ማቴዎስ 19:16-21
ማቴዎስ 19:16-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እነሆም፥ አንድ ሰው ቀርቦ “መምህር ሆይ! የዘላለምን ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ላድርግ” አለው። እርሱም “ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው፤ ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ፤” አለው። እርሱም “የትኞችን?” አለው። ኢየሱስም “አትግደል፥ አታመንዝር፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥ አባትህንና እናትህንአክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው።” ጐበዙም “ይህንማ ሁሉ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ፤ ደግሞስ የሚጐድለኝ ምንድር ነው?” አለው። ኢየሱስም “ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፤ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፤ መጥተህም ተከተለኝ፤” አለው።
ማቴዎስ 19:16-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚያም አንድ ሰው ወደ ኢየሱስ ቀርቦ፣ “መምህር ሆይ፤ የዘላለምን ሕይወት አገኝ ዘንድ ምን መልካም ነገር ልሥራ” ሲል ጠየቀው። ኢየሱስም፣ “ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንዱ ብቻ ነው፤ ወደ ሕይወት ለመግባት ከፈለግህ ግን ትእዛዞቹን ጠብቅ” አለው። ሰውየውም፣ “የትኞቹን ትእዛዞች?” ሲል ጠየቀ። ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “አትግደል፣ አታመንዝር፤ አትስረቅ፤ በሐሰት አትመስክር፤ አባትህንና እናትህን አክብር፤ ጎረቤትህን እንደ ራስህ ውደድ።” ጕልማሳውም ሰው፣ “እነዚህንማ ጠብቄአለሁ፤ ከዚህ ሌላ የሚጐድለኝ ምን አለ?” አለው። ኢየሱስም፣ “ፍጹም ለመሆን ከፈለግህ፣ ሄደህ ንብረትህን ሁሉ ሸጠህ፣ ገንዘቡን ለድኾች ስጥ፤ በሰማይም ሀብት ታገኛለህ። ከዚያም መጥተህ ተከተለኝ” አለው።
ማቴዎስ 19:16-21 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እነሆም፥ አንድ ሰው ቀርቦ፦ መምህር ሆይ፥ የዘላለምን ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ላድርግ? አለው። እርሱም፦ ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው፤ ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ አለው። እርሱም፦ የትኞችን? አለው። ኢየሱስም፦ አትግደል፥ አታመንዝር፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥ አባትህንና እናትህን አክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው። ጕኦበዙም፦ ይህንማ ሁሉ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ፥ ደግሞስ የሚጕኦድለኝ ምንድር ነው? አለው። ኢየሱስም፦ ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ አለው።
ማቴዎስ 19:16-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
አንድ ቀን አንድ ሰው ወደ ኢየሱስ መጥቶ፦ “መምህር ሆይ! የዘለዓለምን ሕይወት ለማግኘት ምን መልካም ነገር ማድረግ ይገባኛል?” ሲል ጠየቀው። ኢየሱስም “ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ ወደ ሕይወት ለመግባት ብትፈልግ ግን ትእዛዞችን ፈጽም” አለው። ሰውየውም “የትኞቹን ትእዛዞች?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “አትግደል፤ አታመንዝር፤ አትስረቅ፤ በሐሰት አትመስክር፤ አባትህንና እናትህን አክብር፤ ጐረቤትህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ፤ የሚሉት ትእዛዞች ናቸው” አለው። ወጣቱም “እነዚህንማ ትእዛዞች ፈጽሜአለሁ፤ ሌላስ የሚጐድለኝ ምንድን ነው?” አለ። ኢየሱስም “ፍጹም መሆን ብትፈልግ ሂድና ያለህን ሸጠህ ገንዘቡን ለድኻ ስጥ፤ በሰማይ ሀብት ታገኛለህ፤ መጥተህም ተከተለኝ” አለው።
ማቴዎስ 19:16-21 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
እነሆ አንድ ሰው ቀርቦ “መምህር ሆይ! የዘለዓለምን ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ላድርግ” አለው። እርሱም “ስለ መልካም ነገር እኔን ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው፤ ወደ ሕይወት መግባት ከፈልግህ ግን ትእዛዛቱን ጠብቅ፤” አለው። እርሱም “የትኞቹን?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው “አትግደል፥ አታመንዝር፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥ አባትህንና እናትህን አክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ።” ወጣቱም “ይህን ሁሉ ጠብቄአለሁ፤ አሁን የሚጐድለኝ ምንድነው?” አለው። ኢየሱስም “ፍጹም መሆን ከፈለግህ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፤ በሰማያት መዝገብ ታገኛለህ፤ መጥተህም ተከተለኝ” አለው።