ሤራሕ የምትባል ልጅ ነበረችው። እነዚህ የአሴር ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት አምሳ ሦስት ሺሕ አራት መቶ ነበሩ። የንፍታሌም ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በያሕጽኤል በኩል፣ የያሕጽኤላውያን ጐሣ፣ በጉኒ በኩል፣ የጉናውያን ጐሣ፣ በዬጽር የዬጽራውያን ጐሣ፤ በሺሌም በኩል፣ የሺሌማውያን ጐሣ፤ እነዚህ የንፍታሌም ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት አርባ አምስት ሺሕ አራት መቶ ነበሩ። በአጠቃላይ የእስራኤል ወንዶች ቍጥር ስድስት መቶ አንድ ሺሕ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበር።

ዘኍል 26:1-51 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እንዲህም ሆነ፤ መቅሠፍቱ ከሆነ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴንና የካህኑን የአሮን ልጅ አልዓዛርን፦ ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን፥ በእስራኤል ወደ ሰልፍ የሚወጣውን ሁሉ፥ የእስራኤልን ልጆች ማኅበር ሁሉ በየአባቶቻቸው ቤት ቍጠሩ ብሎ ተናገራቸው። ሙሴና ካህኑ አልዓዛር በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ላይ፦ እግዚአብሔር ሙሴን ከግብፅም ምድር የወጡትን የእስራኤልን ልጆች እንዳዘዛቸው፥ ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን ሕዝቡን ቍጠሩ ብለው ተናገሩአቸው። የእስራኤል በኵር ሮቤል፤ የሮቤል ልጆች፤ ከሄኖኅ የሄኖኀውያን ወገን፥ ከፈሉስ የፈሉሳውያን ወገን፥ ከአስሮን የአስሮናውያን ወገን፥ ከከርሚ የከርማውያን ወገን። እነዚህ የሮቤላውያን ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት አርባ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ። የፈሉስም ልጆች፤ ኤልያብ። የኤልያብም ልጆች፤ ነሙኤል፥ ዳታን፥ አቤሮን፤ እነዚህ ዳታንና አቤሮን ከማኅበሩ የተመረጡ ነበሩ፤ ከቆሬ ወገን ጋር በእግዚአብሔር ላይ ባመፁ ጊዜ ሙሴንና አሮንን ተጣሉ፤ ያም ወገን በሞተ ጊዜ ምድሪቱ አፍዋን ከፍታ ከቆሬ ጋር ዋጠቻቸው፤ በዚያም ጊዜ እሳቲቱ ሁለት መቶ አምሳውን ሰዎች አቃጠለቻቸው፤ እነርሱም ለምልክት ሆኑ። የቆሬ ልጆች ግን አልሞቱም። የስምዖን ልጆች በየወገናቸው ከነሙኤል የነሙኤላውያን ወገን፥ ከያሚን የያሚናውያን ወገን፥ ከያኪን የያኪናውያን ወገን፥ ከዛራ የዛራውያን ወገን፥ ከሳኡል የሳኡላውያን ወገን። እነዚህ የስምዖናውያን ወገኖች ናቸው፤ ሀያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። የጋድ ልጆች በየወገናቸው፤ ከጽፎን የጽፎናውያን ወገን፥ ከሐጊ የሐጋውያን ወገን፥ ከሹኒ የሹናውያን ወገን፥ ከኤስናን የኤስናናውያን ወገን፥ ከዔሪ የዔራውያን ወገን፥ ከአሮድ የአሮዳውያን ወገን፥ ከአርኤሊ የአርኤላውያን ወገን። እነዚህ የጋድ ልጆች ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት አርባ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። የይሁዳ ልጆች ዔርና አውናን፤ ዔርና አውናንም በከነዓን ምድር ሞቱ። የይሁዳም ልጆች በየወገናቸው፤ ከሴሎም የሴሎማውያን ወገን፥ ከፋሬስ የፋሬሳውያን ወገን፥ ከዛራ የዛራውያን ወገን። የፋሬስም ልጆች፤ ከኤስሮም የኤስሮማውያን ወገን፥ ከሐሙል የሐሙላውያን ወገን። እነዚህ የይሁዳ ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት ሰባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። የይሳኮር ልጆች በየወገናቸው፤ ከቶላ የቶላውያን ወገን፥ ከፉዋ የፉዋውያን ወገን፥ ከያሱብ የያሱባውያን ወገን፥ ከሺምሮን የሺምሮናውያን ወገን። እነዚህ የይሳኮር ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት ስድሳ አራት ሺህ ሦስት መቶ ነበሩ። የዛብሎን ወገኖች በየወገናቸው፤ ከሴሬድ የሴሬዳውያን ወገን፥ ከኤሎን የኤሎናውያን ወገን፥ ከያሕልኤል የያሕልኤላውያን ወገን። እነዚህ የዛብሎናውያን ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት ስድሳ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። የዮሴፍ ልጆች በየወገናቸው፤ ምናሴና ኤፍሬም። የምናሴ ልጆች፤ ከማኪር የማኪራውያን ወገን፤ ማኪርም ገለዓድን ወለደ፤ ከገለዓድ የገለዓዳውያን ወገን። የገለዓድ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከኢዔዝር የኢዔዝራውያን ወገን፥ ከኬሌግ የኬሌጋውያን ወገን፥ ከአሥሪኤል የአሥሪኤላውያን ወገን፥ ከሴኬም የሴኬማውያን ወገን፥ ከሸሚዳ የሸሚዳውያን ወገን፥ ከኦፌር የኦፌራውያን ወገን። የኦፌርም ልጅ ሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ የሰለጰዓድም የሴቶች ልጆቹ ስም ማህለህ፥ ኑዓ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ቲርጻ ነበረ። እነዚህ የምናሴ ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት አምሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። በየወገናቸው የኤፍሬም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከሱቱላ የሱቱላውያን ወገን፥ ከቤኬር የቤኬራውያን ወገን፥ ከታሐን የታሐናውያን ወገን። እነዚህ የሱቱላ ልጆች ናቸው፤ ከዔዴን የዔዴናውያን ወገን። እነዚህ የኤፍሬም ልጆች ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት ሠላሳ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። በየወገናቸው የዮሴፍ ልጆች እነዚህ ናቸው። የብንያም ልጆች በየወገናቸው፤ ከቤላ የቤላውያን ወገን፥ ከአስቤል የአስቤላውያን ወገን፥ ከአኪራን የአኪራናውያን ወገን፥ ከሶፋን የሶፋናውያን ወገን፥ ከሑፋም የሑፋማውያን ወገን። የቤላም ልጆች፤ አርድና ናዕማን፤ ከአርድ የአርዳውያን ወገን፥ ከናዕማን የናዕማናውያን ወገን። በየወገናቸው የብንያም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት አርባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ። በየወገናቸው የዳን ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከሰምዔ የሰምዔያውያን ወገን፤ በየወገናቸው የዳን ወገኖች እነዚህ ናቸው። የሰምዔያውያን ወገኖች ሁሉ ከእነርሱ እንደ ተቈጠሩ ስድሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። የአሴር ልጆች በየወገናቸው፤ ከዪምና የዪምናውያን ወገን፥ ከየሱዋ የየሱዋውያን ወገን፥ ከበሪዓ የበሪዓውያን ወገን። ከበሪዓ ልጆች፤ ከሔቤር የሔቤራውያን ወገን፥ ከመልኪኤል የመልኪኤላውያን ወገን። የአሴርም የሴት ልጁ ስም ሤራሕ ነበረ። እነዚህ የአሴር ልጆች ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት አምሳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። የንፍታሌም ልጆች በየወገናቸው፤ ከያሕጽኤል የያሕጽኤላውያን ወገን፥ ከጉኒ የጉናውያን ወገን፥ ከዬጽር የዬጽራውያን ወገን፥ ከሺሌም የሺሌማውያን ወገን። በየወገናቸው የንፍታሌም ወገኖች እነዚህ ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት አርባ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። ከእስራኤል ልጆች የተቈጠሩት እነዚህ ናቸው፤ ስድስት መቶ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ።

ዘኍል 26:1-51 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

መቅሠፍቱ ከቆመ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴንና የካህኑን የአሮንን ልጅ አልዓዛርን እንዲህ አላቸው፤ “በመላው የእስራኤል ማኅበር በየቤተሰቡ ዕድሜአቸው ኻያ ዓመት የሞላቸውንና ከዚያም በላይ የሆኑትን፥ ወታደር ሆነው ለማገልገል ብቃት ያላቸውን ወንዶች ልጆች ሁሉ ቊጠሩ።” ሙሴና ካህኑ አልዓዛር በዮርዳኖስ አጠገብ ከኢያሪኮ ትይዩ ባለው የሞአብ ሜዳ ሕዝቡን ሰብስበው እንዲህ አሉአቸው፦ “እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ኻያና ከኻያ ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸውን ሰዎች ሁሉ ቈጠሩ።” ከግብጽ ምድር የወጡትም እስራኤላውያን እነዚህ ነበሩ፦ የያዕቆብ የበኲር ልጅ የሮቤል ነገድ ተወላጆች ሐኖክ፥ ፋሉስ፥ ሔጽሮን፥ ከርሚና የእነርሱ ተወላጆች ናቸው። ከሮቤል ነገድ የጐሣ መሪዎች የተቈጠሩት ጠቅላላ ቊጥር አርባ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበር፤ የፋሉ ዘሮችም ኤሊአብና የኤሊአብ ልጆች ነሙኤል፥ ዳታንና አቤሮን ነበሩ፤ ዳታንና አቤሮንም በማኅበሩ ተመርጠው የነበሩት ሲሆኑ እነርሱም ከቆሬና ከተከታዮቹ ጋር ተባብረው በእግዚአብሔር ላይ ባመፁ ጊዜ ሙሴንና አሮንን የተፈታተኑአቸው ናቸው። እነርሱንም ምድር ተከፍታ ከቆሬ ጋር ዋጠቻቸው፤ እነርሱም በሞቱ ጊዜ እሳት ወርዶ ሁለት መቶ ኀምሳውን ሰዎች አቃጠላቸው፤ ለሕዝቡም መቀጣጫ ሆኑ። የቆሬ ልጆች ግን አልሞቱም። የስምዖን ነገድ ተወላጆች፦ ነሙኤል፥ ያሚንና፥ ያኪን፥ ዛራ፥ ሳኡልና የእነርሱ ተወላጆች ናቸው። ከስምዖን ነገድ የጐሣ መሪዎች የተቈጠሩት ኻያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። የጋድ ነገድ ተወላጆች ጽፎን፥ ሐጊ፥ ሹኒ፥ ኤስናን፥ ዔሪ፥ አሮድ አርኤሊና ተወላጆቻቸው ናቸው። ከጋድ ወገኖች የተቈጠሩት ጠቅላላ ቊጥር አርባ ሺህ አምስት መቶ ነበር። የይሁዳ ነገድ ተወላጆች፥ ኤርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ። የቀሩት የይሁዳ ልጆች ሴሎም ፋሬስ ዛራና ተወላጆቻቸው ናቸው። የፋሬስም ልጆች፥ ኤስሮም፥ ሐሙልና ተወላጆቻቸው ናቸው። ከይሁዳ ነገድ የጐሣ መሪዎች የተቈጠሩት ሰባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። የይሳኮር ነገድ ተወላጆች ቶላ፥ ፉዋ፥ ያሱብ፥ ሺምሮንና ተወላጆቻቸው ናቸው። ከይሳኮር ነገድ የጐሣ መሪዎች የተቈጠሩት ሥልሳ አራት ሺህ ሦስት መቶ ነበሩ። የዛብሎን ነገድ ተወላጆች ሴሬድ፥ ኤሎን ያሕይኤልና ተወላጆቻቸው ናቸው፥ ከዛብሎን ነገድ የጐሣ መሪዎች የተቈጠሩት ሥልሳ ሺህ አምስት መቶ ነበር። የዮሴፍ ልጆች በየወገናቸው፥ ምናሴና ኤፍሬም፥ የምናሴ ነገድ ተወላጆች ማኪር ገለዓድን ወለደ፤ የገለዓድ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ኢኤዝር፥ ሔሌቅ፥ አስሪኤል፥ ሴኬም። ሸሚዳ፥ ኦፌር፥ የሔፌር ልጅ ጸሎፍሐድ ከሴቶች በቀር ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ እነርሱም ማሕላ፥ ኖዓ፥ ሖግላ፥ ሚልካ እና ቲርጻ ተብለው የሚጠሩ ነበሩ፤ ከምናሴ ነገድ የጐሣ መሪዎች የተቈጠሩ ኀምሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። የኤፍሬም ነገድ ተወላጆች ሱቱላ፥ ቤኬር፥ ታሖን፥ የሱቱላ ልጅ፦ ዔራንና የእነርሱ ተወላጆች ናቸው። እነዚህ የኤፍሬም ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት ሠላሳ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። በየወገናቸው የዮሴፍ ተወላጆች እነዚህ ናቸው። የብንያም ነገድ በየትውልዳቸው ቤላ፥ አሽቤል፥ አሒራም። ሹፋም፥ ሑፋም፥ የቤላም ልጆች አርድና ናዕማን ናቸው። ከናዕማናውያን ወገን ናዕማን፥ የብንያም ነገድ ተወላጆች እነዚህ ናቸው። ከእነርሱም የተቈጠሩት አርባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ። የዳን ነገድ ተወላጆች ሰሜዔና፤ ተወላጆቹ፥ የሰምዔያውያን ወገኖች ሁሉ ከእነርሱ እንደ ተቈጠሩ ሥልሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። የአሴር ነገድ ተወላጆች ዪምና፥ የሱዋ፥ በሪዓ። ከበሪዓ ልጆች፦ ሔቤር፥ መልኪኤል፥ አሴርም ሤራሕ የምትባል ሴት ልጅ ነበረችው፤ እነዚህ የአሴር ተወላጆች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት ኀምሳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነበር። የንፍታሌም ነገድ ተወላጆች ያሕጼል፥ ጉኒ ዬጽር፥ ሺሌምና የእነርሱ ተወላጆች ናቸው። የንፍታሌም ነገድ በየወገናቸው እነዚህ ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት አርባ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። በዚህም ዐይነት ከእስራኤላውያን የተቈጠሩት ስድስት መቶ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ።

ዘኍል 26:1-51 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

እንዲህም ሆነ፤ መቅሠፍቱ ከሆነ በኋላ ጌታ ሙሴንና የካህኑን የአሮን ልጅ አልዓዛርን እንዲህ አላቸው፦ “ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለውን፥ በእስራኤል ወደ ጦርነት የሚወጣውን ሁሉ፥ የእስራኤልን ልጆች ማኅበር ሁሉ በየአባቶቻቸው ቤት ቁጠሩ።” ሙሴና ካህኑ አልዓዛር በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ላይ እንዲህ ብለው ተናገሩአቸው፦ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው “ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለውን ሕዝብ ቁጠሩ።” ከግብጽም ምድር የወጡት የእስራኤል ልጆች እነዚህ ነበሩ፦ የእስራኤል በኩር ሮቤል፤ የሮቤልም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከሄኖኅ የሄኖኀውያን ወገን፥ ከፈሉስ የፈሉሳውያን ወገን፥ ከአስሮን የአስሮናውያን ወገን፥ ከከርሚ የከርማውያን ወገን። እነዚህ የሮቤላውያን ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት አርባ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ። የፈሉስም ልጆች፤ ኤልያብ። የኤልያብም ልጆች፤ ነሙኤል፥ ዳታን፥ አቤሮን ናቸው፤ እነዚህ ዳታንና አቤሮን ከማኅበሩ የተመረጡ ነበሩ፤ ቆሬን ከተከተሉት ሰዎች ጋር በመሆን በጌታ ላይ ባመፁ ጊዜ ሙሴንና አሮንን የተገዳደሩ ነበሩ፤ ያም ወገን በሞተ ጊዜ፥ እሳቲቱም ሁለት መቶ ኀምሳውን ሰዎች ባቃጠለች ጊዜ ምድሪቱ አፍዋን ከፍታ እነርሱን ከቆሬ ጋር ዋጠቻቸው፤ እነርሱም ለምልክት ሆኑ። የቆሬ ልጆች ግን አልሞቱም። በየወገናቸው የስምዖን ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከነሙኤል የነሙኤላውያን ወገን፥ ከያሚን የያሚናውያን ወገን፥ ከያኪን የያኪናውያን ወገን፥ ከዛራ የዛራውያን ወገን፥ ከሳኡል የሳኡላውያን ወገን። እነዚህ የስምዖናውያን ወገኖች ናቸው፤ ሀያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። በየወገናቸው የጋድ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከጽፎን የጽፎናውያን ወገን፥ ከሐጊ የሐጋውያን ወገን፥ ከሹኒ የሹናውያን ወገን፥ ከኤስናን የኤስናናውያን ወገን፥ ከዔሪ የዔራውያን ወገን፥ ከአሮድ የአሮዳውያን ወገን፥ ከአርኤሊ የአርኤላውያን ወገን። እነዚህ የጋድ ልጆች ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት አርባ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። የይሁዳ ልጆች ዔርና አውናን ናቸው፤ ዔርና አውናንም በከነዓን ምድር ሞቱ። በየወገናቸው የይሁዳም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከሴሎም የሴሎማውያን ወገን፥ ከፋሬስ የፋሬሳውያን ወገን፥ ከዛራ የዛራውያን ወገን። የፋሬስም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከኤስሮም የኤስሮማውያን ወገን፥ ከሐሙል የሐሙላውያን ወገን። እነዚህ የይሁዳ ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት ሰባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። በየወገናቸው የይሳኮር ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከቶላ የቶላውያን ወገን፥ ከፉዋ የፉዋውያን ወገን፥ ከያሱብ የያሱባውያን ወገን፥ ከሺምሮን የሺምሮናውያን ወገን። እነዚህ የይሳኮር ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት ስልሳ አራት ሺህ ሦስት መቶ ነበሩ። በየወገናቸው የዛብሎን ወገኖች እነዚህ ናቸው፤ ከሴሬድ የሴሬዳውያን ወገን፥ ከኤሎን የኤሎናውያን ወገን፥ ከያሕልኤል የያሕልኤላውያን ወገን። እነዚህ የዛብሎናውያን ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት ስልሳ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። በየወገናቸው የዮሴፍ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ምናሴና ኤፍሬም። የምናሴ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከማኪር የማኪራውያን ወገን፤ ማኪርም ገለዓድን ወለደ፤ ከገለዓድ የገለዓዳውያን ወገን። የገለዓድ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከኢዔዝር የኢዔዝራውያን ወገን፥ ከኬሌግ የኬሌጋውያን ወገን፥ ከአሥሪኤል የአሥሪኤላውያን ወገን፥ ከሴኬም የሴኬማውያን ወገን፥ ከሸሚዳ የሸሚዳውያን ወገን፥ ከኦፌር የኦፌራውያን ወገን። የኦፌርም ልጅ ሰለጰአድ ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ የሰለጰዓድም የሴቶች ልጆቹ ስም ማህለህ፥ ኑዓ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ቲርጻ ነበረ። እነዚህ የምናሴ ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት ኀምሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። በየወገናቸው የኤፍሬም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከሱቱላ የሱቱላውያን ወገን፥ ከቤኬር የቤኬራውያን ወገን፥ ከታሐን የታሐናውያን ወገን። እነዚህ የሱቱላ ልጆች ናቸው፤ ከዔዴን የዔዴናውያን ወገን። እነዚህ የኤፍሬም ልጆች ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት ሠላሳ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። በየወገናቸው የዮሴፍ ልጆች እነዚህ ናቸው። በየወገናቸው የብንያም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከቤላ የቤላውያን ወገን፥ ከአስቤል የአስቤላውያን ወገን፥ ከአኪራን የአኪራናውያን ወገን፥ ከሶፋን የሶፋናውያን ወገን፥ ከሑፋም የሑፋማውያን ወገን። እነዚህ የቤላም ልጆች ናቸው፤ አርድና ናዕማን፤ ከአርድ የአርዳውያን ወገን፥ ከናዕማን የናዕማናውያን ወገን። በየወገናቸው የብንያም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት አርባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ። በየወገናቸው የዳን ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከሰምዔ የሰምዔያውያን ወገን፤ በየወገናቸው የዳን ወገኖች እነዚህ ናቸው። የሰምዔያውያን ወገኖች ሁሉ ከእነርሱ የተቈጠሩት ስልሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። በየወገናቸው የአሴር ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከዪምና የዪምናውያን ወገን፥ ከየሱዋ የየሱዋውያን ወገን፥ ከበሪዓ የበሪዓውያን ወገን። እነዚህ ከበሪዓ ልጆች ናቸው፤ ከሔቤር የሔቤራውያን ወገን፥ ከመልኪኤል የመልኪኤላውያን ወገን። የአሴርም የሴት ልጁ ስም ሤራሕ ነበረ። እነዚህ የአሴር ልጆች ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት ኀምሳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። በየወገናቸው የንፍታሌም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከያሕጽኤል የያሕጽኤላውያን ወገን፥ ከጉኒ የጉናውያን ወገን፥ ከዬጽር የዬጽራውያን ወገን፥ ከሺሌም የሺሌማውያን ወገን። በየወገናቸው የንፍታሌም ወገኖች እነዚህ ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት አርባ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። ከእስራኤል ልጆች የተቈጠሩት እነዚህ ናቸው፤ እነርሱም ስድስት መቶ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ።