ማቴዎስ 19:19-26
ማቴዎስ 19:19-26 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አባትህንና እናትህንአክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው።” ጐበዙም “ይህንማ ሁሉ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ፤ ደግሞስ የሚጐድለኝ ምንድር ነው?” አለው። ኢየሱስም “ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፤ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፤ መጥተህም ተከተለኝ፤” አለው። ጐበዙም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ብዙ ንብረት ነበረውና እያዘነ ሄደ። ኢየሱስም ለደቀ መዛሙርቱ “እውነት እላችኋለሁ፥ ለባለጠጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ጭንቅ ነው። ዳግመኛም እላችኋለሁ፤ ባለጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል፤” አለ። ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው እጅግ ተገረሙና “እንኪያስ ማን ሊድን ይችላል?” አሉ። ኢየሱስም እነርሱን ተመልክቶ “ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል፤” አላቸው።
ማቴዎስ 19:19-26 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አባትህንና እናትህን አክብር፤ ጎረቤትህን እንደ ራስህ ውደድ።” ጕልማሳውም ሰው፣ “እነዚህንማ ጠብቄአለሁ፤ ከዚህ ሌላ የሚጐድለኝ ምን አለ?” አለው። ኢየሱስም፣ “ፍጹም ለመሆን ከፈለግህ፣ ሄደህ ንብረትህን ሁሉ ሸጠህ፣ ገንዘቡን ለድኾች ስጥ፤ በሰማይም ሀብት ታገኛለህ። ከዚያም መጥተህ ተከተለኝ” አለው። ጕልማሳው ሰውየም ይህን ሲሰማ፣ ብዙ ሀብት ስለ ነበረው እያዘነ ሄደ። ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አለ፤ “እውነት እላችኋለሁ፣ ለሀብታም ወደ መንግሥተ ሰማይ መግባት እጅግ አስቸጋሪ ነው። ደግሜ እላችኋለሁ፤ ሀብታም ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ ይቀልላል።” ይህን ሲሰሙ፣ ደቀ መዛሙርቱ እጅግ በመገረም፣ “እንግዲያስ ማን ሊድን ይችላል?” ሲሉ ጠየቁ። ኢየሱስም እየተመለከታቸው፣ “ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉም ነገር ይቻላል” አላቸው።
ማቴዎስ 19:19-26 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አባትህንና እናትህን አክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው። ጕኦበዙም፦ ይህንማ ሁሉ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ፥ ደግሞስ የሚጕኦድለኝ ምንድር ነው? አለው። ኢየሱስም፦ ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ አለው። ጕኦበዙም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ብዙ ንብረት ነበረውና እያዘነ ሄደ። ኢየሱስም ለደቀ መዛሙርቱ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ለባለጠጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ጭንቅ ነው። ዳግመኛም እላችኋለሁ፥ ባለጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል አለ። ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው እጅግ ተገረሙና፦ እንኪያስ ማን ሊድን ይችላል? አሉ። ኢየሱስም እነርሱን ተመልክቶ፦ ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል አላቸው።
ማቴዎስ 19:19-26 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
አባትህንና እናትህን አክብር፤ ጐረቤትህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ፤ የሚሉት ትእዛዞች ናቸው” አለው። ወጣቱም “እነዚህንማ ትእዛዞች ፈጽሜአለሁ፤ ሌላስ የሚጐድለኝ ምንድን ነው?” አለ። ኢየሱስም “ፍጹም መሆን ብትፈልግ ሂድና ያለህን ሸጠህ ገንዘቡን ለድኻ ስጥ፤ በሰማይ ሀብት ታገኛለህ፤ መጥተህም ተከተለኝ” አለው። ወጣቱ ግን ብዙ ሀብት ስለ ነበረው ይህን በሰማ ጊዜ እየተከዘ ሄደ። ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፦ “በእውነት እላችኋለሁ፤ ለሀብታም ሰው ወደ መንግሥተ ሰማይ መግባት በጣም ከባድ ነው። ደግሞም እላችኋለሁ፦ ሀብታም ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል።” ደቀ መዛሙርቱ ይህን በሰሙ ጊዜ በጣም ተገረሙና “ታዲያ፥ ማን ሊድን ይችላል?” አሉ። ኢየሱስ ወደ እነርሱ ተመልክቶ “ይህ ነገር ለሰው የማይቻል ነው፤ ለእግዚአብሔር ግን ሁሉም ይቻለዋል” አለ።
ማቴዎስ 19:19-26 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
አባትህንና እናትህን አክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ።” ወጣቱም “ይህን ሁሉ ጠብቄአለሁ፤ አሁን የሚጐድለኝ ምንድነው?” አለው። ኢየሱስም “ፍጹም መሆን ከፈለግህ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፤ በሰማያት መዝገብ ታገኛለህ፤ መጥተህም ተከተለኝ” አለው። ወጣቱ ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ብዙ ንብረት ነበረውና እያዘነ ሄደ። ኢየሱስም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው “እውነት እላችኋለሁ፥ ለባለጸጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ከባድ ነው። ደግሜ እላችኋለሁ፤ ባለጸጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል።” ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው እጅግ ተገረሙና “ታዲያ ማን ሊድን ይችላል?” አሉ። ኢየሱስ ግን አያቸውና እንዲህ አላቸው “ይህ በሰው ዘንድ የማይቻል ነው፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል።”