ሉቃስ 8:27-56
ሉቃስ 8:27-56 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ኢየሱስ ከጀልባዋ ወደ ምድር በወረደ ጊዜ፣ አጋንንት ያደረበት አንድ ሰው ከከተማ ወጥቶ አገኘው፤ ይህ ሰው ለብዙ ጊዜ ልብስ ሳይለብስ፣ በቤትም ሳይኖር በመቃብር ቦታ ይኖር ነበር። ኢየሱስንም ባየው ጊዜ እየጮኸ ፊቱ ተደፋ፤ በታላቅ ድምፅም፣ “የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፤ ከእኔ ምን አለህ? እንዳታሠቃየኝ እለምንሃለሁ” አለ። ርኩሱ መንፈስ ይህን ያለው ከሰውየው እንዲወጣ ኢየሱስ አዝዞት ስለ ነበር ነው። ርኩሱ መንፈስ በየጊዜው ስለሚነሣበት ሰውየው በሰንሰለትና በእግር ብረት እየታሰረ ቢጠበቅም፣ የታሰረበትን ሰንሰለት እየበጣጠሰ ያደረበት ጋኔን ወደ በረሓ ይነዳው ነበር። ኢየሱስም፣ “ስምህ ማን ነው?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም ብዙ አጋንንት ገብተውበት ስለ ነበር፣ “ሌጌዎን” አለው። አጋንንቱም እንጦርጦስ ግቡ ብሎ እንዳያዝዛቸው አጥብቀው ለመኑት። በዚያም አካባቢ በተራራ ወገብ ላይ የብዙ ዐሣማ መንጋ ተሰማርቶ ነበር፤ አጋንንቱም ወደ ዐሣማው መንጋ ግቡ ብሎ እንዲፈቅድላቸው ለመኑት፤ እርሱም ፈቀደላቸው። አጋንንቱም ከሰውየው ወጥተው ወደ ዐሣማዎቹ ገቡ፤ የዐሣማውም መንጋ በገደሉ አፋፍ ቍልቍል በመንደርደር ባሕሩ ውስጥ ገብቶ ሰጠመ። እረኞቹም የሆነውን ነገር ባዩ ጊዜ፣ ሸሽተው በመሄድ በከተማውና በገጠሩ አወሩ። ሕዝቡም የተደረገውን ነገር ለማየት ከያሉበት ወጥተው ወደ ኢየሱስ መጡ። አጋንንት የወጡለትም ሰው ልብስ ለብሶ፣ ወደ ልቡናው ተመልሶ፣ በኢየሱስም እግር ሥር ተቀምጦ ባዩት ጊዜ ፈሩ። ይህን ያዩ ሰዎችም በአጋንንት የተያዘው ሰው እንዴት እንደ ዳነ ለሕዝቡ አወሩላቸው። የጌርጌሴኖን አካባቢ ሰዎችም ሁሉ ታላቅ ፍርሀት ስላደረባቸው፣ ከዚያ እንዲሄድላቸው ኢየሱስን ለመኑት፤ እርሱም ወደ ጀልባው ገብቶ ተመልሶ ሄደ። አጋንንት የወጡለትም ሰው ዐብሮት ለመሆን ኢየሱስን ለመነው፤ እርሱ ግን እንዲህ ሲል አሰናበተው፤ “ወደ ቤትህ ተመልሰህ፣ እግዚአብሔር ያደረገልህን ታላቅ ነገር ተናገር።” ሰውየውም ኢየሱስ ያደረገለትን ታላቅ ነገር በከተማው ሁሉ በይፋ እየተናገረ ሄደ። ሕዝቡ ሁሉ መምጣቱን ይጠባበቁ ስለ ነበር፣ ኢየሱስ በተመለሰ ጊዜ በደስታ ተቀበሉት። በዚህ ጊዜ ኢያኢሮስ የተባለ የምኵራብ አለቃ መጥቶ፣ በኢየሱስ እግር ላይ በመውደቅ ወደ ቤቱ እንዲሄድለት ለመነው፤ ይህን ልመና ያቀረበው ዕድሜዋ ዐሥራ ሁለት ዓመት የሆነ አንዲት ልጅ ስለ ነበረችው ነው፤ እርሷ በሞት አፋፍ ላይ ነበረች። ወደዚያው እያመራ ሳለ፣ ሕዝቡ በመጋፋት እጅግ ያጨናንቀው ነበር። ዐሥራ ሁለት ዓመት ደም ሲፈስሳት የኖረች አንዲት ሴት ነበረች፤ ሊፈውሳትም የቻለ ማንም አልነበረም። እርሷም ከበስተኋላው ተጠግታ የልብሱን ጫፍ ነካች፤ የሚፈስሰው ደሟም ወዲያውኑ ቆመ። ኢየሱስም፣ “የነካኝ ማን ነው?” አለ። ሁሉም መንካታቸውን በካዱ ጊዜ ጴጥሮስ፣ “ጌታ ሆይ፤ ሕዝቡ ሁሉ ከብቦህ በግፊያ እያስጨነቀህ ነው” አለው። ኢየሱስ ግን፣ “አንድ ሰው ነክቶኛል፤ ኀይል ከእኔ እንደ ወጣ ዐውቃለሁና” አለ። ሴትዮዋም ሳትታወቅ መሄድ እንዳልቻለች በተረዳች ጊዜ፣ እየተንቀጠቀጠች መጥታ በፊቱ ተደፋች፤ ለምን እንደ ነካችውና እንዴት ወዲያው እንደ ተፈወሰች በሕዝቡ ሁሉ ፊት ተናገረች። እርሱም፣ “ልጄ ሆይ፤ እምነትሽ ፈውሶሻል፤ በሰላም ሂጂ” አላት። ኢየሱስ ገና እየተናገረ ሳለ፣ አንድ ሰው ከምኵራብ አለቃው ከኢያኢሮስ ቤት መጥቶ፣ “ልጅህ ሞታለች፤ ከዚህ በኋላ መምህሩን አታድክመው” አለው። ኢየሱስም ይህን ሰምቶ ኢያኢሮስን፣ “አትፍራ፤ እመን ብቻ እንጂ፤ ልጅህ ትድናለች” አለው። ወደ ኢያኢሮስ ቤት ሲገባም ከጴጥሮስ፣ ከዮሐንስና ከያዕቆብ እንዲሁም ከልጅቱ አባትና እናት በቀር ማንም ዐብሮት እንዲገባ አልፈቀደም። በዚህ ጊዜ ሰዎቹ ሁሉ እያለቀሱላት ዋይ ዋይ ይሉ ነበር። እርሱ ግን፣ “አታልቅሱ፤ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አላቸው። ሰዎቹም መሞቷን ስላወቁ ሣቁበት። እርሱ ግን እጇን ይዞ፣ “ልጄ ሆይ፤ ተነሺ” አላት። የልጅቷም መንፈስ ተመለሰ፤ ወዲያውም ተነሥታ ቆመች፤ ኢየሱስም የሚበላ ነገር እንዲሰጧት አዘዛቸው። ወላጆቿም ተደነቁ፤ እርሱ ግን የሆነውን ነገር ለማንም እንዳያወሩ አዘዛቸው።
ሉቃስ 8:27-56 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ወደ ምድርም በወረዱ ጊዜ ጋኔን ያደረበት ሰው ከከተማ ወጥቶ ተገናኘው፤ ልብሱንም ከጣለ ብዙ ዘመን ሆኖት ነበር፤ በመቃብር ብቻ ይኖር ነበር እንጂ ወደ ቤት አይገባም ነበር፤ ጌታችን ኢየሱስንም ባየው ጊዜ ጮኸ፤ ሮጦም ሰገደለት፤ “የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ካንተ ጋር ምን አለኝ?” እያለም በታላቅ ቃል ጮኸ፤ እንዳያሠቃየውም ማለደው። ክፉውን ጋኔን ከዚያ ሰው ላይ እንዲወጣ ያዝዘው ነበርና፤ ዘወትርም አእምሮዉን ያሳጣው ነበርና፤ ብላቴኖችም በእግር ብረት አስረው ይጠብቁት ነበር፤ እግር ብረቱንም ይሰብር ነበር፤ ጋኔኑም በምድረ በዳ ያዞረው ነበር። ጌታችን ኢየሱስም፥ “ስምህ ማነው?” ብሎ ጠየቀው፤ እርሱም፥ “ስሜ ሌጌዎን ነው” አለው፤ ብዙ አጋንንት ይዘውት ነበርና። ወደ ጥልቁም ይገቡ ዘንድ እንዳይሰድዳቸው ማለዱት። በዚያም ብዙ የእሪያ መንጋ በተራራ ላይ ተሰማርቶ ነበር፤ ወደ እሪያዎችም እንዲገቡባቸው ይፈቅድላቸው ዘንድ ማለዱት፤ እርሱም ፈቀደላቸው። እነዚያ አጋንንትም ከዚያ ሰው ላይ ወጥተው ወደ እሪያዎች ገቡ፤ የእሪያዎችም መንጋ አብደው ከገደሉ ወደ ባሕር ጠልቀው ሞቱ። እረኞችም የሆነውን ባዩ ጊዜ ሸሽተው ሄዱና ገብተው በከተማዉና በመንደሩ አወሩ። ሰዎችም የሆነውን ያዩ ዘንድ ወጡ፤ ሄደውም ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ በደረሱ ጊዜ አጋንንት የወጡለትን ያን ሰው አእምሮዉ ተመልሶለት ልብሱን ለብሶ፥ ከጌታችን ከኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጦ አገኙትና ፈሩ። ያዩትም ሰዎች ጋኔን አድሮበት የነበረው ሰው እንዴት እንደ ዳነ ነገሩአቸው። በጌርጌሴኖንም ዙሪያ ያሉ ሰዎች ከእነርሱ ዘንድ እንዲሄድላቸው ማለዱት፤ ጽኑ ፍርሀት ይዞአቸዋልና፤ ጌታችን ኢየሱስም በታንኳ ሆኖ ተመለሰ። ያም አጋንንት የወጡለት ሰው ከእርሱ ጋር ይሄድ ዘንድ ጌታችን ኢየሱስን ማለደው፤ እርሱ ግን፥ “ወደ ቤትህ ተመልሰህ እግዚአብሔር ያደረገልህን ታላቅ ነገር ሁሉ ተናገር” ብሎ አሰናበተው። እርሱም ሄዶ በከተማዉ ሁሉ ጌታችን ኢየሱስ ያደረገለትን ሁሉ ተናገረ። ጌታችን ኢየሱስም በተመለሰ ጊዜ ሕዝቡ በአንድነት ተቀበሉት፤ ሁሉ ይጠባበቁት ነበርና። እነሆም ኢያኢሮስ የሚባል ሰው መጣ፤ እርሱም የምኵራብ ሹም ነበር፤ ከጌታችን ኢየሱስ እግር በታችም ሰገደ። ወደ ቤቱም ይገባ ዘንድ ለመነው። ዕድሜዋ ዐሥራ ሁለት ዓመት የሚሆናት አንዲት ልጅ ነበረችው፤ እርስዋም ልትሞት ቀርባ ነበረች። ከዚህም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ከእርሱ ጋር ሲሄድ ሰዎች ያጨናንቁት ነበር፤ ከዐሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም ይፈስሳት የነበረች ሴት መጣች፤ ገንዘብዋንም ሁሉ ለባለመድኀኒቶች ሰጥታ ጨርሳ ነበር፤ ነገር ግን ሊያድናት የቻለ ማንም አልነበረም። ቀርባም በጌታችን በኢየሱስ በስተኋላው ቆመችና የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤ ያንጊዜም የደምዋ መፍሰስ ቆመ። ጌታችን ኢየሱስም፥ “ማን ዳሰሰኝ?” አለ፤ ሁሉም ካዱ፤ ጴጥሮስና ከእርሱ ጋር የነበሩትም፥ “መምህር ሆይ፥ ሰው ይጋፋህና ያጨናንቅህ የለምን? አንተ ግን ማን ዳሰሰኝ? ትላለህ” አሉት። ጌታችን ኢየሱስም፥ “የዳሰሰኝ አለ፤ ከእኔ ኀይል እንደ ወጣ ዐውቃለሁና” አላቸው። ሴቲቱም እንዳልተሰወረላት ባየች ጊዜ እየተንቀጠቀጠች ሄዳ ሰገደችለት፤ በሕዝቡም ሁሉ ፊት በምን ምክንያት ወደ እርሱ እንደ ቀረበችና የልብሱን ጫፍ እንደ ዳሰሰች ወዲያውም እንደ ዳነች ተናገረች። እርሱም፥ “ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አዳነችሽ፤ በሰላም ሂጂ” አላት። ይህንም ሲናገር አንድ ሰው ከምኵራቡ ሹም ቤት መጥቶ፥ “ልጅህስ ሞታለች እንግዲህ መምህሩን አታድክመው” አለው። ጌታችን ኢየሱስም በሰማ ጊዜ የምኵራቡን ሹም፥ “አትፍራ፥ ብቻ እመን፤ ልጅህስ ትድናለች” አለው። ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ከጴጥሮስ፥ ከያዕቆብና ከዮሐንስ፥ ከብላቴናይቱም አባትና እናት በቀር ማንም ከእርሱ ጋር ሌላ ሰው ይገባ ዘንድ አልፈቀደም። ሁሉም እያለቀሱ ዋይ ዋይ ይሉላት ነበር፤ ጌታችን ኢየሱስ ግን፥ “አታልቅሱ፤ ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አላቸው። እንደ ሞተችም ዐውቀዋልና ሳቁበት። እርሱ ግን ሁሉን ወደ ውጭ አስወጣና እጅዋን ይዞ ጠራት፤ እንዲህም አላት፥ “ አንቺ ብላቴና ተነሺ።” ወዲያውም ነፍስዋ ተመልሶላት ፈጥና ቆመች፥ የምትበላውንም ይሰጡአት ዘንድ አዘዘ። አባቷና እናቷም አደነቁ፤ እርሱ ግን የሆነውን ለማንም እንዳይነግሩ ከለከላቸው።
ሉቃስ 8:27-56 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ኢየሱስ ከጀልባዋ ወደ ምድር በወረደ ጊዜ፣ አጋንንት ያደረበት አንድ ሰው ከከተማ ወጥቶ አገኘው፤ ይህ ሰው ለብዙ ጊዜ ልብስ ሳይለብስ፣ በቤትም ሳይኖር በመቃብር ቦታ ይኖር ነበር። ኢየሱስንም ባየው ጊዜ እየጮኸ ፊቱ ተደፋ፤ በታላቅ ድምፅም፣ “የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፤ ከእኔ ምን አለህ? እንዳታሠቃየኝ እለምንሃለሁ” አለ። ርኩሱ መንፈስ ይህን ያለው ከሰውየው እንዲወጣ ኢየሱስ አዝዞት ስለ ነበር ነው። ርኩሱ መንፈስ በየጊዜው ስለሚነሣበት ሰውየው በሰንሰለትና በእግር ብረት እየታሰረ ቢጠበቅም፣ የታሰረበትን ሰንሰለት እየበጣጠሰ ያደረበት ጋኔን ወደ በረሓ ይነዳው ነበር። ኢየሱስም፣ “ስምህ ማን ነው?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም ብዙ አጋንንት ገብተውበት ስለ ነበር፣ “ሌጌዎን” አለው። አጋንንቱም እንጦርጦስ ግቡ ብሎ እንዳያዝዛቸው አጥብቀው ለመኑት። በዚያም አካባቢ በተራራ ወገብ ላይ የብዙ ዐሣማ መንጋ ተሰማርቶ ነበር፤ አጋንንቱም ወደ ዐሣማው መንጋ ግቡ ብሎ እንዲፈቅድላቸው ለመኑት፤ እርሱም ፈቀደላቸው። አጋንንቱም ከሰውየው ወጥተው ወደ ዐሣማዎቹ ገቡ፤ የዐሣማውም መንጋ በገደሉ አፋፍ ቍልቍል በመንደርደር ባሕሩ ውስጥ ገብቶ ሰጠመ። እረኞቹም የሆነውን ነገር ባዩ ጊዜ፣ ሸሽተው በመሄድ በከተማውና በገጠሩ አወሩ። ሕዝቡም የተደረገውን ነገር ለማየት ከያሉበት ወጥተው ወደ ኢየሱስ መጡ። አጋንንት የወጡለትም ሰው ልብስ ለብሶ፣ ወደ ልቡናው ተመልሶ፣ በኢየሱስም እግር ሥር ተቀምጦ ባዩት ጊዜ ፈሩ። ይህን ያዩ ሰዎችም በአጋንንት የተያዘው ሰው እንዴት እንደ ዳነ ለሕዝቡ አወሩላቸው። የጌርጌሴኖን አካባቢ ሰዎችም ሁሉ ታላቅ ፍርሀት ስላደረባቸው፣ ከዚያ እንዲሄድላቸው ኢየሱስን ለመኑት፤ እርሱም ወደ ጀልባው ገብቶ ተመልሶ ሄደ። አጋንንት የወጡለትም ሰው ዐብሮት ለመሆን ኢየሱስን ለመነው፤ እርሱ ግን እንዲህ ሲል አሰናበተው፤ “ወደ ቤትህ ተመልሰህ፣ እግዚአብሔር ያደረገልህን ታላቅ ነገር ተናገር።” ሰውየውም ኢየሱስ ያደረገለትን ታላቅ ነገር በከተማው ሁሉ በይፋ እየተናገረ ሄደ። ሕዝቡ ሁሉ መምጣቱን ይጠባበቁ ስለ ነበር፣ ኢየሱስ በተመለሰ ጊዜ በደስታ ተቀበሉት። በዚህ ጊዜ ኢያኢሮስ የተባለ የምኵራብ አለቃ መጥቶ፣ በኢየሱስ እግር ላይ በመውደቅ ወደ ቤቱ እንዲሄድለት ለመነው፤ ይህን ልመና ያቀረበው ዕድሜዋ ዐሥራ ሁለት ዓመት የሆነ አንዲት ልጅ ስለ ነበረችው ነው፤ እርሷ በሞት አፋፍ ላይ ነበረች። ወደዚያው እያመራ ሳለ፣ ሕዝቡ በመጋፋት እጅግ ያጨናንቀው ነበር። ዐሥራ ሁለት ዓመት ደም ሲፈስሳት የኖረች አንዲት ሴት ነበረች፤ ሊፈውሳትም የቻለ ማንም አልነበረም። እርሷም ከበስተኋላው ተጠግታ የልብሱን ጫፍ ነካች፤ የሚፈስሰው ደሟም ወዲያውኑ ቆመ። ኢየሱስም፣ “የነካኝ ማን ነው?” አለ። ሁሉም መንካታቸውን በካዱ ጊዜ ጴጥሮስ፣ “ጌታ ሆይ፤ ሕዝቡ ሁሉ ከብቦህ በግፊያ እያስጨነቀህ ነው” አለው። ኢየሱስ ግን፣ “አንድ ሰው ነክቶኛል፤ ኀይል ከእኔ እንደ ወጣ ዐውቃለሁና” አለ። ሴትዮዋም ሳትታወቅ መሄድ እንዳልቻለች በተረዳች ጊዜ፣ እየተንቀጠቀጠች መጥታ በፊቱ ተደፋች፤ ለምን እንደ ነካችውና እንዴት ወዲያው እንደ ተፈወሰች በሕዝቡ ሁሉ ፊት ተናገረች። እርሱም፣ “ልጄ ሆይ፤ እምነትሽ ፈውሶሻል፤ በሰላም ሂጂ” አላት። ኢየሱስ ገና እየተናገረ ሳለ፣ አንድ ሰው ከምኵራብ አለቃው ከኢያኢሮስ ቤት መጥቶ፣ “ልጅህ ሞታለች፤ ከዚህ በኋላ መምህሩን አታድክመው” አለው። ኢየሱስም ይህን ሰምቶ ኢያኢሮስን፣ “አትፍራ፤ እመን ብቻ እንጂ፤ ልጅህ ትድናለች” አለው። ወደ ኢያኢሮስ ቤት ሲገባም ከጴጥሮስ፣ ከዮሐንስና ከያዕቆብ እንዲሁም ከልጅቱ አባትና እናት በቀር ማንም ዐብሮት እንዲገባ አልፈቀደም። በዚህ ጊዜ ሰዎቹ ሁሉ እያለቀሱላት ዋይ ዋይ ይሉ ነበር። እርሱ ግን፣ “አታልቅሱ፤ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አላቸው። ሰዎቹም መሞቷን ስላወቁ ሣቁበት። እርሱ ግን እጇን ይዞ፣ “ልጄ ሆይ፤ ተነሺ” አላት። የልጅቷም መንፈስ ተመለሰ፤ ወዲያውም ተነሥታ ቆመች፤ ኢየሱስም የሚበላ ነገር እንዲሰጧት አዘዛቸው። ወላጆቿም ተደነቁ፤ እርሱ ግን የሆነውን ነገር ለማንም እንዳያወሩ አዘዛቸው።
ሉቃስ 8:27-56 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ወደ ምድርም በወጣ ጊዜ አጋንንት ያደሩበት አንድ ሰው ከከተማ ወጥቶ ተገናኘው፥ ከብዙ ዘመንም ጀምሮ ልብስ ሳይለብስ በመቃብር እንጂ በቤት አይኖርም ነበር። ኢየሱስንም ባየ ጊዜ ጮኾ በፊቱ ተደፋ በታላቅ ድምፅም፦ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? እንዳትሣቀየኝ እለምንሃለሁ አለ። ርኵሱን መንፈስ ከሰውዬው እንዲወጣ ያዘው ነበርና። ብዙ ዘመንም ይዞት ነበርና፥ በሰንሰለትና በእግር ብረትም ታስሮ ይጠበቅ ነበር፤ እስራቱንም ሰብሮ በጋኔኑ ወደ ምድረ በዳ ይነዳ ነበር። ኢየሱስም፦ ስምህ ማን ነው? ብሎ ጠየቀው። እርሱም ብዙዎች አጋንንት ገብተውበት ነበርና፦ ሌጌዎን አለው። ወደ ጥልቁም ሊሄዱ እንዳያዛቸው ለመኑት። በዚያም በተራራው የብዙ እሪያ መንጋ ይሰማሩ ነበር፤ ወደ እነርሱም ሊገቡ እንዲፈቅድላቸው ለመኑት፤ ፈቀደላቸውም። አጋንንትም ከሰውዬው ወጥተው ወደ እሪያዎች ገቡ፥ መንጋውም ከአፋፉ ወደ ባሕር ተጣደፉና ሰጠሙ። እረኞችም የሆነውን ባዩ ጊዜ ሸሽተው በከተማውና በአገሩ አወሩት። የሆነውን ነገር ሊያዩ ወጥተውም ወደ ኢየሱስ መጡ፥ አጋንንትም የወጡለትን ሰው ለብሶ ልቡም ተመልሶ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጦ አገኙትና ፈሩ። ያዩትም ደግሞ አጋንንት ያደሩበት ሰው እንዴት እንደ ዳነ አወሩላቸው። በዙሪያውም በጌርጌሴኖን አገር ያሉት ሕዝብ ሁሉ ታላቅ ፍርሃት ይዞአቸዋልና ከእነርሱ እንዲሄድ ለመኑት በታንኳም ገብቶ ተመለሰ። አጋንንት የወጡለት ሰውም ከእርሱ ጋር ይኖር ዘንድ ለመነው፤ ነገር ግን፦ ወደ ቤትህ ተመለስ፥ እግዚአብሔር እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረግልህ ንገር ብሎ አሰናበተው። ኢየሱስም እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገለት በከተማው ሁሉ እየሰበከ ሄደ። ኢየሱስም በተመለሰ ጊዜ ሁሉ ይጠብቁት ነበርና ሕዝቡ ተቀበሉት። እነሆም፥ ኢያኢሮስ የሚባል ሰው መጣ፥ እርሱም የምኵራብ አለቃ ነበረ በኢየሱስም እግር ላይ ወድቆ ወደ ቤቱ እንዲገባ ለመነው፤ አሥራ ሁለት ዓመት የሆናት አንዲት ሴት ልጅ ነበረችውና፤ እርስዋም ለሞት ቀርባ ነበረች። ሲሄድም ሕዝቡ ያጨናንቁት ነበር። ከአሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፥ ትዳርዋንም ሁሉ ለባለመድኃኒቶች ከስራ ማንም ሊፈውሳት አልተቻለውም። በኋላውም ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፥ የደምዋም ፈሳሽ በዚያን ጊዜ ቆመ። ኢየሱስም፦ የዳሰሰኝ ማን ነው? አለ። ሁሉም በካዱ ጊዜ፥ ጴጥሮስና ከእርሱ ጋር የነበሩት፦ አቤቱ፥ ሕዝቡ ያጫንቁሃልና ያጋፉህማል፤ የዳሰሰኝ ማን ነው ትላለህን? አሉ። ኢየሱስ ግን፦ አንድ ሰው ዳስሶኛል፥ ኃይል ከእኔ እንደ ወጣ እኔ አውቃለሁና አለ። ሴቲቱም እንዳልተሰወረች ባየች ጊዜ እየተንቀጠቀጠች መጥታ በፊቱ ተደፋች፥ በምን ምክንያትም እንደ ዳሰሰችው ፈጥናም እንደ ተፈወሰች በሕዝቡ ሁሉ ፊት አወራች። እርሱም፦ ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ አላት። እርሱም ገና ሲናገር አንድ ሰው ከምኵራብ አለቃው ቤት መጥቶ፦ ልጅህ ሞታለች፤ እንግዲህ መምህሩን አታድክም አለ። ኢየሱስ ግን ሰምቶ፦ አትፍራ፤ እመን ብቻ ትድንማለች ብሎ መለሰለት። ወደ ቤትም ሲገባ ከጴጥሮስና ከያዕቆብ ከዮሐንስም ከብላቴናይቱም አባትና እናት በቀር ማንም ከእርሱ ጋር ይገባ ዘንድ አልፈቀደም። ሁሉም እያለቀሱላት ዋይ ዋይ ይሉ ነበር። እርሱ ግን፦ አታልቅሱ፤ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም አለ። እንደ ሞተችም አውቀው በጣም ሳቁበት። እርሱ ግን እጅዋን ይዞ፦ አንቺ ብላቴና፥ ተነሺ ብሎ ጮኸ። ነፍስዋም ተመለሰች፥ ፈጥናም ቆመች፥ የምትበላውንም እንዲሰጡአት አዘዘ። ወላጆችዋም ተገረሙ፤ እርሱ ግን የሆነውን ለማንም እንዳይነግሩ አዘዛቸው።
ሉቃስ 8:27-56 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ኢየሱስ ከጀልባ ወደ ምድር በወረደ ጊዜ አጋንንት ያደሩበት አንድ ሰው ከከተማ ወጥቶ ተገናኘው፤ ይህ ሰው ልብሱን ከጣለ ብዙ ጊዜው ነበር፤ የሚኖረውም በመቃብር ቦታ እንጂ በቤት ውስጥ አልነበረም። ኢየሱስን ባየ ጊዜ ጮኸ፤ በኢየሱስ ፊትም ወደቀና ድምፁን ከፍ አድርጎ፥ “አንተ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ከእኔ ጋር ምን ጉዳይ አለህ? እባክህ አታሠቃየኝ፤” አለው። ይህንንም ያለበት ምክንያት ኢየሱስ ርኩሱን መንፈስ ከሰውየው እንዲወጣ አዞት ስለ ነበር ነው። ከዚህ በፊት ርኩሱ መንፈስ በሰውየው ላይ ብዙ ጊዜ ይነሣበት ነበር፤ በሰንሰለትና በእግር ብረት እየታሰረ ይጠበቅ ነበር፤ ይሁን እንጂ ሰንሰለቱን ይበጥስ፥ እግር ብረቱንም ይሰብር ነበር። ጋኔኑም እየነዳ ወደ በረሓ ይወስደው ነበር። ኢየሱስም “ስምህ ማን ነው?” ብሎ ጠየቀው፤ እርሱም ብዙ አጋንንት ሰፍረውበት ስለ ነበር “ስሜ ሌጌዎን ነው” ሲል መለሰለት። ወዲያውም አጋንንቱም “እባክህ ወደ ጥልቁ ገደል አትስደደን” ሲሉ ለመኑት። በዚያም ስፍራ በኮረብታ ጥግ የብዙ ዐሣማዎች መንጋ ተሰማርቶ ነበር፤ አጋንንቱ “ወደ ዐሣማዎቹ እንድንገባ ፍቀድልን” ሲሉ ኢየሱስን ለመኑት፤ እርሱም ፈቀደላቸው። ስለዚህ አጋንንቱ ከሰውየው ወጥተው በዐሣማዎቹ ውስጥ ገቡ፤ ዐሣማዎቹ ከገደሉ ላይ እየተንደረደሩ ወረዱ፤ ወደ ባሕር ገብተውም ሰጠሙ። የዐሣማዎቹም እረኞች የሆነውን ነገር ባዩ ጊዜ ሸሽተው ሄዱ፤ በየከተማውና በየገጠሩም ወሬውን አዳረሱ። ሰዎቹም የሆነውን ነገር ለማየት ከየቤታቸው ወጥተው ወደ ኢየሱስ መጡ፤ አጋንንት የወጡለትንም ሰው ልቡናው ተመልሶለትና ልብሱንም ለብሶ በኢየሱስ እግር ሥር ተቀምጦ ባዩት ጊዜ ፈሩ፤ የዐይን ምስክር የነበሩ ሰዎችም አጋንንት አድረውበት የነበረው ሰው እንዴት እንደ ዳነ አወሩላቸው። ከዚህ በኋላ የጌርጌሴኖን አካባቢ ሰዎች ሁሉ ኢየሱስ ከአገራቸው እንዲሄድላቸው ለመኑት። ይህንንም ያሉበት ምክንያት በጣም ፈርተው ስለ ነበረ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ በጀልባ ተሳፈረና ወደ መጣበት ስፍራ ተመልሶ ሄደ። አጋንንት የወጡለትም ሰው ኢየሱስን “እባክህ ልከተልህ፤” ብሎ ለመነው። ኢየሱስ ግን እንዲህ ብሎ አሰናበተው። “ወደ ቤትህ ሂድና እግዚአብሔር ያደረገልህን ሁሉ ተናገር!”፤ ሰውየውም ኢየሱስ ያደረገለትን ትልቅ ነገር በከተማው ሁሉ እየተናገረ ሄደ። ሕዝቡ ይጠባበቀው ስለ ነበር ኢየሱስ ተመልሶ በመጣ ጊዜ ሁሉም በደስታ ተቀበሉት። በዚያን ጊዜ አንድ የምኲራብ አለቃ የሆነ፥ ኢያኢሮስ የተባለ ሰው መጣ፤ በኢየሱስ እግር ሥር ወድቆ፥ “እባክህ ወደ ቤቴ ናልኝ፤” ብሎ ለመነው። ይህንንም ያለው ዕድሜዋ ዐሥራ ሁለት ዓመት የሆናት አንድያ ልጁ ታማ በሞት አፋፍ ላይ ስለ ነበረች ነው። ኢየሱስም ከእርሱ ጋር አብሮ ሲሄድ ሳለ ተከትለውት የነበሩ ብዙ ሰዎች በመጨናነቅ ይጋፉ ነበር። ዐሥራ ሁለት ዓመት ሙሉ ደም እየመታት የምትሠቃይ አንዲት ሴት ነበረች፤ እርስዋም ያላትን ገንዘብ ሁሉ ለሐኪሞች በመክፈል ጨርሳ ማንም ሊያድናት አልቻለም። እርስዋ ወደ ኢየሱስ መጥታ ከበስተኋላው ቀረበችና የልብሱን ጫፍ ነካች፤ ወዲያውኑ ደምዋ መፍሰሱን አቆመ። ኢየሱስም “ማን ነው የነካኝ?” ሲል ጠየቀ። ሁሉም “እኛ አልነካንህም፤” አሉ፤ ጴጥሮስም “መምህር ሆይ፥ ሕዝቡ እየተጋፋ ሲከተልህ እያየህ ማን ነው የነካኝ ትላለህን?” አለው። ኢየሱስ ግን “ኀይል ከእኔ መውጣቱን ዐውቄአለሁና በእርግጥ አንድ ሰው ነክቶኛል፤” አለ። ሴትዮዋም እንዳልተሰወረች ባወቀች ጊዜ እየተንቀጠቀጠች ወደ ኢየሱስ መጥታ በእግሩ ሥር ወደቀች፤ ከዚያም በኋላ ለምን እንደ ነካችውና እንዴት ወዲያውኑ እንደ ተፈወሰችም በሕዝቡ ሁሉ ፊት ገለጠች። ኢየሱስም “ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ!” አላት። ኢየሱስ ገና ይህንን በመናገር ላይ ሳለ አንድ ሰው ከምኲራብ አለቃው ከኢያኢሮስ ቤት መጥቶ “ልጅህ ሞታለች፤ እንግዲህ መምህሩን በከንቱ አታድክመው!” አለው። ኢየሱስ ግን ይህን ሰምቶ ኢያኢሮስን፥ “አይዞህ አትፍራ፤ እመን ብቻ፤ ልጅህ ትድናለች፤” አለው። ኢየሱስ ወደ ኢያኢሮስ ቤት በደረሰ ጊዜ ከጴጥሮስ፥ ከዮሐንስ፥ ከያዕቆብ፥ ከልጅትዋ አባትና እናት በቀር ሌላ ማንም ከእርሱ ጋር ወደ ውስጥ እንዲገባ አልፈቀደም። በዚያ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ስለ ልጅትዋ ያለቅሱ! ዋይ ዋይም ይሉ ነበር። ኢየሱስ ግን “አታልቅሱ፤ ልጅትዋ አንቀላፍታለች እንጂ አልሞተችም፤” አላቸው። እነርሱ ግን ልጅትዋ መሞትዋን ስላወቁ ሁሉም በማፌዝ ሳቁበት። ኢየሱስ የልጅትዋን እጅ ይዞ፦ “አንቺ ልጅ፥ ተነሽ!” አላት። እርስዋም ነፍስዋ ስለ ተመለሰችላት ወዲያውኑ ብድግ አለች፤ ኢየሱስም “የምትበላውን ስጡአት!” ሲል አዘዘ። የልጅትዋም ወላጆች ተገረሙ፤ እርሱ ግን የሆነውን ነገር ለማንም አትናገሩ ሲል አዘዛቸው።
ሉቃስ 8:27-56 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
እርሱም ወደ ምድር እንደ ወረደ አጋንንት ያደሩበት አንድ ሰው ከከተማ ወጥቶ ተገናኘው፤ ለረጅም ጊዜ ልብስ አይለብስም ነበር፥ በመቃብሮች እንጂ በቤት ውስጥም አይኖርም ነበር። ኢየሱስንም ባየ ጊዜ ጮኾ በፊቱ ተደፋ፤ በታላቅ ድምፅም፦ “የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ! አንተ ከእኔ ጋር ምን አለህ? እንዳታሰቃየኝ እለምንሃለሁ፤” አለ። እንዲህም የሆነው ኢየሱስ ርኩሱን መንፈስ ከሰውዬው እንዲወጣ አዞት ስለ ነበረ ነው። ለብዙም ጊዜ ይዞት ነበርና፤ በሰንሰለትና በእግር ብረትም ታስሮ ይጠበቅ ነበር፤ እስራቱንም ሰብሮ በጋኔኑ ወደ ምድረ በዳ ይወሰድ ነበር። ኢየሱስም፦ “ስምህ ማን ነው?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም ብዙዎች አጋንንት ገብተውበት ነበርና፦ “ሌጌዎን” አለው። ወደ ጥልቁም ሂዱ ብሎ እንዳያዛቸው ለመኑት። በዚያም በኮረብታው ዳርቻ ላይ የብዙ ዐሣማዎች መንጋ ተሰማርቶ ነበር፤ ወደ እነርሱም ለመግባት እንዲፈቅድላቸው ለመኑት፤ ፈቀደላቸውም። አጋንንቱም ከሰውዬው ወጥተው ወደ ዐሣማዎቹ ገቡ፤ መንጋውም ከአፋፉ ወደ ሐይቁ ተጣድፎ በመውረድ ሰጠመ። እረኞቹም የሆነውን ባዩ ጊዜ ሸሽተው በከተማውና በገጠሩ አወሩት። ሰዎቹም የሆነውን ነገር ለማየት ወጥተው ወደ ኢየሱስ መጡ፤ አጋንንትም የወጡለትን ሰው ለብሶ፥ ልቡም ተመልሶ፥ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጦ አገኙትና ፈሩ። ያዩትም ደግሞ አጋንንት ያደሩበት ሰው እንዴት እንደ ዳነ አወሩላቸው። በጌርጌሴኖንም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች የሚኖረው ሕዝብ ሁሉ በታላቅ ፍርሃት ተይዘው ስለ ነበር ከእነርሱ እንዲሄድ ለመኑት፤ እርሱም በታንኳ ገብቶ ተመለሰ። አጋንንትም የወጡለት ሰው ከእርሱ ጋር እንዲሆን ለመነው፤ ኢየሱስ ግን እንዲህ ብሎ አሰናበተው፦ “ወደ ቤትህ ተመለስ፤ እግዚአብሔር እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረግልህ ተናገር።” እርሱም በመላው ከተማ ኢየሱስ እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገለት እየሰበከ ሄደ። ሕዝቡም ሁሉ እየጠበቁት ስለ ነበር ኢየሱስ በተመለሰ ጊዜ ተቀበሉት። እነሆም፥ ኢያኢሮስ የሚባል ሰው መጣ፤ እርሱም የምኵራብ አለቃ ነበረ፤ በኢየሱስም እግር ላይ ወድቆ ወደ ቤቱ እንዲገባ ለመነው፤ ዐሥራ ሁለት ዓመት የሚሆናት አንዲት ሴት ልጅ ነበረችውና፤ እርሷም ለመሞት እያጣጣረች ነበር። ሲሄድም ሕዝቡ በዙርያው እየተጋፉት ያጨናንቁት ነበር። ከዐሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፤ ያላትንም ንብረት ሁሉ ተጠቅማ ለባለመድኃኒቶች ብታውልም ማንም ሊፈውሳት አልተቻለውም። ከበስተኋላውም ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤ ወዲያውም ደምዋ መፍሰሱን አቆመ። ኢየሱስም፦ “ማን ነው የነካኝ?” አለ። ሁሉም በካዱ ጊዜ፥ ጴጥሮስ፦ “አቤቱ! ሕዝቡ በዙሪያህ ከበውህ እየተጋፉህ እኮ ነው!” አለ። ኢየሱስ ግን፦ “አንድ ሰው ዳስሶኛል፤ ከእኔ ኃይል መውጣቱን አውቄአለሁና፤” አለ። ሴቲቱም መደበቅ እንዳልቻለች ባወቀች ጊዜ እየተንቀጠቀጠች መጥታ በፊቱ ተደፋች፤ በምን ምክንያት እንደ ዳሰሰችውና እንዴት ፈጥና እንደ ተፈወሰች በሕዝቡ ሁሉ ፊት አወራች። እርሱም፦ “ልጄ ሆይ! እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፤” አላት። እርሱም ይህን እየተናገረ ሳለ አንድ ሰው ከምኵራብ አለቃው ቤት መጥቶ፦ “ልጅህ ሞታለች፤ እንግዲህ መምህሩን አታድክም፤” አለ። ኢየሱስ ግን ይህን ሰምቶ ለኢያኢሮስ መልሶ እንዲህ አለው፦ “አትፍራ፤ እመን ብቻ፤ እርሷም ትድናለች።” ወደ ቤቱም በደረሰ ጊዜ ከጴጥሮስና ከያዕቆብ ከዮሐንስም፥ ከልጅቱም አባትና እናት በቀር ማንም ከእርሱ ጋር እንዲገባ አልፈቀደም። ሁሉም እያለቀሱ ደረታቸውን ይመቱላት ነበር። እርሱ ግን፦ “አታልቅሱ፤ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም፤” አለ። እንደ ሞተችም ስላወቁ በጣም ሳቁበት። እርሱ ግን እጅዋን ይዞ፦ “አንቺ ልጅ! ተነሺ፤” ብሎ ተጣራ። መንፈሷም ተመለሰች፤ ፈጥናም ተነሣች፤ የምትበላውም ነገር እንዲሰጣት አዘዘ። ወላጆችዋም ተገረሙ፤ እርሱ ግን የሆነውን ለማንም እንዳይነግሩ አዘዛቸው።