ማርቆስ 1:40-42
ማርቆስ 1:40-42 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
አንድ ለምጻም ወደ ኢየሱስ መጣና በእግሩ ሥር ተንበርክኮ፦ “ብትፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህ፤” ሲል ለመነው። ኢየሱስም ራራለትና እጁን ዘርግቶ እየዳሰሰው፥ “ፈቅጃለሁ፤ ንጻ!” አለው። ሰውየውም ወዲያውኑ ከለምጹ ነጻ።
ያጋሩ
ማርቆስ 1 ያንብቡማርቆስ 1:40-42 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ለምጻምም ወደ እርሱ መጥቶ ተንበረከከና “ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ፤” ብሎ ለመነው። ኢየሱስም አዘነለት እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና “እወድዳለሁ፤ ንጻ፤” አለው። በተናገረም ጊዜ ለምጹ ወዲያው ለቀቀውና ነጻ።
ያጋሩ
ማርቆስ 1 ያንብቡማርቆስ 1:40-42 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አንድ ለምጻም ወደ እርሱ ቀርቦ ከፊቱ በመንበርከክ፣ “ብትፈቅድ እኮ ልታነጻኝ ትችላለህ” በማለት ለመነው። ኢየሱስም ለሰውየው በመራራት እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና፣ “እፈቅዳለሁ፣ ንጻ!” አለው። እርሱም ወዲያው ከለምጹ ነጻ፤ ከበሽታውም ተፈወሰ።
ያጋሩ
ማርቆስ 1 ያንብቡማርቆስ 1:40-42 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ለምጻምም ወደ እርሱ መጥቶ ተንበረከከና፦ ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ ብሎ ለመነው። ኢየሱስም አዘነለት እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና፦ እወድዳለሁ፤ ንጻ አለው። በተናገረም ጊዜ ለምጹ ወዲያው ለቀቀውና ነጻ።
ያጋሩ
ማርቆስ 1 ያንብቡ