የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሉቃስ 24:33-42

ሉቃስ 24:33-42 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በዚ​ያ​ችም ሰዓት ተነ​ሥ​ተው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ፤ ዐሥራ አን​ዱን ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትና አብ​ረ​ዋ​ቸው የነ​በ​ሩ​ት​ንም ተሰ​ብ​ስ​በው አገ​ኙ​አ​ቸው፤ እን​ዲህ እያሉ፥ “ጌታ​ችን በእ​ው​ነት ተነ​ሥ​ቶ​አል፤ ለስ​ም​ዖ​ንም ታይ​ቶ​ታል።” እነ​ር​ሱም በመ​ን​ገድ የሆ​ነ​ው​ንና እን​ጀ​ራ​ውን ሲቈ​ርስ ጌታ​ች​ንን እን​ዴት እን​ዳ​ወ​ቁት ነገ​ሩ​አ​ቸው። ይህ​ንም ሲነ​ጋ​ገሩ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ቆመና፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን፤ አት​ፍሩ፤ እኔ ነኝ” አላ​ቸው። እነ​ርሱ ግን ፈሩ፤ ደነ​ገ​ጡም፤ ምት​ሐ​ት​ንም የሚ​ያዩ መሰ​ላ​ቸው። እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ምን ያስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ች​ኋል? በል​ባ​ች​ሁስ እን​ዲህ ያለ ዐሳብ ለምን ይነ​ሣ​ሣል? እጄ​ንና እግ​ሬን እዩ፤ ዳስ​ሱ​ኝም፤ እኔ እንደ ሆን​ሁም ዕወቁ፤ በእኔ እን​ደ​ም​ታ​ዩት ለም​ት​ሐት አጥ​ን​ትና ሥጋ የለ​ው​ምና።” ይህ​ንም ብሎ እጆ​ቹ​ንና እግ​ሮ​ቹን አሳ​ያ​ቸው። ከድ​ን​ጋጤ የተ​ነ​ሣም ገና ሳያ​ምኑ ደስ ብሎ​አ​ቸ​ውም ሲያ​ደ​ንቁ ሳሉ፥ “በዚህ አን​ዳች የሚ​በላ አላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም ከተ​ጠ​በሰ ዓሣ አንድ ቁራጭ፤ ከማር ወለ​ላም ጥቂት ሰጡት።

ሉቃስ 24:33-42 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በዚያኑም ሰዓት ተነሥተው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ ዐሥራ አንዱና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም በዚያ በአንድነት ተሰብስበው አገኟቸው፤ “እነርሱም ጌታ በርግጥ ተነሥቷል! ለስምዖንም ታይቷል” ይባባሉ ነበር። ሁለቱ ደቀ መዛሙርትም በመንገድ ላይ የሆነውንና ኢየሱስ እንጀራውን በቈረሰ ጊዜ እንዴት እንዳወቁት ተረኩላቸው። ይህን እየተነጋገሩ ሳሉ፣ ኢየሱስ ራሱ በመካከላቸው ቆሞ፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። እነርሱ ግን ደንግጠው በፍርሀት ተዋጡ፤ መንፈስም ያዩ መሰላቸው። እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ለምን ትጨነቃላችሁ? ለምንስ ጥርጣሬ በልባችሁ ይገባል? እጆቼንና እግሮቼን ተመልከቱ፤ እኔው ራሴ ነኝ። ደግሞም ንኩኝና እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት መንፈስ ሥጋና ዐጥንት የለውምና።” ይህንም ብሎ እጆቹንና እግሮቹን አሳያቸው። እነርሱም ከመደሰትና ከመገረም የተነሣ ገና ሳያምኑ፣ “በዚያ ቦታ አንዳች የሚበላ ነገር አላችሁን?” አላቸው። እነርሱም ከተጠበሰ ዓሣ አንድ ቍራሽ ሰጡት፤

ሉቃስ 24:33-42 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እነርሱም በዚያችው ሰዓት ተነሡና ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው ሄዱ፤ በዚያም ዐሥራ አንዱን ደቀ መዛሙርት አብረዋቸው ካሉት ጋር በአንድነት ተሰብስበው አገኙአቸው። እነርሱም “ጌታ ኢየሱስ በእርግጥ ተነሥቶአል! ለስምዖንም ታይቶአል!” ይሉ ነበር። ሁለቱም ደቀ መዛሙርት በበኩላቸው በመንገድ ላይ የሆነውን ነገርና ጌታ ኢየሱስ እንጀራውን በቈረሰ ጊዜ እንዴት እንዳወቁትም ተረኩላቸው። እነርሱም ይህን ሲናገሩ ሳሉ ኢየሱስ ራሱ በመካከላቸው ቆሞ፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” አላቸው። እነርሱ ግን መንፈስ የሚያዩ መስሎአቸው ደንግጠው በፍርሃት ተዋጡ። ኢየሱስ ግን እንዲህ አላቸው፤ “ስለምን ትደነግጣላችሁ፤ ስለምንስ በልባችሁ ትጠራጠራላችሁ? እጆቼንና እግሮቼን አይታችሁ እኔ ራሴ መሆኔን ዕወቁ፤ ዳሳችሁም እዩኝ፤ በእኔ እንደምታዩት መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውም።” ይህንንም ብሎ እጆቹንና እግሮቹን አሳያቸው፤ እነርሱም ከደስታና ከአድናቆት ብዛት የተነሣ ገና አላመኑም ነበር። ኢየሱስም “አንዳች የሚበላ ነገር አላችሁን?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም ትንሽ የተጠበሰ ዓሣ ሰጡት።

ሉቃስ 24:33-42 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በዚያችም ሰዓት ተነሥተው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ ዐሥራ አንዱንና ከእነርሱ ጋር የነበሩትንም በአንድነት ተሰብስበው አገኙአቸው። እነርሱም “ጌታ በእርግጥ ተነሥቷል፥ ለስምዖንም ታይቷል” ይሉ ነበር። እነርሱም በመንገድ የሆነውን፥ እንጀራውንም በቈረሰ ጊዜ እንዴት እንዳወቁት ተረኩላቸው። ይህንንም ሲነጋገሩ ሳለ ኢየሱስ ራሱ በመካከላቸው ቆሞ “ሰላም ለእናንተ ይሁን፤” አላቸው። እነርሱ ግን ደንግጠው በፍርሃት ተዋጡ፤ መንፈስም ያዩ መሰላቸው። እርሱም እንዲህ አላቸው “ስለምን ትደነግጣላችሁ? ስለ ምንስ ጥርጣሬ በልባችሁ ያድራል? እኔ ራሴ እንደሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ ዳስሱኝና እዩ፥ መንፈስ በእኔ እንደምታዩት፥ ሥጋና አጥንት የለውምና፤” ይህንም ብሎ እጆቹንና እግሮቹን አሳያቸው። እነርሱም ከደስታ ብዛት ገና ሳያምኑ ገና በመገረም ላይ ሳሉ “በዚህ አንዳች የሚበላ ነገር አላችሁን?” አላቸው። እነርሱም ትንሽ የተጠበሰ ዓሣ ሰጡት፤