የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘኍል 14:25-35

ዘኍል 14:25-35 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

አማሌቃውያንና ከነዓናውያን በሸለቆው የሚኖሩ ስለሆነ በነገው ዕለት ተመልሳችሁ በቀይ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳው ሂዱ።” እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ “ይህ ክፉ ማኅበረ ሰብ በእኔ ላይ የሚያጕረመርመው እስከ መቼ ነው? የእነዚህን ነጭናጮች እስራኤላውያን ማጕረምረም ሰምቻለሁ። ስለዚህ እንዲህ በላቸው፤ ‘እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዲህ ይላል፤ እኔ ሕያው ነኝ፤ ስትናገሩ የሰማኋችሁን እነዚያን ነገሮች አደርግባችኋለሁ፤ በተደረገው ቈጠራ መሠረት፣ ሃያ ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆናችሁና በእኔም ላይ ያጕረመረማችሁ ሁሉ በድናችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃል። መኖሪያችሁ እንድትሆን በጽኑ ወደ ማልሁላችሁ ምድር ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በስተቀር ከእናንተ አንዳችሁም አትገቡባትም። ይማረካሉ ያላችኋቸውን ልጆቻችሁን ግን አገባቸዋለሁ፤ እናንተ የናቃችኋትን ምድር እነርሱ ይደሰቱባታል። እናንተ ግን፣ በድናችሁ በዚሁ ምድረ በዳ ወድቆ ይቀራል። ካለማመናችሁ የተነሣ ከእናንተ የመጨረሻው በድን እዚሁ ምድረ በዳ እስኪወድቅ ድረስ፣ ልጆቻችሁ መከራ እየበሉ አርባ ዓመት እረኞች ይሆናሉ። ምድሪቱን ለመሰለል በቈያችሁበት አርባ ቀን ልክ እያንዳንዱ ዓመት እንደ አንድ ዕለት ተቈጥሮ ስለ ኀጢአታችሁ አርባ ዓመት መከራ ትቀበላላችሁ፤ ምን ያህል በእናንተ ላይ እንደ ተነሣሁም ታውቃላችሁ። እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ይህን ተናግሬአለሁ፤ ደግሞም አንድ ሆኖ በተነሣብኝ በዚህ ክፉ ማኅበረ ሰብ ሁሉ ላይ እነዚህን ነገሮች አደርጋለሁ፤ መጨረሻቸው በዚሁ ምድረ በዳ ይሆናል፤ እዚሁም ይሞታሉ።’ ”

ዘኍል 14:25-35 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

አማሌቅና ከነዓናዊውም በሸለቆው ውስጥ ተቀምጦአል፤ በነጋው ተመልሳችሁ በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ። እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ የሚያጕረመርምብኝን ይህን ክፉ ሕዝብ እስከ መቼ እታገሠዋለሁ? በእኔ ላይ የሚያጕረመርሙትን የእስራኤልን ልጆች ማጕረምረም ሰማሁ። እንዲህ በላቸው፦ እኔ ሕያው ነኝና በጆሮዬ እንደ ተናገራችሁት እንዲሁ በእውነት አደርግባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ በድኖቻችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃሉ፤ የተቈጠራችሁ ሁሉ፥ እንደ ቍጥራችሁ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ የሆነ ሁሉ፥ እናንተ ያጕረመረማችሁብኝ፥ ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር በእርስዋ አስቀምጣችሁ ዘንድ እጄን ዘርግቼ ወደ ማልሁላችሁ ምድር በእውነት እናንተ አትገቡም። ምርኮኛ ይሆናሉ ያላችኋቸውን ልጆቻችሁን እነርሱን አገባቸዋለሁ፥ እናንተም የናቃችኋትን ምድር ያውቃሉ። እናንተ ግን በድኖቻችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃሉ። ልጆቻችሁም በምድረ በዳ አርባ ዓመት ይቅበዘበዛሉ፥ በድኖቻችሁም በምድረ በዳ እስኪጠፉ ድረስ ግልሙትናችሁን ይሸከማሉ። ምድሪቱን በሰላለችሁባት ቀን ቍጥር፥ አርባ ቀን፥ ስለ አንድ ቀንም አንድ ዓመት፥ ኃጢአታችሁን አርባ ዓመት ትሸከማላችሁ፥ ቍጣዬንም ታውቃላችሁ። እኔ እግዚአብሔር፦ በእኔ ላይ በተሰበሰበ በዚህ ክፉ ማኅበር ሁሉ ላይ እንዲህ አደርጋለሁ ብዬ ተናገርሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ ያልቃሉ፥ በዚያም ይሞታሉ።

ዘኍል 14:25-35 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

አማሌቃውያንና ከነዓናውያን በሸለቆዎቹ ውስጥ ስለሚኖሩ ነገ ተመልሳችሁ በቀይ ባሕር በኩል በሚወስደው መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ።” እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ “እነዚህ ክፉዎች የሆኑ ሰዎች በእኔ ላይ የሚያጒረመርሙት እስከ መቼ ነው? እነዚህ አጒረምራሚዎች እስራኤላውያን በእኔ ላይ ማጒረምረማቸውን ሰምቻለሁ። እነሆ! ይህን መልስ ስጣቸው፥ ‘በጠየቃችሁት ዐይነት እንደማደርግባችሁ ሕያው በሆነ ስሜ እምላለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ፤ ሁላችሁም ትሞታላችሁ፤ ሬሳችሁም በዚህ ምድረ በዳ ተበትኖ ይቀራል፤ በእኔ ላይ በማጒረምረማችሁ ምክንያት ከእናንተ መካከል ከኻያ ዓመት በላይ ዕድሜ ኖሮአችሁ የተቈጠራችሁት ሁሉ ከቶ ወደዚያች ምድር አትገቡም፤ ወደዚያች ምድር ገብታችሁ እንደምትኖሩ ቃል ገብቼላችሁ ነበር፤ ነገር ግን ከየፉኔ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር ከእናንተ አንዱ እንኳ ወደዚያች ምድር አይገባም። ልጆቻችን ምርኮኞች ሆነው ይቀራሉ ብላችሁ የተናገራችሁባቸውን እነርሱን እናንተ ወደናቃችኋት ምድር አገባቸዋለሁ፤ ርስታቸውም ትሆናለች። የእናንተ በድን ግን በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃል፤ ልጆቻችሁም በእናንተ አለማመን ምክንያት ከእናንተ የመጨረሻው በድን በምድረ በዳ እስኪወድቅ ድረስ አርባ ዓመት ሙሉ ጽኑ መከራ እየተቀበሉ በዚህ ምድረ በዳ ይንከራተታሉ፤ በኃጢአታችሁ ምክንያት አርባ ዓመት ሙሉ ትሠቃያላችሁ፤ ይህም ምድሪቱን ለማጥናት በቈያችሁበት አርባ ቀን ልክ አንዲቱ ዕለት አንድ ዓመት ትሆንባችኋለች፤ በዚያን ጊዜ እኔን መቃወም ምን እንደሚያመጣባችሁ ትገነዘባላችሁ። በእኔ ላይ አድመው በተነሡብኝ በእነዚህ ዐመፀኞች ላይ ይህን ሁሉ አደርግባቸዋለሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ የሁሉም መጨረሻ ይሆናል፤ ሁሉም ይሞታሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።’ ”

ዘኍል 14:25-35 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ዐማ​ሌ​ቅና ከነ​ዓ​ና​ዊ​ውም በሸ​ለቆ ውስጥ ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ እና​ንተ ግን ነገ ተመ​ል​ሳ​ችሁ በኤ​ር​ትራ ባሕር መን​ገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ “የሚ​ያ​ጕ​ረ​መ​ር​ሙ​ብ​ኝን እኒ​ህን ክፉ ማኅ​በር እስከ መቼ እታ​ገ​ሣ​ቸ​ዋ​ለሁ? ስለ እና​ንተ በእኔ ላይ የሚ​ያ​ጕ​ረ​መ​ር​ሙ​ትን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማጕ​ረ​ም​ረ​ምን ሰማሁ። እን​ዲህ በላ​ቸው፦ እኔ ሕያው ነኝና በጆ​ሮዬ እንደ ተና​ገ​ራ​ች​ሁት እን​ዲሁ በእ​ው​ነት አደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። በድ​ኖ​ቻ​ችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወ​ድ​ቃሉ፤ የተ​ቈ​ጠ​ራ​ችሁ ሁሉ፥ እንደ ቍጥ​ራ​ችሁ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ የሆነ ሁሉ፥ እና​ንተ ያጕ​ረ​መ​ረ​ማ​ች​ሁ​ብኝ፥ ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌ​ብና ከነዌ ልጅ ከኢ​ያሱ በቀር በእ​ር​ስዋ አስ​ቀ​ም​ጣ​ችሁ ዘንድ እጄን ዘር​ግቼ ወደ ማል​ሁ​ላ​ችሁ ምድር በእ​ው​ነት እና​ንተ አት​ገ​ቡም። ንጥ​ቂያ ይሆ​ናሉ ያላ​ች​ኋ​ቸ​ውን ልጆ​ቻ​ች​ሁን እነ​ር​ሱን አገ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም የና​ቃ​ች​ኋ​ትን ምድር ይወ​ር​ሷ​ታል። የእ​ና​ንተ ግን በድ​ኖ​ቻ​ችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወ​ድ​ቃሉ። ልጆ​ቻ​ች​ሁም በም​ድረ በዳ አርባ ዓመት ይቅ​በ​ዘ​በ​ዛሉ፤ በድ​ኖ​ቻ​ች​ሁም በም​ድረ በዳ እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ ግል​ሙ​ት​ና​ች​ሁን ይሸ​ከ​ማሉ። ምድ​ሪ​ቱን እንደ ሰለ​ሉ​ባ​ቸው እንደ እነ​ዚያ አርባ ቀኖች ቍጥር ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ ሁሉ አር​ባው ቀን አርባ ዓመት፥ አንዱ ቀንም አንድ ዓመት ይሁ​ን​ባ​ችሁ፤ እን​ግ​ዲህ የቍ​ጣ​ዬን መቅ​ሠ​ፍት ታው​ቃ​ላ​ችሁ። እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በእኔ ላይ በተ​ሰ​በ​ሰበ በዚህ ክፉ ማኅ​በር ሁሉ ላይ እን​ዲህ አደ​ር​ጋ​ለሁ ብዬ ተና​ገ​ርሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ ያል​ቃሉ፤ በዚ​ያም ይሞ​ታሉ።”

ዘኍል 14:25-35 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

አማሌቃውያንና ከነዓናውያን በሸለቆው ውስጥ ስለ ተቀመጡ ነገ ተመልሳችሁ በኤርትራ ባሕር በኩል በሚወስደው መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ።” ጌታም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ “የሚያጉረመርምብኝን ይህን ክፉ ማኅበር እስከ መቼ እታገሠዋለሁ? በእኔ ላይ የሚያጉረመርሙትን የእስራኤልን ልጆች ማጉረምረም ሰምቻለሁ። እንዲህ በላቸው፦ ‘እኔ ሕያው ነኝና በጆሮዬ እንደ ተናገራችሁት እንዲሁ በእውነት አደርግባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ በድኖቻችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃሉ፤ ከአጠቃላይም ቁጥራችሁ፥ በእኔ ላይ ያጉረመረሙ ዕድሜአቸው ሀያ ዓመት የሆናቸውና ከዚያም በላይ ሆነው የተቈጠሩት ሁሉ፥ ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር በእርሷ ላስቀምጣችሁ እጄን ዘርግቼ ወደ ማልሁላችሁ ምድር በእውነት እናንተ አትገቡም። ነገር ግን ምርኮኛ ይሆናሉ ያላችኋቸውን ልጆቻችሁን እነርሱን ወደ ምድሪቱ አስገባቸዋለሁ፥ እናንተም የናቃችኋትን ምድር ያውቋታል። እናንተ ግን በድኖቻችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃሉ። ልጆቻችሁም በምድረ በዳ አርባ ዓመት እረኛች ይሆናሉ፥ በድኖቻችሁም በምድረ በዳ እስኪጠፉ ድረስ ዝሙታችሁን ይሸከማሉ። ምድሪቱን በሰላለችሁባት ቀን ቍጥር፥ አርባ ቀን፥ እያንዳንዱም ቀን እንደ አንድ ዓመት ሆኖ፥ በደላችሁን አርባ ዓመት ትሸከማላችሁ፥ መከፋቴንም ታውቃላችሁ።’ እኔ ጌታ፦ በእኔ ላይ በተሰበሰበ በዚህ ክፉ ማኅበር ሁሉ ላይ በእውነት እንዲህ አደርጋለሁ ብዬ ተናገርሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ ያልቃሉ፥ በዚያም ይሞታሉ።”