የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘኍል 20:2-12

ዘኍል 20:2-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ለማ​ኅ​በ​ሩም ውኃ አል​ነ​በ​ረም፤ ሕዝ​ቡም በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ ተሰ​በ​ሰቡ። ሙሴ​ንም ተጣ​ሉት፤ እን​ዲ​ህም ብለው ተና​ገ​ሩት፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ምነው በሞ​ትን ኖሮ፤ እኛ፥ ከብ​ቶ​ቻ​ች​ንም በዚያ እን​ሞት ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማኅ​በር ወደ​ዚህ ምድረ በዳ ለምን አወ​ጣ​ችሁ? ዘር ወደ​ማ​ይ​ዘ​ራ​በት፥ በለ​ስና ወይ​ንም፥ ሮማ​ንም፥ የሚ​ጠ​ጣም ውኃ ወደ​ሌ​ለ​በት ወደ​ዚህ ክፉ ስፍራ ታመ​ጡን ዘንድ ከግ​ብፅ ለምን አወ​ጣ​ች​ሁን?” ሙሴና አሮ​ንም ከማ​ኅ​በሩ ፊት ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ዳጃፍ ሄደው በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ወደቁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ተገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ “ይህ​ችን በት​ር​ህን ውሰድ፤ አን​ተና ወን​ድ​ምህ አሮ​ንም ማኅ​በ​ሩን ሰብ​ስቡ፤ ዐለ​ቷ​ንም በፊ​ታ​ቸው እዘ​ዟት፤ ውኃ ትሰ​ጣ​ለች፤ ከድ​ን​ጋ​ይ​ዋም ውኃ ታወ​ጡ​ላ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤ እን​ዲ​ሁም ማኅ​በ​ሩን፥ ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ታጠ​ጡ​ላ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።” ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አዘ​ዘው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የነ​በ​ረ​ች​ውን በት​ሩን ወሰደ። ሙሴና አሮ​ንም ማኅ​በ​ሩን በዐ​ለቷ ፊት ሰብ​ስ​በው፥ “እና​ንተ ዓመ​ፀ​ኞች፥ እን​ግ​ዲህ ስሙ፤ በውኑ ከዚ​ህች ዐለት ውኃን እና​ወ​ጣ​ላ​ችሁ ነበር?” አሏ​ቸው። ሙሴም እጁን ዘር​ግቶ ዐለ​ቷን ሁለት ጊዜ በበ​ትሩ መታት፤ ብዙም ውኃ ወጣ፤ ማኅ​በ​ሩም፥ ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ጠጡ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ትቀ​ድ​ሱኝ ዘንድ በእኔ አላ​መ​ና​ች​ሁ​ምና ስለ​ዚህ ወደ ሰጠ​ኋ​ችሁ ምድር ይህን ማኅ​በር ይዛ​ችሁ አት​ገ​ቡም” አላ​ቸው።

ዘኍል 20:2-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በዚህ ጊዜ ለማኅበረ ሰቡ የሚሆን ውሃ አልነበረም፤ ሕዝቡም ሙሴንና አሮንን በመቃወም ተሰበሰቡ። ሙሴን ተጣሉት፤ እንዲህም አሉት፤ “ወንድሞቻችን በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት በሞቱ ጊዜ ምነው እኛም ያኔ ሞተን ባረፍነው ኖሮ! የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ማኅበረ ሰብ ወደዚህ ምድረ በዳ ያመጣችሁት ለምንድን ነው! ከነከብቶቻችን እዚሁ እንድናልቅ ነውን? ከግብፅ አውጥታችሁ እህል ወይም በለስ፣ ወይን ወይም ሮማን ወደሌለበት ወደዚህ ክፉ ቦታ ያመጣችሁንስ ለምንድን ነው? የሚጠጣ ውሃ እንኳ ይታጣ!” ሙሴና አሮን ከማኅበረ ሰቡ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሄደው በግንባራቸው ተደፉ፤ የእግዚአብሔርም (ያህዌ) ክብር ተገለጠላቸው። እግዚአብሔርም (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በትሪቱን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮን ማኅበሩን በአንድነት ሰብሰቡ፤ እነርሱም እያዩ ዐለቱን ተናገሩት፤ ዐለቱም ውሃ ያወጣል። አንተም ለማኅበረ ሰቡ ከዐለቱ ውሃ ታወጣላቸዋለህ፤ እነርሱና ከብቶቻቸውም ይጠጣሉ።” ስለዚህም ሙሴ ልክ እንደ ታዘዘው በትሩን ከእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ወሰደ። እርሱና አሮንም ማኅበሩን በዐለቱ ፊት አንድ ላይ ሰበሰቡ፤ ሙሴም፣ “እናንት ዐመፀኞች አድምጡ፤ ከዚህ ዐለት እኛ ለእናንተ ውሃ ማውጣት አለብን?” አላቸው። ከዚያም ሙሴ እጁን ዘርግቶ በበትሩ ዐለቱን ሁለት ጊዜ መታው፤ ውሃውም ተንዶለዶለ፤ ማኅበረ ሰቡና ከብቶቻቸውም ጠጡ። ነገር ግን እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴንና አሮንን፣ “በእስራኤላውያን ፊት እኔን ቅዱስ አድርጋችሁ ለማክበር ስላልታመናችሁብኝ ይህን ማኅበረ ሰብ ወደምሰጠው ምድር ይዛችሁ አትገቡም” አላቸው።

ዘኍል 20:2-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ለማኅበሩም ውኃ አልነበረም፤ በሙሴና በአሮንም ላይ ተሰበሰቡ። ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፥ እንዲህም ብለው ተናገሩት፦ ወንድሞቻችን በእግዚአብሔር ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ምነው በሞትን ኖሮ! እኛ ከብቶቻችንም በዚያ እንሞት ዘንድ የእግዚአብሔርን ጉባኤ ወደዚህ ምድረ በዳ ለምን አመጣችሁ? ወደዚህ ክፉ ስፍራ ታመጡን ዘንድ ከግብፅ ለምን አወጣችሁን? ዘርና በለስ ወይንም ሮማንም የሌለበት ስፍራ ነው፤ የሚጠጣም ውኃ የለበትም። ሙሴና አሮንም ከጉባኤው ፊት ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሂደው በግምባራቸው ወደቁ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ተገለጠላቸው። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ በትርህን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮን ማኅበሩን ሰብስቡ፥ ድንጋዩም ውኃን እንዲሰጥ እነርሱ ሲያዩ ተናገሩት፤ ከድንጋዩም ውኃ ታወጣላቸዋለህ፤ እንዲሁም ማኅበሩን ከብቶቻቸውንም ታጠጣላቸዋለህ። ሙሴም እንደ ታዘዘ በትሩን ከእግዚአብሔር ፊት ወሰደ። ሙሴና አሮንም ጉባኤውን በድንጋዩ ፊት ሰብስበው፦ እናንተ ዓመፀኞች፥ እንግዲህ ስሙ፤ በውኑ ከዚህ ድንጋይ ውኃን እናወጣላችኋለን? አላቸው። ሙሴም እጁን ዘርግቶ ድንጋዩን ሁለት ጊዜ በበትሩ መታው፤ ብዙም ውኃ ወጣ፥ ማኅበሩም ከብቶቻቸውም ጠጡ። እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን፦ በእስራኤል ልጆች ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ በእኔ አላመናችሁምና ስለዚህ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ይህን ጉባኤ ይዛችሁ አትገቡም አላቸው።

ዘኍል 20:2-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በሰፈሩበት ቦታ ውሃ አልነበረም፤ ስለዚህ ሕዝቡ ሙሴንና አሮንን በመቃወም ተሰብስበው፥ እንዲህ በማለት ከሙሴ ጋር ተጣሉ፦ “በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ለፊት ከቀሩት እስራኤላውያን ወገኖቻችን ጋር ሞተን ቢሆን መልካም በሆነ ነበር። የእግዚአብሔርን ማኅበር ወደዚህ ምድረ በዳ ያመጣችሁት እኛና እንስሶቻችን እዚህ እንድናልቅ ለማድረግ ነውን? ከግብጽ አውጥታችሁ ምንም ነገር ወደማይበቅልበት ወደዚህ አስከፊ ምድር ለምን አመጣችሁን? በዚህ ስፍራ እህል፥ በለስ፥ ወይንና ሮማን አይገኝም፤ ሌላው ቀርቶ የሚጠጣ ውሃ እንኳ የለም!” ሙሴና አሮን ከሕዝቡ ፈቅ ብለው ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሄዱ፤ በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፍተው ሳሉም የእግዚአብሔር ክብር ተገለጠላቸው። እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ያለውን በትር ወስደህ አንተና አሮን ሆናችሁ መላውን ማኅበር በአንድነት ሰብስቡ፤ እዚያም በእነርሱ ሁሉ ፊት ሆነህ ያንን አለት ውሃውን እንዲያወጣ እዘዘው፤ በዚህ ዐይነት ከአለቱ ውስጥ ውሃ ታወጣላቸዋለህ፤ እንዲሁም እነርሱና እንስሶቻቸውም ጠጥተው ይረካሉ።” ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ከድንኳኑ ውስጥ በትሩን አመጣ። እርሱና አሮን መላውን ማኅበር በአለቱ ፊት ለፊት እንዲሰበሰቡ ካደረጉ በኋላ ሙሴ ሕዝቡን “እናንተ ዐመፀኞች! ከዚህ አለት ለእናንተ ውሃ እናውጣላችሁን?” አላቸው። ከዚህ በኋላ ሙሴ በትሩን አንሥቶ አለቱን ሁለት ጊዜ መታው፤ ታላቅ የውሃ ምንጭም ከውስጡ ፈሰሰ፤ ሕዝቡና እንስሶቹም ሁሉ ጠጡ። ነገር ግን እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ ሲል ገሠጻቸው፤ “በእስራኤላውያን ፊት የተቀደሰ ክብሬን ትገልጡ ዘንድ ስላላመናችሁብኝ፥ ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር የዚህ ሕዝብ መሪዎች ሆናችሁ አትገቡም።”

ዘኍል 20:2-12 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ለማኅበሩም ውኃ አልነበረም፤ እነርሱም በሙሴና በአሮን ላይ ተሰበሰቡ። ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፥ እንዲህም ብለው ተናገሩት፦ “ወንድሞቻችን በጌታ ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ምነው በሞትን ኖሮ! እኛም ከብቶቻችንም በዚህ እንድንሞት የጌታን ጉባኤ ወደዚህ ምድረ በዳ ለምን አመጣችሁ? ወደዚህ ክፉ ስፍራ ልታመጡን ከግብጽ ለምን አወጣችሁን? ለዘርና ለበለስ ለወይንም ለሮማንም የማይሆን ስፍራ ነው፤ የሚጠጣም ውኃ የለበትም።” ሙሴና አሮንም ከጉባኤው ፊት ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሂደው በግምባራቸው ወድቀው ሰገዱ፤ የጌታም ክብር ተገለጠላቸው። ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “በትሩን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮን ማኅበሩን ሰብስቡ፥ እነርሱም ዓይናቸው እያየ ድንጋዩ ውኃን እንዲሰጥ ተናገሩት፤ ለእነርሱም ከድንጋዩ ውኃ ታወጣላቸዋለህ፤ እንዲሁም ለማኅበሩና ለከብቶቻቸው የሚጠጣ ወኃ ትሰጣቸዋለህ።” ሙሴም እንደ ታዘዘ በትሩን ከጌታ ፊት ወሰደ። ሙሴና አሮንም ጉባኤውን በድንጋዩ ፊት ሰበሰቡአቸው ሙሴም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ዓመፀኞች፥ እንግዲህ ስሙ፤ በውኑ ከዚህ ድንጋይ ውኃን እናውጣላችሁን?” ሙሴም እጁን ዘርግቶ ድንጋዩን ሁለት ጊዜ በበትሩ መታው፤ ብዙም ውኃ ወጣ፥ ማኅበሩም ከብቶቻቸውም ጠጡ። ጌታም ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ “በእስራኤል ልጆች ፊት ቅድስናዬን ለማሳየት በእኔ አላመናችሁምና ስለዚህ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ይህን ጉባኤ ይዛችሁ አትገቡም።”