ማርቆስ 9:33-50
ማርቆስ 9:33-50 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ቅፍርናሆም መጡ፤ ኢየሱስ ወደ ቤት ከገባ በኋላ ደቀ መዛሙርቱን፦ “በመንገድ ሳላችሁ የተከራከራችሁበት ነገር ምን ነበር?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱ ግን ዝም አሉ፤ ይህም በመንገድ ሳሉ፥ “ከሁላችን የሚበልጥ ማን ነው?” እያሉ ይከራከሩ ስለ ነበረ ነው። እርሱም ከተቀመጠ በኋላ ዐሥራ ሁለቱን ጠርቶ፥ “መጀመሪያ መሆን የሚፈልግ ማናቸውም ሰው የሁሉ መጨረሻና የሁሉም አገልጋይ መሆን አለበት፤” አላቸው። አንድ ሕፃን አምጥቶ በመካከላቸው አቆመው፤ ዐቅፎትም እንዲህ አላቸው፦ “እንደዚህ ካሉት ሕፃናት አንዱን በስሜ የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል ሁሉ እኔን ሳይሆን፥ የላከኝን ይቀበላል።” ዮሐንስ ኢየሱስን “መምህር ሆይ፥ አንድ ሰው በስምህ አጋንንትን ሲያስወጣ አየን፤ ግን ከእኛም ጋር ስላልሆነ ከለከልነው፤” አለው። ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ፦ “በስሜ ተአምር እያደረገ ወዲያውኑ በእኔ ላይ ክፉ የሚናገር ስለሌለ ተዉት፤ አትከልክሉት፤ እኛን የማይቃወም ሁሉ ከእኛ ጋር ነው፤ በእውነት እላችኋለሁ፤ የክርስቶስ ስለ ሆናችሁ በስሜ አንድ ብርጭቆ ውሃ እንኳ የሚያጠጣቸው ዋጋውን አያጣም፤” አላቸው። “ማንም ሰው በእኔ ከሚያምኑት ከእነዚህ ከትንንሾቹ አንዱን ከሚያስት ከባድ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ላይ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለዋል። ስለዚህ እጅህ ኃጢአት እንድትሠራ ቢያስትህ ቈርጠህ ጣለው! ሁለት እጅ እያለህ ወደ ገሃነም ከምትጣል ይልቅ ጒንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል። ገሃነም ትሉ የማይሞትበት፥ እሳቱ የማይጠፋበት ስፍራ ነው። እግርህም ቢያስትህ፥ ቈርጠህ ጣለው፤ ሁለት እግር እያለህ፥ ወደ ገሃነም ከምትጣል ይልቅ፥ አንካሳ ሆነህ፥ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል። [ ገሃነም ትሉ የማይሞትበት፥ እሳቱ የማይጠፋበት ስፍራ ነው።] ዐይንህም ቢያስትህ፥ አውጥተህ ጣለው፤ ሁለት ዐይን እያለህ፥ ወደ ገሃነም ከምትጣል ይልቅ አንድ ዐይና ሆነህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል። ገሃነም ትሉ የማይሞትበት፥ እሳቱም የማይጠፋበት ስፍራ ነው። “መሥዋዕት በጨው እንደሚጠራ እያንዳንዱ ሰው በእሳት መጥራት አለበት። “ጨው መልካም ነው፤ ይሁን እንጂ፥ የጨውነቱን ጣዕም ካጣ በምን ታጣፍጡታላችሁ? “በእናንተም የፍቅር ጨው ጣዕም ይኑርባችሁ፤ እርስ በርሳችሁ ተስማምታችሁ በሰላም ኑሩ፤” አለ።
ማርቆስ 9:33-50 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ወደ ቅፍርናሆምም መጣ። በቤትም ሆኖ “በመንገድ እርስ በርሳችሁ ምን ተነጋገራችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱ ግን በመንገድ “ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን?” ተባብለው ነበርና ዝም አሉ። ተቀምጦም ዐሥራ ሁለቱን ጠርቶ “ሰው ፊተኛ ሊሆን ቢወድ ከሁሉ በኋላ የሁሉም አገልጋይ ይሁን፤” አላቸው። ሕፃንም ይዞ በመካከላቸው አቆመው፤ አቅፎም “እንደዚህ ካሉ ሕፃናት አንዱን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤ የሚቀበለኝም ሁሉ የላከኝን እንጂ እኔን አይቀበልም አላቸው።” ዮሐንስ መልሶ “መምህር ሆይ! አንድ ሰው በስምህ አጋንንትን ሲያወጣ አየነው፤ ስለማይከተለንም ከለከልነው፤” አለው። ኢየሱስ ግን አለ “በስሜ ተአምር ሠርቶ በቶሎ በእኔ ላይ ክፉ መናገር የሚችል ማንም የለምና አትከልክሉት፤ የማይቃወመን እርሱ ከእኛ ጋር ነውና። የክርስቶስ ስለ ሆናችሁ በስሜ ጽዋ ውኀ የሚያጠጣችሁ ሁሉ፥ ዋጋው እንዳይጠፋበት እውነት እላችኋለሁ። “በእኔም ከሚያምኑት ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለው ነበር። እጅህ ብታሰናክልህ ቍረጣት፤ ሁለት እጅ ኖሮህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነም ወደማይጠፋ እሳት ከመሄድ ጕንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻላል። እግርህ ብታሰናክልህ ቍረጣት፤ ሁለት እግር ኖሮህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነም ወደማይጠፋ እሳት ከመጣል አንካሳ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል። ዐይንህ ብታሰናክልህ አውጣት፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነመ እሳት ከመጣል አንዲት ዐይን ኖራህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል። ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና፤ መሥዋዕትም ሁሉ በጨው ይቀመማል። ጨው መልካም ነው፤ ጨው ግን አልጫ ቢሆን በምን ታጣፍጡታላችሁ? በነፍሳችሁ ጨው ይኑርባችሁ፤ እርስ በርሳችሁም ተስማሙ።”
ማርቆስ 9:33-50 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚህ በኋላ ወደ ቅፍርናሆም መጡ። ቤት ከገባ በኋላም፣ “በመንገድ ላይ የምትከራከሩት ስለ ምን ነበር?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱ ግን በመንገድ ላይ የተከራከሩት ከሁሉ የሚበልጥ ማን ነው በሚል ስለ ነበር ዝም አሉ። ከተቀመጠ በኋላ ዐሥራ ሁለቱን ወደ ራሱ ጠርቶ፣ “መጀመሪያ ለመሆን የሚፈልግ፣ ከሁሉ መጨረሻና የሁሉም አገልጋይ ይሁን” አላቸው። አንድ ሕፃን አምጥቶም በመካከላቸው አቆመ፤ ዐቅፎትም፣ “ከእነዚህ ሕፃናት አንዱን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበለኝ ማንም ቢኖር የሚቀበለው እኔን ሳይሆን የላከኝን ነው” አላቸው። ዮሐንስም፣ “መምህር ሆይ፤ አንድ ሰው በስምህ አጋንንት ሲያወጣ አየነው፣ እኛን ስለማይከተልም ልንከለክለው ሞከርን” አለው። ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ፤ “አትከልክሉት፤ ማንም በስሜ ታምር ሠርቶ ወዲያውኑ በእኔ ላይ ክፉ መናገር አይችልም፤ የማይቃወመን ሁሉ ከእኛ ጋራ ነውና፤ እውነት እላችኋለሁ፣ የክርስቶስ በመሆናችሁ በስሜ አንድ ኩባያ ውሃ የሚሰጣችሁ ሁሉ ዋጋውን አያጣም። “ማንም በእኔ ከሚያምኑት ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ከሚያሰናክል ከባድ የወፍጮ ድንጋይ በዐንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለዋል። ስለዚህ እጅህ ብታሰናክልህ ቍረጣት፤ ሁለት እጅ ኖሮህ እሳቱ ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነም ከመሄድ፣ ጕንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል፤ [በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና።] እግርህ ብታሰናክልህ ቍረጣት፤ ሁለት እግር ኖሮህ ወደ ገሃነም ከመጣል፣ ዐንካሳ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል፤ [በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና።] ዐይንህ ብታሰናክልህ ጐልጕለህ አውጣት፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነም ከመጣል፣ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል፤ “ ‘በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና።’ ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና። “ጨው መልካም ነው፤ ነገር ግን ጨው ጨውነቱን ቢያጣ እንዴት መልሳችሁ ጣዕም እንዲኖረው ታደርጉታላችሁ? ጨው በውስጣችሁ ይኑራችሁ፤ እርስ በርሳችሁም ተስማሙ።”
ማርቆስ 9:33-50 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ወደ ቅፍርናሆምም መጣ። በቤትም ሆኖ፦ በመንገድ እርስ በርሳችሁ ምን ተነጋገራችሁ? ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱ ግን በመንገድ፦ ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን? ተባብለው ነበርና ዝም አሉ። ተቀምጦም አሥራ ሁለቱን ጠርቶ፦ ሰው ፊተኛ ሊሆን ቢወድ ከሁሉ በኋላ የሁሉም አገልጋይ ይሁን አላቸው። ሕፃንም ይዞ በመካከላቸው አቆመው አቅፎም፦ እንደዚህ ካሉ ሕፃናት አንዱን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤ የሚቀበለኝም ሁሉ የላከኝን እንጂ እኔን አይቀበልም አላቸው። ዮሐንስ መልሶ፦ መምህር ሆይ፥ አንድ ሰው በስምህ አጋንንትን ሲያወጣ አየነው፥ ስለማይከተለንም ከለከልነው አለው። ኢየሱስ ግን አለ፦ በስሜ ተአምር ሠርቶ በቶሎ በእኔ ላይ ክፉ መናገር የሚችል ማንም የለምና አትከልክሉት፤ የማይቃወመን እርሱ ከእኛ ጋር ነውና። የክርስቶስ ስለ ሆናችሁ በስሜ ጽዋ ውኃ የሚያጠጣችሁ ሁሉ፥ ዋጋው እንዳይጠፋበት እውነት እላችኋለሁ። በእኔም ከሚያምኑት ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለው ነበር። እጅህ ብታሰናክልህ ቍረጣት፤ ሁለት እጅ ኖሮህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነም ወደማይጠፋ እሳት ከመሄድ ጕንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻላል። እግርህ ብታሰናክልህ ቍረጣት፤ ሁለት እግር ኖሮህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነም ወደማይጠፋ እሳት ከመጣል አንካሳ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል። ዓይንህ ብታሰናክልህ አውጣት፤ ሁለት ዓይን ኖሮህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነመ እሳት ከመጣል አንዲት ዓይን ኖራህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል። ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና፥ መሥዋዕትም ሁሉ በጨው ይቀመማል። ጨው መልካም ነው፤ ጨው ግን አልጫ ቢሆን በምን ታጣፍጡታላችሁ? በነፍሳችሁ ጨው ይኑርባችሁ፥ እርስ በርሳችሁም ተስማሙ።
ማርቆስ 9:33-50 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ቅፍርናሆም መጡ፤ ኢየሱስ ወደ ቤት ከገባ በኋላ ደቀ መዛሙርቱን፦ “በመንገድ ሳላችሁ የተከራከራችሁበት ነገር ምን ነበር?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱ ግን ዝም አሉ፤ ይህም በመንገድ ሳሉ፥ “ከሁላችን የሚበልጥ ማን ነው?” እያሉ ይከራከሩ ስለ ነበረ ነው። እርሱም ከተቀመጠ በኋላ ዐሥራ ሁለቱን ጠርቶ፥ “መጀመሪያ መሆን የሚፈልግ ማናቸውም ሰው የሁሉ መጨረሻና የሁሉም አገልጋይ መሆን አለበት፤” አላቸው። አንድ ሕፃን አምጥቶ በመካከላቸው አቆመው፤ ዐቅፎትም እንዲህ አላቸው፦ “እንደዚህ ካሉት ሕፃናት አንዱን በስሜ የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል ሁሉ እኔን ሳይሆን፥ የላከኝን ይቀበላል።” ዮሐንስ ኢየሱስን “መምህር ሆይ፥ አንድ ሰው በስምህ አጋንንትን ሲያስወጣ አየን፤ ግን ከእኛም ጋር ስላልሆነ ከለከልነው፤” አለው። ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ፦ “በስሜ ተአምር እያደረገ ወዲያውኑ በእኔ ላይ ክፉ የሚናገር ስለሌለ ተዉት፤ አትከልክሉት፤ እኛን የማይቃወም ሁሉ ከእኛ ጋር ነው፤ በእውነት እላችኋለሁ፤ የክርስቶስ ስለ ሆናችሁ በስሜ አንድ ብርጭቆ ውሃ እንኳ የሚያጠጣቸው ዋጋውን አያጣም፤” አላቸው። “ማንም ሰው በእኔ ከሚያምኑት ከእነዚህ ከትንንሾቹ አንዱን ከሚያስት ከባድ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ላይ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለዋል። ስለዚህ እጅህ ኃጢአት እንድትሠራ ቢያስትህ ቈርጠህ ጣለው! ሁለት እጅ እያለህ ወደ ገሃነም ከምትጣል ይልቅ ጒንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል። ገሃነም ትሉ የማይሞትበት፥ እሳቱ የማይጠፋበት ስፍራ ነው። እግርህም ቢያስትህ፥ ቈርጠህ ጣለው፤ ሁለት እግር እያለህ፥ ወደ ገሃነም ከምትጣል ይልቅ፥ አንካሳ ሆነህ፥ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል። [ ገሃነም ትሉ የማይሞትበት፥ እሳቱ የማይጠፋበት ስፍራ ነው።] ዐይንህም ቢያስትህ፥ አውጥተህ ጣለው፤ ሁለት ዐይን እያለህ፥ ወደ ገሃነም ከምትጣል ይልቅ አንድ ዐይና ሆነህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል። ገሃነም ትሉ የማይሞትበት፥ እሳቱም የማይጠፋበት ስፍራ ነው። “መሥዋዕት በጨው እንደሚጠራ እያንዳንዱ ሰው በእሳት መጥራት አለበት። “ጨው መልካም ነው፤ ይሁን እንጂ፥ የጨውነቱን ጣዕም ካጣ በምን ታጣፍጡታላችሁ? “በእናንተም የፍቅር ጨው ጣዕም ይኑርባችሁ፤ እርስ በርሳችሁ ተስማምታችሁ በሰላም ኑሩ፤” አለ።
ማርቆስ 9:33-50 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ከዚህ በኋላ ወደ ቅፍርናሆም መጡ። ቤት ከገባ በኋላም፥ “በመንገድ ላይ የምትከራከሩት ስለምን ነበር?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱ ግን በመንገድ ላይ የተከራከሩት፥ ከሁሉ የሚበልጥ ማን ነው በሚል ስለ ነበር ዝም አሉ። ከተቀመጠ በኋላ ዐሥራ ሁለቱን ጠርቶ፥ “መጀመሪያ ለመሆን የሚፈልግ፥ ከሁሉ መጨረሻና የሁሉም አገልጋይ ይሁን” አላቸው። ትንሽ ልጅ አምጥቶም በመካከላቸው አቆመ፤ አቅፎትም፥ “ከእነዚህ ሕፃናት አንዱን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበለኝ ሁሉ የሚቀበለው እኔን ሳይሆን የላከኝን ነው” አላቸው። ዮሐንስም፥ “መምህር ሆይ፤ አንድ ሰው በስምህ አጋንንት ሲያወጣ አየን፥ እኛን ስለማይከተልም ከለከልነው” አሉት። ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ፤ “አትከልክሉት፤ ማንም በስሜ ተአምር ሠርቶ ወዲያውኑ በእኔ ላይ ክፉ መናገር አይችልም፤ የማይቃወመን ሁሉ ከእኛ ጋር ነውና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ የክርስቶስ በመሆናችሁ በስሜ አንድ ኩባያ ውሃ የሚሰጣችሁ ሁሉ ዋጋውን አያጣም።” “በእኔ ከሚያምኑት ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ ከባድ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለዋል። ስለዚህ እጅህ ብታሰናክልህ ቁረጣት፤ ሁለት እጅ ኖሮህ ወደ ገሃነም ከመሄድ፥ ጉንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል፤ በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና፤ እግርህ ብታሰናክልህ ቁረጣት፤ ሁለት እግር ኖሮህ ወደ ገሃነም ከመጣል፥ አንካሳ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል፤ በገሃነም ትሉ አይሞትም እሳቱ አይጠፋምና። ዐይንህ ብታሰናክልህ ጐልጉለህ አውጣት፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነም ከመጣል፥ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል፤ በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና፤ ሰውም ሁሉ በእሳት ይቀመማል። ጨው መልካም ነው፤ ነገር ግን ጨው ጨውነቱን ቢያጣ እንዴት መልሳችሁ ጣዕም እንዲኖረው ታደርጉታላችሁ? ጨው በውስጣችሁ ይኑራችሁ፤ እርስ በርሳችሁም ተስማሙ።”