ዘኍል 13:1-14
ዘኍል 13:1-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለእስራኤላውያን የምሰጠውን የከነዓንን ምድር እንዲሰልሉ ጥቂት ሰዎች ላክ፤ ከእያንዳንዱም የአባቶች ነገድ አለቃ ይላክ።” ስለዚህ ሙሴ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ትእዛዝ ከፋራን ምድረ በዳ እነዚህን ላካቸው፤ ሁሉም የእስራኤላውያን አለቆች ነበሩ፤ ስማቸውም እንደሚከተለው ነው፤ ከሮቤል ነገድ፣ የዘኩር ልጅ ሳሙኤል፤ ከስምዖን ነገድ፣ የሱሬ ልጅ ሰፈጥ፤ ከይሁዳ ነገድ፣ የዩፎኒ ልጅ ካሌብ፤ ከይሳኮር ነገድ፣ የዮሴፍ ልጅ ይግአል፤ ከኤፍሬም ነገድ፣ የነዌ ልጅ አውሴ፤ ከብንያም ነገድ፣ የራፉ ልጅ ፈልጢ፤ ከዛብሎን ነገድ፣ የሰዲ ልጅ ጉዲኤል፤ ከምናሴ ነገድ ይህም የዮሴፍ ነገድ ነው፤ የሱሲ ልጅ ጋዲ፤ ከዳን ነገድ፣ የገማሊ ልጅ ዓሚኤል፤ ከአሴር ነገድ፣ የሚካኤል ልጅ ሰቱር፤ ከንፍታሌም ነገድ፣ የያቢ ልጅ ናቢ፤
ዘኍል 13:1-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ይገዙአት ዘንድ እኔ ለእስራኤል ልጆች የምሰጣትን የከነዓንን ምድር የሚሰልሉ ሰዎችን ላክ፤ ከአባቶች ቤት ከእያንዳንዱ ነገድ ሁሉ በመካከላቸው አለቃ የሆነ አንድ አንድ ሰው ትልካላችሁ።” ሙሴም እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ከፋራን ምድረ በዳ ላካቸው፤ እነርሱም ሁሉ የእስራኤል ልጆች አለቆች ነበሩ። ስማቸውም ይህ ነበረ፤ ከሮቤል ነገድ የዝኩር ልጅ ሰሙኤል፤ ከስምዖን ነገድ የሱሬ ልጅ ሰፈጥ ፤ ከይሁዳ ነገድ የዮፎኒ ልጅ ካሌብ፤ ከይሳኮር ነገድ የዮሴፍ ልጅ ኢጋል፤ ከኤፍሬም ነገድ የነዌ ልጅ አውሴ፤ ከብንያም ነገድ የራፋ ልጅ ፈልጢ፤ ከዛብሎን ነገድ የሶዲ ልጅ ጉዲኤል፤ ከዮሴፍ ነገድ ከምናሴ ልጆች የሱሲ ልጅ ጋዲ፤ ከዳን ነገድ የገማሊ ልጅ ዓሚሄል፤ ከአሴር ነገድ የሚካኤል ልጅ ሳቱር፤ ከንፍታሌም ነገድ የያቢ ልጅ ናቢ፤
ዘኍል 13:1-14 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ ለእስራኤል ልጆች የምሰጣትን የከንዓንን ምድር ይሰልሉ ዘንድ ሰዎችን ላክ፤ ከአባቶች ነገድ ሁሉ እያንዳንዱ በመካከላቸው አለቃ የሆነ አንድ ሰው ትልካላችሁ። ሙሴም እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ከፋራን ምድረ በዳ ላካቸው፤ እነርሱም ሁሉ የእስራኤል ልጆች አለቆች ነበሩ። ስማቸውም ይህ ነበረ፤ ከሮቤል ነገድ የዘኩር ልጅ ሰሙኤል፤ ከስምዖን ነገድ የሱሬ ልጅ ሰፈጥ፤ ከይሁዳ ነገድ የዮፎኒ ልጅ ካሌብ፤ ከይሳኮር ነገድ የዮሴፍ ልጅ ይግአል፤ ከኤፍሬም ነገድ የነዌ ልጅ አውሴ፤ ከብንያም ነገድ የራፉ ልጅ ፈልጢ፤ ከዛብሎን ነገድ የሰዲ ልጅ ጉዲኤል፤ ከዮሴፍ ነገድ እርሱም የምናሴ ነገድ የሱሲ ልጅ ጋዲ፤ ከዳን ነገድ የገማሊ ልጅ ዓሚኤል፤ ከአሴር ነገድ የሚካኤል ልጅ ሰቱር፤ ከንፍታሌም ነገድ የያቢ ልጅ ናቢ፤
ዘኍል 13:1-14 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ከዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች አንዳንድ የሕዝብ መሪዎችን መርጠህ፥ እኔ ለእስራኤላውያን ወደምሰጣት ወደ ከነዓን ምድር ሄደው የምድሪቱን ሁኔታ መርምረው እንዲመለሱ ላካቸው፤” ሙሴም በእግዚአብሔር ትእዛዝ መሠረት ከእስራኤል መሪዎች መካከል ከፋራን ምድረ በዳ ዐሥራ ሁለት ሰዎችን ላከ። ስማቸው እንደሚከተለው ነበር፤ ከሮቤል ነገድ የዛኩር ልጅ ሻሙዓ፥ ከስምዖን ነገድ የሖሪ ልጅ ሣፋጥ፥ ከይሁዳ ነገድ የይፉኔ ልጅ ካሌብ፥ ከይሳኮር ነገድ የዮሴፍ ልጅ ይግአል፥ ከኤፍሬም ነገድ የነዌ ልጅ ሆሼዓ ከብንያም ነገድ የራፉ ልጅ ፈልጢ፥ ከዛብሎን ነገድ የሶዲ ልጅ ጋዱኤል፥ ከዮሴፍ ነገድ (እርሱም ከምናሴ ነገድ) የሱሲ ልጅ ጋዲ፥ ከዳን ነገድ የገማሊ ልጅ ዓሚኤል፥ ከአሴር ነገድ የሚካኤል ልጅ ሰቱር፥ ከንፍታሌም ነገድ የዋፍሲ ልጅ ናሕቢ፥
ዘኍል 13:1-14 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ለእስራኤል ልጆች የምሰጣትን የከንዓንን ምድር እንዲሰልሉ ሰዎችን ላክ፤ ከአባቶች ነገድ ሁሉ እያንዳንዱ በመካከላቸው አለቃ የሆነ አንድ ሰው ትልካላችሁ።” ሙሴም እንደ ጌታ ትእዛዝ ከፋራን ምድረ በዳ ላካቸው፤ እነርሱም ሁሉ የእስራኤል ልጆች አለቆች ነበሩ። ስማቸውም ይህ ነበረ፤ ከሮቤል ነገድ የዘኩር ልጅ ሰሙኤል፤ ከስምዖን ነገድ የሱሬ ልጅ ሳፋጥ፤ ከይሁዳ ነገድ የዮፎኒ ልጅ ካሌብ፤ ከይሳኮር ነገድ የዮሴፍ ልጅ ይግዓል፤ ከኤፍሬም ነገድ የነዌ ልጅ ሆሴአ፤ ከብንያም ነገድ የራፉ ልጅ ፈልጢ፤ ከዛብሎን ነገድ የሰዲ ልጅ ጉዲኤል፤ ከዮሴፍ ነገድ እርሱም የምናሴ ነገድ የሱሲ ልጅ ጋዲ፤ ከዳን ነገድ የገማሊ ልጅ ዓሚኤል፤ ከአሴር ነገድ የሚካኤል ልጅ ሰቱር፤ ከንፍታሌም ነገድ የያቢ ልጅ ናቢ፤