ማርቆስ 3:1-5
ማርቆስ 3:1-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ደግሞም ወደ ምኵራብ ገባ፤ በዚያም እጁ የሰለለች ሰው ነበር፤ ሊከሱትም በሰንበት ይፈውሰው እንደ ሆነ ይጠባበቁት ነበር። እጁ የሰለለችውንም ሰው “ተነሥተህ ወደ መካከል ና፤” አለው። “በሰንበት በጎ ማድረግ ተፈቅዶአልን? ወይስ ክፉ? ነፍስ ማዳን ወይስ መግደል?” አላቸው፤ እነርሱም ዝም አሉ። ስለ ልባቸውም ድንዛዜ አዝኖ ዙሪያውን እየተመለከተ በቍጣ አያቸው፤ ሰውየውንም “እጅህን ዘርጋ፤” አለው። ዘረጋትም፤ እጁም ዳነች።
ማርቆስ 3:1-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በሌላ ጊዜ ወደ ምኵራብ ገባ፤ በዚያም እጁ የሰለለች ሰው ነበር። በምክንያት ሊከስሱት የሚፈልጉ ሰዎችም በሰንበት ቀን ይፈውሰው እንደ ሆነ ለማየት ይጠባበቁ ነበር። እርሱም እጁ የሰለለችውን ሰው፣ “በተሰበሰበው ሕዝብ ፊት ተነሥተህ ቁም” አለው። ኢየሱስም፣ “በሰንበት ቀን የተፈቀደው መልካም ማድረግ ነው ወይስ ክፉ? ሕይወት ማዳን ነውን ወይስ ማጥፋት?” አላቸው። እነርሱ ግን ዝም አሉ። በልባቸው ደንዳናነት ዐዝኖ በዙሪያው የቆሙትን በቍጣ ተመለከታቸውና ሰውየውን፣ “እጅህን ዘርጋ!” አለው፤ ሰውየውም እጁን ዘረጋ፤ እጁም ፍጹም ደኅና ሆነችለት።
ማርቆስ 3:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ደግሞም ወደ ምኵራብ ገባ፥ በዚያም እጁ የሰለለች ሰው ነበር፤ ሊከሱትም፥ በሰንበት ይፈውሰው እንደ ሆነ ይጠባበቁት ነበር። እጁ የሰለለችውንም ሰው፦ ተነሥተህ ወደ መካከል ና አለው። በሰንበት በጎ ማድረግ ተፈቅዶአልን? ወይስ ክፉ? ነፍስ ማዳን ወይስ መግደል? አላቸው፤ እነርሱም ዝም አሉ። ስለ ልባቸውም ድንዛዜ አዝኖ ዙሪያውን እየተመለከተ በቍጣ አያቸው፥ ሰውየውንም፦ እጅህን ዘርጋ አለው።
ማርቆስ 3:1-5 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ኢየሱስ እንደገና ወደ ምኲራብ ገባ፤ እዚያም አንድ እጀ ሽባ ሰው ነበር። ኢየሱስን ሊከሱት የፈለጉ ሰዎች፥ “እስቲ በሰንበት ቀን ይፈውሰው እንደ ሆነ እንይ!” ብለው ይጠባበቁት ነበር። ኢየሱስም እጀ ሽባውን ሰው፦ “ና በመካከል ቁም” አለው። ከዚያም በኋላ “ለመሆኑ በሰንበት ቀን የተፈቀደው መልካም ማድረግ ነውን ወይስ ክፉ? ነፍስን ማዳን ነውን ወይስ ማጥፋት?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱ ግን ዝም አሉ። ኢየሱስም ስለ ልባቸው ድንዛዜ አዝኖ በዙሪያው ያሉትን በቊጣ ተመለከተና ሰውየውን፦ “እጅህን ዘርጋ” አለው። እርሱም በዘረጋ ጊዜ እጁ ዳነለት።
ማርቆስ 3:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ኢየሱስ እንደገና ወደ ምኵራብ ገባ፤ በዚያም እጁ የሰለለች ሰው ነበር፤ እነርሱም በሰንበት ይፈውሰው እንደሆነ አይተው ሊከስሱት ፈልገው ይጠባበቁት ነበር። እርሱም እጁ የሰለለችውን ሰው “ተነሥ! በመካከል ቁም” አለው። ከዚያም “በሰንበት በጎ ማድረግ ተፈቅዷልን? ወይስ ክፉ? ነፍስ ማዳን ወይስ መግደል?” ሲል ጠየቃቸው፤ እነርሱ ግን ዝም አሉ። ስለ ልባቸውም ድንዛዜ አዝኖ፥ ዙሪያውን በቁጣ ተመለከተና ሰውየውን፦ “እጅህን ዘርጋ፤” አለው። እርሱም ዘረጋ፤ እጁም ዳነች።