ሉቃስ 21:25-38

ሉቃስ 21:25-38 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“በፀሓይ፣ በጨረቃና በከዋክብት ላይ ምልክት ይሆናል፤ ከባሕሩና ከሞገድ ድምፅ የተነሣ፣ በምድር ላይ ያሉ ሕዝቦች ይጨነቃሉ፤ ይታወካሉም። የሰማያት ኀይላት ስለሚናወጡ፣ ሰዎች በፍርሀትና በዓለም ላይ ምን ይመጣ ይሆን እያሉ በመጠባበቅ ይዝላሉ። በዚያ ጊዜ የሰው ልጅ በኀይልና በታላቅ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል። እናንተም እነዚህ ነገሮች መፈጸም ሲጀምሩ፣ መዳናችሁ ስለ ተቃረበ ቀጥ ብላችሁ ቁሙ፤ ራሳችሁንም ወደ ላይ ቀና አድርጉ።” ቀጥሎም እንዲህ ሲል ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ “በለስንና ዛፎችን ሁሉ ተመልከቱ፤ ቅጠሎቻቸው አቈጥቍጠው ስታዩ፣ በዚያ ጊዜ በጋ መቃረቡን ራሳችሁ ታውቃላችሁ። እንዲሁ ደግሞ እነዚህ ነገሮች መፈጸማቸውን ስታዩ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ቀረበች ዕወቁ። “እውነት እላችኋለሁ፤ ይህ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም። ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም። “እንግዲህ በገደብ የለሽ ሕይወት፣ በመጠጥ ብዛትና ስለ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝልና ያ ቀን እንደ ወጥመድ ድንገት እንዳይደርስባችሁ ተጠንቀቁ፤ ይህ በመላው ምድር በሚኖሩት ሁሉ ላይ ይደርሳልና። ስለዚህ ከሚመጣው ሁሉ እንድታመልጡና በሰው ልጅ ፊት መቆም እንድትችሉ ሁልጊዜ ተግታችሁ ጸልዩ።” ኢየሱስም ቀን ቀን በቤተ መቅደስ እያስተማረ፣ ሌሊት ግን ደብረ ዘይት ወደ ተባለ ተራራ ወጥቶ ያድር ነበር። ሕዝቡም ሁሉ ሊሰሙት ማልደው ወደ ቤተ መቅደስ ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።

ሉቃስ 21:25-38 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በፀሐይና በጨረቃ፥ በከዋክብትም ላይ ድንቅ ምልክቶች ይታያሉ፤ በምድርም ላይ ሕዝቦች ሁሉ ከባሕርና ከማዕበሉ አስደንጋጭ ድምፅ የተነሣ ፈርተው ይጨነቃሉ። በዓለም ላይ የሚመጣውን ነገር በመጠባበቅ ሰዎች በፍርሃት ይሸበራሉ፤ በዚያን ጊዜ የሰማይ ኀይሎች ይናወጣሉ፤ ከዚህም በኋላ የሰው ልጅ በታላቅ ኀይልና ክብር በደመና ላይ ሆኖ ሲመጣ ሰዎች ያዩታል። ይህ ሁሉ መሆን በሚጀምርበት ጊዜ መዳናችሁ ቀርቦአልና ቀና ብላችሁ ወደ ላይ ተመልከቱ።” ቀጥሎም ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፦ “የበለስን ዛፍና የሌሎችንም ዛፎች ሁኔታ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤ ቅጠሎቻቸው ሲያቈጠቊጡ ባያችሁ ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ። በዚህ ዐይነት ይህ ሁሉ ነገር መሆን ሲጀምር ባያችሁ ጊዜ የእግዚአብሔር መንግሥት ልትመጣ መቃረብዋን ዕወቁ። “በእውነት እላችኋለሁ፤ ይህ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም። ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።” ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በመብልና በመጠጥ ብዛት በስካርም በመባከንና ስለ ዓለማዊ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝል ተጠንቀቁ! አለበለዚያ ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይይዛችኋል። ያ ቀን በምድር ላይ የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ በድንገት ያጠምዳቸዋል። ስለዚህ ከሚመጣው ክፉ ነገር ሁሉ ለማምለጥ ኀይል እንድታገኙና በሰው ልጅ ፊት ለመቆም እንድትችሉ እየጸለያችሁ ዘወትር ትጉ።” ኢየሱስ በየቀኑ በቤተ መቅደስ ያስተምር ነበር፤ ሲመሽ ግን ደብረ ዘይት ወደምትባል ተራራ ላይ እየወጣ ያድር ነበር። ሰዎቹ ሁሉ ኢየሱስን ለመስማት ጠዋት በማለዳ ወደ ቤተ መቅደስ ወደ እርሱ ይሄዱ ነበር።

ሉቃስ 21:25-38 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

“በፀ​ሐ​ይና በጨ​ረቃ፥ በከ​ዋ​ክ​ብ​ትም ላይ ምል​ክት ይሆ​ናል፤ በም​ድር ላይም አሕ​ዛብ ይጨ​ነ​ቃሉ፤ ከባ​ሕ​ሩና ከሞ​ገዱ ድምፅ የተ​ነ​ሣም ይሸ​በ​ራሉ። በዓ​ለም ላይ ከሚ​መ​ጣው ፍር​ሀ​ትና ሽብር የተ​ነ​ሣም የሰ​ዎች ነፍስ ትዝ​ላ​ለች፤ ያን​ጊዜ የሰ​ማ​ያት ኀይል ይና​ወ​ጣ​ልና። ያን​ጊ​ዜም በሰ​ማይ ደመና፥ በፍ​ጹም ኀይ​ልና ክብር ሲመጣ የሰ​ውን ልጅ ያዩ​ታል። ይህም ሁሉ በሆነ ጊዜ ወደ ላይ አቅ​ን​ታ​ችሁ ተመ​ል​ከቱ፤ ራሳ​ች​ሁ​ንም አንሡ፤ የሚ​ያ​ድ​ና​ችሁ መጥ​ቶ​አ​ልና።” ምሳ​ሌም መስሎ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በለ​ስ​ንና ዛፎ​ችን ሁሉ እዩ። ለም​ል​መ​ውም ያያ​ች​ኋ​ቸው እንደ ሆነ መከር እንደ ደረሰ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። እን​ዲሁ እና​ን​ተም ይህ እንደ ሆነ ስታዩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እንደ ደረ​ሰች ዕወቁ። እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይህ ሁሉ እስ​ኪ​ደ​ረግ ድረስ ይህቺ ትው​ልድ አታ​ል​ፍም። ሰማ​ይና ምድር ያል​ፋል፤ ቃሌ ግን አያ​ል​ፍም። “ራሳ​ች​ሁን ጠብቁ፤ በመ​ብ​ልና በመ​ጠጥ፥ በመ​ቀ​ማ​ጠ​ልና የዓ​ለ​ምን ኑሮ በማ​ሰብ ልባ​ች​ሁን አታ​ደ​ን​ድኑ፤ ያቺ ቀንም በድ​ን​ገት ትደ​ር​ስ​ባ​ች​ኋ​ለች። በም​ድር በሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ላይ እንደ ተዘ​ረ​ጋች ወጥ​መድ ትደ​ር​ሳ​ለ​ችና። እን​ግ​ዲህ ከዚህ ከሚ​መ​ጣው ሁሉ በጸ​ሎ​ታ​ችሁ ማም​ለጥ እን​ድ​ት​ችሉ፥ በሰው ልጅ ፊትም እን​ድ​ት​ቆሙ ሁል​ጊዜ ትጉ።” ቀን ቀን በመ​ቅ​ደስ ያስ​ተ​ምር ነበር፤ ሌሊት ግን ወጥቶ ደብረ ዘይት በሚ​ባ​ለው ተራራ ያድር ነበር። ሕዝ​ቡም ሁሉ ቃሉን ሊሰሙ እርሱ ወዳ​ለ​በት ወደ መቅ​ደስ ማል​ደው ይሄዱ ነበር።

ሉቃስ 21:25-38 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“በፀሓይ፣ በጨረቃና በከዋክብት ላይ ምልክት ይሆናል፤ ከባሕሩና ከሞገድ ድምፅ የተነሣ፣ በምድር ላይ ያሉ ሕዝቦች ይጨነቃሉ፤ ይታወካሉም። የሰማያት ኀይላት ስለሚናወጡ፣ ሰዎች በፍርሀትና በዓለም ላይ ምን ይመጣ ይሆን እያሉ በመጠባበቅ ይዝላሉ። በዚያ ጊዜ የሰው ልጅ በኀይልና በታላቅ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል። እናንተም እነዚህ ነገሮች መፈጸም ሲጀምሩ፣ መዳናችሁ ስለ ተቃረበ ቀጥ ብላችሁ ቁሙ፤ ራሳችሁንም ወደ ላይ ቀና አድርጉ።” ቀጥሎም እንዲህ ሲል ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ “በለስንና ዛፎችን ሁሉ ተመልከቱ፤ ቅጠሎቻቸው አቈጥቍጠው ስታዩ፣ በዚያ ጊዜ በጋ መቃረቡን ራሳችሁ ታውቃላችሁ። እንዲሁ ደግሞ እነዚህ ነገሮች መፈጸማቸውን ስታዩ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ቀረበች ዕወቁ። “እውነት እላችኋለሁ፤ ይህ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም። ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም። “እንግዲህ በገደብ የለሽ ሕይወት፣ በመጠጥ ብዛትና ስለ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝልና ያ ቀን እንደ ወጥመድ ድንገት እንዳይደርስባችሁ ተጠንቀቁ፤ ይህ በመላው ምድር በሚኖሩት ሁሉ ላይ ይደርሳልና። ስለዚህ ከሚመጣው ሁሉ እንድታመልጡና በሰው ልጅ ፊት መቆም እንድትችሉ ሁልጊዜ ተግታችሁ ጸልዩ።” ኢየሱስም ቀን ቀን በቤተ መቅደስ እያስተማረ፣ ሌሊት ግን ደብረ ዘይት ወደ ተባለ ተራራ ወጥቶ ያድር ነበር። ሕዝቡም ሁሉ ሊሰሙት ማልደው ወደ ቤተ መቅደስ ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።

ሉቃስ 21:25-38 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ከባሕሩና ከሞገዱም ድምፅ የተነሣ እያመነቱ ይጨነቃሉ፤ ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም የሚመጣበትን ከመጠበቅ የተነሣ ይደክማሉ፤ የሰማያት ኃይላት ይናወጣሉና። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በኃይልና በብዙ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል። ይህም ሊሆን ሲጀምር ቤዛችሁ ቀቦአልና አሻቅባችሁ ራሳችሁን አንሡ። ምሳሌንም ነገራቸው እንዲህ ሲል፦ በለስንና ዛፎችን ሁሉ እዩ፤ ሲያቈጠቍጡ ተመልክታችሁ በጋ አሁን እንደ ቀረበ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። እንዲሁ ደግሞ እናንተ ይህ ሁሉ መሆኑን ስታዩ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ቀረበች እወቁ። እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም። ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም። ነገር ግን ልባችሁ በመጠጥ ብዛትና በስካር ስለ ትዳርም በማሰብ እንዳይከብድ፥ ያ ቀንም በድንገት እንዳይመጣባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ በምድር ሁሉ ላይ በሚቀመጡ ሁሉ እንደ ወጥመድ ይደርስባቸዋልና። እንግዲህ ሊመጣ ካለው ከዚህ ሁሉ ለማምለጥ፥ በሰው ልጅም ፊት ለመቆም እንድትችሉ ስትጸልዩ ሁል ጊዜ ትጉ። ዕለት ዕለትም በመቅደስ ያስተምር ነበር፥ ሌሊት ግን ደብረ ዘይት ወደምትባል ተራራ ወጥቶ ያድር ነበር። ሕዝቡም ሁሉ ይሰሙት ዘንድ ማልደው በመቅደስ ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።

ሉቃስ 21:25-38 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በፀሐይና በጨረቃ፥ በከዋክብትም ላይ ድንቅ ምልክቶች ይታያሉ፤ በምድርም ላይ ሕዝቦች ሁሉ ከባሕርና ከማዕበሉ አስደንጋጭ ድምፅ የተነሣ ፈርተው ይጨነቃሉ። በዓለም ላይ የሚመጣውን ነገር በመጠባበቅ ሰዎች በፍርሃት ይሸበራሉ፤ በዚያን ጊዜ የሰማይ ኀይሎች ይናወጣሉ፤ ከዚህም በኋላ የሰው ልጅ በታላቅ ኀይልና ክብር በደመና ላይ ሆኖ ሲመጣ ሰዎች ያዩታል። ይህ ሁሉ መሆን በሚጀምርበት ጊዜ መዳናችሁ ቀርቦአልና ቀና ብላችሁ ወደ ላይ ተመልከቱ።” ቀጥሎም ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፦ “የበለስን ዛፍና የሌሎችንም ዛፎች ሁኔታ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤ ቅጠሎቻቸው ሲያቈጠቊጡ ባያችሁ ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ። በዚህ ዐይነት ይህ ሁሉ ነገር መሆን ሲጀምር ባያችሁ ጊዜ የእግዚአብሔር መንግሥት ልትመጣ መቃረብዋን ዕወቁ። “በእውነት እላችኋለሁ፤ ይህ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም። ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።” ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በመብልና በመጠጥ ብዛት በስካርም በመባከንና ስለ ዓለማዊ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝል ተጠንቀቁ! አለበለዚያ ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይይዛችኋል። ያ ቀን በምድር ላይ የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ በድንገት ያጠምዳቸዋል። ስለዚህ ከሚመጣው ክፉ ነገር ሁሉ ለማምለጥ ኀይል እንድታገኙና በሰው ልጅ ፊት ለመቆም እንድትችሉ እየጸለያችሁ ዘወትር ትጉ።” ኢየሱስ በየቀኑ በቤተ መቅደስ ያስተምር ነበር፤ ሲመሽ ግን ደብረ ዘይት ወደምትባል ተራራ ላይ እየወጣ ያድር ነበር። ሰዎቹ ሁሉ ኢየሱስን ለመስማት ጠዋት በማለዳ ወደ ቤተ መቅደስ ወደ እርሱ ይሄዱ ነበር።

ሉቃስ 21:25-38 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

“በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ላይ ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ከባሕሩና ከሞገዱም ድምፅ የተነሣ በመረበሽ ይጨነቃሉ፤ የሰማያት ኀይላት ይናወጣሉና፥ ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም ላይ የሚመጣውን ከመጠበቅ የተነሣ ይደክማሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በኃይልና በብዙ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል። ይህም መሆን ሲጀምር መዳናችሁ ቀርቦአልና ቁሙ፤ ቀናም በሉ።” እንዲህ ሲልም ምሳሌ ነገራቸው “በለስንና ዛፎችን ሁሉ እዩ፤ ሲያቈጠቁጡ ተመልክታችሁ በጋ አሁን እንደ ቀረበ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። እንዲሁ ደግሞ ይህ ሁሉ መሆኑን ስታዩ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ቀረበች እወቁ። እውነት እላችኋለሁ፤ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም። ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም። “ነገር ግን ልባችሁ በመጠጥ ብዛትና በስካር፥ ስለ ኑሮም ማሰብ እንዳይዝል፥ ያ ቀንም በድንገት እንዳይመጣባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ በምድር ሁሉ ላይ በሚቀመጡ ሁሉ እንደ ወጥመድ ይደርስባቸዋልና። እንግዲህ ሊመጣ ካለው ከዚህ ሁሉ ለማምለጥ፥ በሰው ልጅም ፊት ለመቆም እንድትችሉ እየጸለያችሁ ሁልጊዜ ትጉ።” ዕለት ዕለትም በመቅደስ ያስተምር ነበር፤ ሌሊት ግን ደብረዘይት ወደምትባል ተራራ ወጥቶ ያድር ነበር። ሕዝቡም ሁሉ ይሰሙት ዘንድ ማልደው ወደ መቅደስ ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።