ማርቆስ 6:48-51
ማርቆስ 6:48-51 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ነፋስ ከወደ ፊታቸው ነበረና እየቀዘፉ ሲጨነቁ አይቶ፥ ከሌሊቱ በአራተኛው ክፍል በባሕር ላይ እየሄደ ወደ እነርሱ መጣ፤ ሊያልፋቸውም ይወድ ነበር። እነርሱ ግን በባሕር ላይ ሲሄድ ባዩት ጊዜ ምትሀት መሰላቸውና ጮኹ፤ ሁሉ አይተውታልና ታወኩም። ወዲያውም ተናገራቸውና “አይዞአችሁ፤ እኔ ነኝ፤ አትፍሩ፤” አላቸው። ወደ እነርሱም ወደ ታንኳይቱ ገባ፤ ነፋሱም ተወ፤ እነርሱ ራሳቸው ያለ መጠን እጅግ ተገረሙ፤
ማርቆስ 6:48-51 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ነፋስ በርትቶባቸው ስለ ነበር፣ ደቀ መዛሙርቱ ከመቅዘፊያው ጋር ሲታገሉ አያቸው፤ በአራተኛውም ክፍለ ሌሊት ገደማ፣ በባሕር ላይ እየሄደ ወደ እነርሱ መጣ፤ በአጠገባቸውም ዐልፎ ሊሄድ ነበር። ነገር ግን በባሕር ላይ ሲሄድ ባዩት ጊዜ ምትሀት መስሏቸው ጮኹ፤ ሁሉም እርሱን ባዩት ጊዜ ደንግጠው ነበርና። እርሱም ወዲያውኑ አነጋገራቸውና፣ “አይዟችሁ እኔ ነኝ፤ አትፍሩ!” አላቸው። እርሱም በጀልባዋ ላይ ወጥቶ አብሯቸው ሆነ፤ ነፋሱም ተወ፤ እነርሱም እጅግ ተደነቁ።
ማርቆስ 6:48-51 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ነፋስ ወደ ፊታቸው ነበረና እየቀዘፉ ሲጨነቁ አይቶ፥ ከሌሊቱ በአራተኛው ክፍል በባሕር ላይ እየሄደ ወደ እነርሱ መጣ፤ ሊያልፋቸውም ይወድ ነበር። እነርሱ ግን በባሕር ላይ ሲሄድ ባዩት ጊዜ ምትሀት መሰላቸውና ጮኹ፥ ሁሉ አይተውታልና፥ ታወኩም። ወዲያውም ተናገራቸውና፦ አይዞአችሁ፤ እኔ ነኝ፥ አትፍሩ አላቸው። ወደ እነርሱም ወደ ታንኳይቱ ገባ፥ ነፋሱም ተወ፤ በራሳቸውም ያለ መጠን እጅግ ተገረሙ፤
ማርቆስ 6:48-51 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ደቀ መዛሙርቱ ከወደፊታቸው በሚነፍሰው ነፋስ ምክንያት መቅዘፍ ተቸግረው ሲጨነቁ አያቸው፤ ከሌሊቱም ከዘጠኝ እስከ ዐሥራ ሁለት ሰዓት ባለው ጊዜ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ እነርሱ መጣ፤ አልፎአቸውም ሊሄድ ነበር። ነገር ግን እነርሱ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ሲሄድ አይተው መንፈስ መስሎአቸው ጮኹ። ሁሉም ባዩት ጊዜ ደነገጡ። እርሱ ግን ወዲያውኑ፦ “አይዞአችሁ! እኔ ነኝ! አትፍሩ!” አላቸው፤ ወደ ጀልባውም ገብቶ፥ ከእነርሱ ጋር በሆነ ጊዜ ነፋሱ ቆመ፤ ደቀ መዛሙርቱ በጣም ተደነቁ።
ማርቆስ 6:48-51 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ነፋስ በርትቶባቸው ስለ ነበር፥ ደቀመዛሙርቱ ከመቅዘፊያው ጋር ሲታገሉ አያቸው፤ በአራተኛውም ክፍለ ሌሊት ገደማ፥ በባሕር ላይ እየሄደ ወደ እነርሱ መጣ፤ በአጠገባቸውም ዐልፎ ሊሄድ ነበር። ነገር ግን በባሕር ላይ ሲሄድ ባዩት ጊዜ ምትሐት መስሏቸው ጮኹ፤ ሁሉም እርሱን ባዩት ጊዜ ደንግጠው ነበርና። እርሱም ወዲያውኑ አነጋገራቸውና፥ “አይዟችሁ እኔ ነኝ፤ አትፍሩ” አላቸው። እርሱም በጀልባዋ ላይ ወጥቶ አብሯቸው ሆነ፤ ነፋሱም ፀጥ አለ፤ እነርሱም እጅግ ተደነቁ፤