ዘኍል 20:10-11
ዘኍል 20:10-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እርሱና አሮንም ማኅበሩን በዐለቱ ፊት አንድ ላይ ሰበሰቡ፤ ሙሴም፣ “እናንት ዐመፀኞች አድምጡ፤ ከዚህ ዐለት እኛ ለእናንተ ውሃ ማውጣት አለብን?” አላቸው። ከዚያም ሙሴ እጁን ዘርግቶ በበትሩ ዐለቱን ሁለት ጊዜ መታው፤ ውሃውም ተንዶለዶለ፤ ማኅበረ ሰቡና ከብቶቻቸውም ጠጡ።
Share
ዘኍል 20 ያንብቡዘኍል 20:10-11 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ሙሴና አሮንም ጉባኤውን በድንጋዩ ፊት ሰብስበው፦ እናንተ ዓመፀኞች፥ እንግዲህ ስሙ፤ በውኑ ከዚህ ድንጋይ ውኃን እናወጣላችኋለን? አላቸው። ሙሴም እጁን ዘርግቶ ድንጋዩን ሁለት ጊዜ በበትሩ መታው፤ ብዙም ውኃ ወጣ፥ ማኅበሩም ከብቶቻቸውም ጠጡ።
Share
ዘኍል 20 ያንብቡዘኍል 20:10-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሙሴና አሮንም ማኅበሩን በዐለቷ ፊት ሰብስበው፥ “እናንተ ዓመፀኞች፥ እንግዲህ ስሙ፤ በውኑ ከዚህች ዐለት ውኃን እናወጣላችሁ ነበር?” አሏቸው። ሙሴም እጁን ዘርግቶ ዐለቷን ሁለት ጊዜ በበትሩ መታት፤ ብዙም ውኃ ወጣ፤ ማኅበሩም፥ ከብቶቻቸውም ጠጡ።
Share
ዘኍል 20 ያንብቡ