ዘኍልቍ 14:6-10
ዘኍልቍ 14:6-10 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ምድሪቱን ከሰለሏት መካከል የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዮፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ለመላው የእስራኤል ማኅበርም እንዲህ አሉ፤ “ዞረን ያየናትና የሰለልናት ምድር እጅግ ሲበዛ መልካም ናት። እግዚአብሔር በእኛ ደስ ከተሠኘብን ማርና ወተት ወደምታፈሰው ወደዚያች ምድር መርቶ ያገባናል፤ ለእኛም ይሰጠናል። ብቻ በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ እንጐርሳቸዋለንና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሯቸው። ጥላቸው ተገፍፏል፤ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋራ ነውና አትፍሯቸው።” መላው ማኅበር ግን በድንጋይ ሊወግሯቸው ተነጋገሩ፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ክብር በመገናኛው ድንኳን ለእስራኤላውያን ሁሉ ተገለጠ።
ዘኍልቍ 14:6-10 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ምድሪቱን ከሰለሉት ጋር የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዮፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ለእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ “የሰለልናት ምድር እጅግ በጣም መልካም ናት። እግዚአብሔርስ ከመረጠን ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ወደዚች ምድር ያገባናል፤ እርስዋንም ይሰጠናል። ነገር ግን እናንተ በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እኛ እናጠፋቸዋለንና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጊዜአቸው አልፎባቸዋል፤ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው” ብለው ተናገሩአቸው። ማኅበሩ ሁሉ ግን “በድንጋይ እንውገራቸው” አሉ። የእግዚአብሔርም ክብር ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በምስክሩ ድንኳን ተገለጠ።
ዘኍልቍ 14:6-10 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ምድሪቱን ከሰለሏት መካከል የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዮፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ለመላው የእስራኤል ማኅበርም እንዲህ አሉ፤ “ዞረን ያየናትና የሰለልናት ምድር እጅግ ሲበዛ መልካም ናት። እግዚአብሔር በእኛ ደስ ከተሠኘብን ማርና ወተት ወደምታፈሰው ወደዚያች ምድር መርቶ ያገባናል፤ ለእኛም ይሰጠናል። ብቻ በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ እንጐርሳቸዋለንና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሯቸው። ጥላቸው ተገፍፏል፤ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋራ ነውና አትፍሯቸው።” መላው ማኅበር ግን በድንጋይ ሊወግሯቸው ተነጋገሩ፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ክብር በመገናኛው ድንኳን ለእስራኤላውያን ሁሉ ተገለጠ።
ዘኍልቍ 14:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ምድርን ከሰለሉት ጋር የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዮፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ለእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ፦ ዞረን የሰለልናት ምድር እጅግ መልካም ናት። እግዚአብሔርስ ከወደደን ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ወደዚች ምድር ያገባናል እርስዋንም ይሰጠናል። ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ ይሆኑልናልና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፥ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው ብለው ተናገሩአቸው። ማኅበሩ ሁሉ ግን በድንጋይ ይወግሩአቸው ዘንድ ተማከሩ። የእግዚአብሔርም ክብር ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ተገለጠ።
ዘኍልቍ 14:6-10 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ምድሪቱን እንዲያጠኑ ከተላኩት ሰዎች ሁለቱ የነዌ ልጅ ኢያሱና የየፉኔ ልጅ ካሌብ በሐዘን ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ለሕዝቡም እንዲህ አሉ፦ “መርምረን ያጠናናት ምድር እጅግ ውብ የሆነች ምድር ናት፤ እግዚአብሔር በእኛ ደስ የሚለው ቢሆን ወደዚያ ይወስደናል፤ በማርና በወተት የበለጸገችውን ያቺን ለም ምድር ይሰጠናል፤ ስለዚህ በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እዚያም የሚኖሩትን ሕዝቦች አትፍሩአቸው፤ እኛ በቀላሉ በጦርነት ድል እንነሣቸዋለን፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፎአል፤ ስለዚህ ፈጽሞ አትፍሩአቸው።” መላውም ማኅበር በድንጋይ ወግሮ ሊገድላቸው በእነርሱ ላይ ተነሣሣ፤ ነገር ግን በመገናኛው ድንኳን የእግዚአብሔር ክብር ለእስራኤላውያን ሁሉ ተገለጠ።
ዘኍልቍ 14:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ምድርን ከሰለሉት ጋር የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዮፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ለእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲህ ብለው ተናገሩ፦ “ዞረን የሰለልናት ምድር እጅግ መልካም የሆነች ናት። ጌታስ በእኛ ደስ የሚሰኝ ቢሆን ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ወደዚች ምድር ያገባናል እርሷንም ይሰጠናል። ብቻ፥ በጌታ ላይ አታምፁ፤ ለእኛ እንደ እንጀራ ቁራሽ ናቸውና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፥ ጌታም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው።” ማኅበሩ ሁሉ ግን በድንጋይ ሊወግሯቸው ተማከሩ። የጌታም ክብር ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ተገለጠ።