ማርቆስ 4:36-40
ማርቆስ 4:36-40 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሕዝቡንም ትተው በታንኳዪቱ ውስጥ እንዳለ ወሰዱት፤ ሌሎች ታንኳዎችም ከእርሱ ጋር ነበሩ። ብርቱ ዐውሎ ነፋስም ተነሣና ውሃ በታንኳይቱ እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ በታንኳይቱ ይገባ ነበር። እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ አንቅተውም “መምህር ሆይ! ስንጠፋ አይገድህምን?” አሉት። ነቅቶም ነፋሱን ገሠጸው፤ ባሕሩንም “ዝም በል፤ ፀጥ በል፤” አለው። ነፋሱም ተወ ታላቅ ፀጥታም ሆነ። “እንዲህ የምትፈሩ ስለ ምን ነው? እንዴትስ እምነት የላችሁም?” አላቸው።
ማርቆስ 4:36-40 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እነርሱ ሕዝቡን ትተው በጀልባዋ ውስጥ እንዳለ በዚያው ይዘውት ሄዱ፤ ሌሎች ጀልባዎችም ዐብረውት ነበሩ። በዚህ ጊዜ ኀይለኛ ዐውሎ ነፋስ ተነሣ፤ ማዕበሉም ውሃ እስኪሞላት ድረስ ጀልባዋን ያናውጣት ነበር። ኢየሱስ ግን ትራስ ተንተርሶ ከጀልባዋ በስተኋላ በኩል ተኝቶ ነበር። እነርሱም ቀስቅሰውት፣ “መምህር ሆይ፤ ስንጠፋ አይገድድህምን?” አሉት። እርሱም ተነሥቶ ነፋሱን ገሠጸው፤ ባሕሩንም፣ “ጸጥ፣ ረጭ በል!” አለው። ነፋሱም ጸጥ፣ ረጭ አለ፤ ፍጹምም ጸጥታ ሆነ። ደቀ መዛሙርቱንም፣ “ስለ ምን እንዲህ ፈራችሁ? እስከዚህ እምነት የላችሁምን?” አላቸው።
ማርቆስ 4:36-40 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ሕዝቡንም ትተው በታንኳ እንዲያው ወሰዱት፥ ሌሎች ታንኳዎችም ከእርሱ ጋር ነበሩ። ብርቱ ዐውሎ ነፋስም ተነሣና ውኃ በታንኳይቱ እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ በታንኳይቱ ይገባ ነበር። እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ አንቅተውም፦ መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን? አሉት። ነቅቶም ነፋሱን ገሠጸው ባሕሩንም፦ ዝም በል፥ ፀጥ በል አለው። ነፋሱም ተወ ታላቅ ፀጥታም ሆነ። እንዲህ የምትፈሩ ስለ ምን ነው? እንዴትስ እምነት የላችሁም? አላቸው።
ማርቆስ 4:36-40 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከሕዝቡም ተለይተው ተሳፍሮበት በነበረው ጀልባ ኢየሱስን ይዘውት ሄዱ፤ ሌሎችም ጀልባዎች አብረው ነበሩ። ብርቱ ዐውሎ ነፋስ ተነሥቶ ውሃው በጀልባው እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ ጀልባውን ይመታ ጀመር። በዚህ ጊዜ ኢየሱስ፥ በጀልባው በኋለኛው ክፍል ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱ ቀሰቀሱትና “መምህር ሆይ! ስንጠፋ አይገድህምን?” አሉት። እርሱም ነቅቶ ነፋሱን ገሠጸው፤ ባሕሩንም “ጸጥ በል!” አለው፤ ነፋሱ ተወ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ። ኢየሱስም፦ “እንዲህ የምትፈሩት ለምንድን ነው? እንዴትስ እምነት የላችሁም?” አላቸው።
ማርቆስ 4:36-40 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ሕዝቡንም ትተው በታንኳዪቱ ውስጥ እንዳለ ወሰዱት፤ ሌሎች ታንኳዎችም ከእርሱ ጋር ነበሩ። ብርቱ ዐውሎ ነፋስም ተነሣና ውሃ በታንኳይቱ እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ በታንኳይቱ ይገባ ነበር። እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ ቀስቅሰውትም “መምህር ሆይ! ስንጠፋ አይገድህምን?” አሉት። ነቅቶም ነፋሱን ገሠጸው፤ ባሕሩንም “ዝም በል፤ ፀጥ በል፤” አለው። ነፋሱም ተወ፤ ታላቅ ፀጥታም ሆነ። “እንዲህ የምትፈሩት ስለምን ነው? እንዴትስ እምነት የላችሁም?” አላቸው።