ሉቃስ 11:1-28

ሉቃስ 11:1-28 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

አንድ ቀን ኢየሱስ በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፤ ጸሎቱንም እንደ ጨረሰ፣ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፣ “ጌታ ሆይ፤ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን ጸሎት እንዳስተማራቸው አንተም መጸለይን አስተምረን” አለው። እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ስትጸልዩ እንዲህ በሉ፤ “ ‘አባታችን ሆይ፤ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ የዕለት እንጀራችንን በየዕለቱ ስጠን፤ በደላችንን ይቅር በለን፤ እኛም የበደሉንን ሁሉ ይቅር ብለናልና። ወደ ፈተናም አታግባን፤ ከክፉው አድነን እንጂ።’ ” ደግሞም እንዲህ አላቸው፤ “ከእናንተ አንዱ ወዳጅ ቢኖረውና በእኩለ ሌሊት ወደ እርሱ ሄዶ፣ ‘ወዳጄ ሆይ፤ ሦስት እንጀራ አበድረኝ፤ አንድ ባልንጀራዬ ከመንገድ መጥቶብኝ የማቀርብለት ምንም ነገር የለኝምና’ ብሎ ለመነው እንበል። በቤት ውስጥ ያለውም፣ ‘አታስቸግረኝ፤ በሩ ተቈልፏል፤ ልጆቼም ዐብረውኝ ተኝተዋል፤ ከእንግዲህ ተነሥቼ ልሰጥህ አልችልም’ ይለዋልን? እላችኋለሁ፤ ወዳጁ በመሆኑ ተነሥቶ ባይሰጠው እንኳ፣ ስለ ንዝነዛው ብቻ የሚፈልገውን ሁሉ ይሰጠዋል። “ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ በሩም ይከፈትላችኋል፤ የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፤ የሚፈልግም ያገኛል፤ ለሚያንኳኳም ይከፈትለታል። “ከእናንተ መካከል አባት ሆኖ ሳለ ልጁ ዓሣ ቢለምነው እባብ የሚሰጠው ይኖራልን? ወይስ ዕንቍላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋልን? እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ፣ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታን መስጠት ካወቃችሁበት፣ በሰማይ ያለው አባት ታዲያ ለሚለምኑት መንፈስ ቅዱስን እንዴት አብልጦ አይሰጥ?” አንድ ቀን ኢየሱስ ድዳ ጋኔን ያወጣ ነበር፤ ጋኔኑም ከወጣለት በኋላ ድዳው ሰው ተናገረ፤ ሕዝቡም ተገረመ። አንዳንዶቹ ግን፣ “በአጋንንት አለቃ፣ በብዔልዜቡል፣ አጋንንትን ያወጣል” አሉ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ሊፈታተኑት ከሰማይ ምልክት እንዲያሳይ ከርሱ ይፈልጉ ነበር። ኢየሱስ ግን ሐሳባቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፤ “እርስ በርሱ የሚከፋፈል መንግሥት ሁሉ ይጠፋል፤ የሚለያይ ቤትም ይወድቃል። ሰይጣንም እርስ በርሱ ከተከፋፈለ፣ መንግሥቱ እንዴት ይጸናል? አጋንንትን በብዔልዜቡል እንደማወጣ ትናገራላችሁና። እንግዲህ እኔ አጋንንትን የማወጣው በብዔልዜቡል ከሆነ፣ ልጆቻችሁ በማን ያወጧቸው ይሆን? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል። እኔ ግን አጋንንትን የማወጣው በእግዚአብሔር ጣት ከሆነ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ እንደ መጣች ዕወቁ። “ብርቱ ሰው በሚገባ ታጥቆ ቤቱን ከጠበቀ፣ ንብረቱ በሰላም ይቀመጣል። ነገር ግን ይበልጥ ብርቱ የሆነ ሰው መጥቶ ካጠቃውና ካሸነፈው ታምኖበት የነበረውን ትጥቁን ያስፈታዋል፤ ምርኮውንም ወስዶ ለሌሎች ያካፍላል። “ከእኔ ጋራ ያልሆነ ይቃወመኛል፤ ከእኔም ጋራ የማይሰበስብ ይበትናል። “ርኩስ መንፈስ ከሰው ከወጣ በኋላ፣ ዕረፍት ፍለጋ ውሃ በሌለበት ስፍራ ይንከራተታል፤ ሳያገኝም ሲቀር፣ ‘ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ’ ይላል፤ ሲመለስም ቤቱ ጸድቶና ተዘጋጅቶ ያገኘዋል። ከዚያም በኋላ ሄዶ ሌሎች ከርሱ የከፉ ሰባት ክፉ መናፍስት ይዞ ይመጣል፤ ገብተውበትም በዚያ ይኖራሉ፤ ለዚያም ሰው ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው ሁኔታ የከፋ ይሆንበታል።” ኢየሱስ ይህን እየተናገረ እያለ፣ ከሕዝቡ መካከል አንዲት ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ፣ “የተሸከመችህ ማሕፀንና የጠባሃቸው ጡቶች ብፁዓን ናቸው” አለችው። እርሱ ግን፣ “ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚታዘዙት ናቸው” አለ።

ሉቃስ 11:1-28 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ከዚ​ህም በኋላ በአ​ን​ዲት ቦታ ጸለየ፤ ጸሎ​ቱን በጨ​ረሰ ጊዜም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ አንዱ፥ “ጌታ ሆይ፥ ዮሐ​ንስ ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ እንደ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው ጸሎት አስ​ተ​ም​ረን” አለው። እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በም​ት​ጸ​ል​ዩ​በት ጊዜ እን​ዲህ በሉ፦ በሰ​ማ​ያት የም​ት​ኖር አባ​ታ​ችን ሆይ፥ ስምህ ይቀ​ደስ፤ መን​ግ​ሥ​ትህ ትምጣ፤ ፈቃ​ድህ በሰ​ማይ እንደ ሆነ እን​ዲ​ሁም በም​ድር ይሁን። የዕ​ለት ምግ​ባ​ች​ንን በየ​ዕ​ለቱ ስጠን። እኛም የበ​ደ​ለ​ንን ሁሉ ይቅር እን​ድ​ንል በደ​ላ​ች​ንን ይቅር በለን፤ አቤቱ፥ ወደ ፈተና አታ​ግ​ባን፤ ከክፉ ሁሉ አድ​ነን እንጂ።” እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ወዳጅ ያለው ሰው ቢኖር በመ​ን​ፈቀ ሌሊ​ትም ወደ እርሱ ሄዶ እን​ዲህ ቢለው፦ ‘ወዳጄ ሆይ ሦስት እን​ጀራ አበ​ድ​ረኝ። ወዳጄ ከመ​ን​ገድ መጥ​ቶ​ብ​ኛ​ልና የማ​ቀ​ር​ብ​ለት የለ​ኝም።’ ያ ወዳ​ጁም ከው​ስጥ ሆኖ፦ ‘አት​ዘ​ብ​ዝ​በኝ፤ ደጁን አጥ​ብ​ቀን ዘግ​ተ​ናል፤ ልጆ​ችም ከእኔ ጋር በአ​ልጋ ላይ ተኝ​ተ​ዋል፤ እሰ​ጥህ ዘንድ መነ​ሣት አል​ች​ልም’ ይለ​ዋ​ልን? ወዳጁ ስለ​ሆነ ሊሰ​ጠው ባይ​ነሣ እንኳ እን​ዳ​ይ​ዘ​በ​ዝ​በው ተነ​ሥቶ የወ​ደ​ደ​ውን ያህል ይሰ​ጠ​ዋል። እኔም እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ለምኑ፥ ይሰ​ጣ​ች​ኋ​ልም፤ ፈልጉ፥ ታገ​ኛ​ላ​ች​ሁም፤ ደጅ ምቱ፥ ይከ​ፈ​ት​ላ​ች​ኋ​ልም። የሚ​ለ​ምን ሁሉ ይሰ​ጠ​ዋ​ልና፤ የሚ​ፈ​ል​ግም ያገ​ኛ​ልና፤ ደጅ ለሚ​መ​ታም ይከ​ፈ​ት​ለ​ታ​ልና። ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ልጁ ዳቦ የሚ​ለ​ም​ነው አባት ቢኖር ድን​ጋይ ይሰ​ጠ​ዋ​ልን? ዓሣ ቢለ​ም​ነ​ውስ በዓሣ ፋንታ እባ​ብን ይሰ​ጠ​ዋ​ልን? ወይስ ዕን​ቍ​ላል ቢለ​ም​ነው በዕ​ን​ቍ​ላል ፋንታ ጊንጥ ይሰ​ጠ​ዋ​ልን? እና​ንተ ክፉ​ዎች ስት​ሆኑ ለል​ጆ​ቻ​ችሁ መል​ካም ስጦ​ታን መስ​ጠ​ትን የም​ታ​ውቁ ከሆነ፥ የሰ​ማይ አባ​ታ​ች​ሁማ ለሚ​ለ​ም​ኑት መል​ካ​ሙን ሀብተ መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዴት አብ​ዝቶ ይሰ​ጣ​ቸው ይሆን?” ዲዳና ደን​ቆሮ ጋኔ​ን​ንም ያወጣ ነበር፤ ጋኔ​ኑም በወጣ ጊዜ ዲዳና ደን​ቆሮ የነ​በ​ረው ተና​ገረ፤ ሰዎ​ችም አደ​ነቁ። ነገር ግን ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው፥ “በአ​ጋ​ን​ንት አለቃ በብ​ዔል ዜቡል አጋ​ን​ን​ትን ያወ​ጣ​ቸ​ዋል” ያሉ ነበሩ፤ እር​ሱም መልሶ፥ “ሰይ​ጣን ሰይ​ጣ​ንን ማው​ጣት እን​ደ​ምን ይቻ​ለ​ዋል?” አላ​ቸው። ሌሎ​ችም ሊፈ​ት​ኑት ከእ​ርሱ ዘንድ ከሰ​ማይ ምል​ክ​ትን ይፈ​ልጉ ነበር። እርሱ ግን የሚ​ያ​ስ​ቡ​ትን ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እርስ በር​ስዋ የም​ት​ለ​ያይ መን​ግ​ሥት ሁሉ ትጠ​ፋ​ለች፤ ቤትም እርስ በርሱ ቢለ​ያይ ያ ቤት ይወ​ድ​ቃል። ሰይ​ጣ​ንስ እርስ በርሱ ከተ​ለ​ያየ መን​ግ​ሥቱ እን​ዴት ይጸ​ናል? በአ​ጋ​ን​ንት አለቃ በብ​ዔል ዜቡል አጋ​ን​ን​ትን ያወ​ጣል ትላ​ላ​ች​ሁና። እኔ በብ​ዔል ዜቡል አጋ​ን​ን​ትን የማ​ወጣ ከሆነ፥ ልጆ​ቻ​ችሁ በምን ያወ​ጡ​አ​ቸ​ዋል? ስለ​ዚህ እነ​ርሱ ይፋ​ረ​ዱ​አ​ች​ኋል። እኔ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት አጋ​ን​ን​ትን የማ​ወጣ ከሆነ እን​ግ​ዲህ አሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ወደ እና​ንተ ደር​ሳ​ለች። ኀይ​ለኛ ሰው በጦር መሣ​ሪያ ቤቱን የጠ​በቀ እንደ ሆነ ገን​ዘቡ ሁሉ ደኅና ይሆ​ናል። ከእ​ርሱ የሚ​በ​ረ​ታው ቢመ​ጣና ቢያ​ሸ​ን​ፈው ግን፥ ይታ​መ​ን​በት የነ​በ​ረ​ውን የጦር መሣ​ሪ​ያ​ውን ይገ​ፈ​ዋል፤ የማ​ረ​ከ​ው​ንና የዘ​ረ​ፈ​ውን ገን​ዘ​ቡ​ንም ይወ​ስ​ዳል። ከእኔ ጋር ያል​ሆነ ባለ​ጋ​ራዬ ነው፤ ከእኔ ጋር የማ​ይ​ሰ​በ​ስ​ብም ይበ​ት​ን​ብ​ኛል። “ክፉ ጋኔ​ንም ከሰው በወጣ ጊዜ ውኃ ወደ​ሌ​ለ​በት ምድረ በዳ ይሄ​ዳል፤ የሚ​ያ​ር​ፍ​በ​ት​ንም መኖ​ሪያ ይሻል፤ ያላ​ገኘ እንደ ሆነም ወደ ወጣ​ሁ​በት ቤቴ እመ​ለ​ሳ​ለሁ ይላል። በመ​ጣም ጊዜ ተጠ​ርጎ አጊ​ጦም ያገ​ኘ​ዋል። ከዚ​ህም በኋላ ይሄ​ድና ከእ​ርሱ የሚ​ከፉ ሌሎች ባል​ን​ጀ​ሮ​ቹን ሰባት አጋ​ን​ንት ያመ​ጣል፤ ገብ​ተ​ውም በዚያ ሰው ያድ​ሩ​በ​ታል፤ ለዚያ ሰውም ከፊ​ተ​ኛው ይልቅ የኋ​ለ​ኛው የከፋ ይሆ​ን​በ​ታል።” ከዚ​ህም በኋላ ይህን ሲና​ገር ከሕ​ዝቡ መካ​ከል አን​ዲት ሴት ድም​ፅ​ዋን አሰ​ምታ፥ “የተ​ሸ​ከ​መ​ችህ ማኅ​ፀን ብፅ​ዕት ናት፤ የጠ​ባ​ሃ​ቸው ጡቶ​ችም ብፁ​ዓት ናቸው” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “ብፁ​ዓ​ንስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰም​ተው የሚ​ጠ​ብቁ ናቸው” አላት።

ሉቃስ 11:1-28 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

አንድ ቀን ኢየሱስ በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፤ ጸሎቱንም እንደ ጨረሰ፣ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፣ “ጌታ ሆይ፤ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን ጸሎት እንዳስተማራቸው አንተም መጸለይን አስተምረን” አለው። እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ስትጸልዩ እንዲህ በሉ፤ “ ‘አባታችን ሆይ፤ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ የዕለት እንጀራችንን በየዕለቱ ስጠን፤ በደላችንን ይቅር በለን፤ እኛም የበደሉንን ሁሉ ይቅር ብለናልና። ወደ ፈተናም አታግባን፤ ከክፉው አድነን እንጂ።’ ” ደግሞም እንዲህ አላቸው፤ “ከእናንተ አንዱ ወዳጅ ቢኖረውና በእኩለ ሌሊት ወደ እርሱ ሄዶ፣ ‘ወዳጄ ሆይ፤ ሦስት እንጀራ አበድረኝ፤ አንድ ባልንጀራዬ ከመንገድ መጥቶብኝ የማቀርብለት ምንም ነገር የለኝምና’ ብሎ ለመነው እንበል። በቤት ውስጥ ያለውም፣ ‘አታስቸግረኝ፤ በሩ ተቈልፏል፤ ልጆቼም ዐብረውኝ ተኝተዋል፤ ከእንግዲህ ተነሥቼ ልሰጥህ አልችልም’ ይለዋልን? እላችኋለሁ፤ ወዳጁ በመሆኑ ተነሥቶ ባይሰጠው እንኳ፣ ስለ ንዝነዛው ብቻ የሚፈልገውን ሁሉ ይሰጠዋል። “ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ በሩም ይከፈትላችኋል፤ የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፤ የሚፈልግም ያገኛል፤ ለሚያንኳኳም ይከፈትለታል። “ከእናንተ መካከል አባት ሆኖ ሳለ ልጁ ዓሣ ቢለምነው እባብ የሚሰጠው ይኖራልን? ወይስ ዕንቍላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋልን? እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ፣ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታን መስጠት ካወቃችሁበት፣ በሰማይ ያለው አባት ታዲያ ለሚለምኑት መንፈስ ቅዱስን እንዴት አብልጦ አይሰጥ?” አንድ ቀን ኢየሱስ ድዳ ጋኔን ያወጣ ነበር፤ ጋኔኑም ከወጣለት በኋላ ድዳው ሰው ተናገረ፤ ሕዝቡም ተገረመ። አንዳንዶቹ ግን፣ “በአጋንንት አለቃ፣ በብዔልዜቡል፣ አጋንንትን ያወጣል” አሉ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ሊፈታተኑት ከሰማይ ምልክት እንዲያሳይ ከርሱ ይፈልጉ ነበር። ኢየሱስ ግን ሐሳባቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፤ “እርስ በርሱ የሚከፋፈል መንግሥት ሁሉ ይጠፋል፤ የሚለያይ ቤትም ይወድቃል። ሰይጣንም እርስ በርሱ ከተከፋፈለ፣ መንግሥቱ እንዴት ይጸናል? አጋንንትን በብዔልዜቡል እንደማወጣ ትናገራላችሁና። እንግዲህ እኔ አጋንንትን የማወጣው በብዔልዜቡል ከሆነ፣ ልጆቻችሁ በማን ያወጧቸው ይሆን? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል። እኔ ግን አጋንንትን የማወጣው በእግዚአብሔር ጣት ከሆነ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ እንደ መጣች ዕወቁ። “ብርቱ ሰው በሚገባ ታጥቆ ቤቱን ከጠበቀ፣ ንብረቱ በሰላም ይቀመጣል። ነገር ግን ይበልጥ ብርቱ የሆነ ሰው መጥቶ ካጠቃውና ካሸነፈው ታምኖበት የነበረውን ትጥቁን ያስፈታዋል፤ ምርኮውንም ወስዶ ለሌሎች ያካፍላል። “ከእኔ ጋራ ያልሆነ ይቃወመኛል፤ ከእኔም ጋራ የማይሰበስብ ይበትናል። “ርኩስ መንፈስ ከሰው ከወጣ በኋላ፣ ዕረፍት ፍለጋ ውሃ በሌለበት ስፍራ ይንከራተታል፤ ሳያገኝም ሲቀር፣ ‘ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ’ ይላል፤ ሲመለስም ቤቱ ጸድቶና ተዘጋጅቶ ያገኘዋል። ከዚያም በኋላ ሄዶ ሌሎች ከርሱ የከፉ ሰባት ክፉ መናፍስት ይዞ ይመጣል፤ ገብተውበትም በዚያ ይኖራሉ፤ ለዚያም ሰው ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው ሁኔታ የከፋ ይሆንበታል።” ኢየሱስ ይህን እየተናገረ እያለ፣ ከሕዝቡ መካከል አንዲት ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ፣ “የተሸከመችህ ማሕፀንና የጠባሃቸው ጡቶች ብፁዓን ናቸው” አለችው። እርሱ ግን፣ “ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚታዘዙት ናቸው” አለ።

ሉቃስ 11:1-28 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እርሱም በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፥ በጨረሰም ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፦ ጌታ ሆይ፥ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እንጸልይ ዘንድ አስተምረን አለው። አላቸውም፦ ስትጸልዩ እንዲህ በሉ፦ በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፤ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤ የዕለት እንጀራችንን ዕለት ዕለት ስጠን፤ ኃጢአታችንንም ይቅር በለን፥ እኛ ደግሞ የበደሉንን ሁሉ ይቅር ብለናልና፤ ከክፉ አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን። እንዲሁም አላቸው፦ ከእናንተ ማናቸውም ወዳጅ አለው፥ በእኩል ሌሊትስ ወደ እርሱ ሄዶ፦ ወዳጄ ሆይ፥ ሦስት እንጀራ አበድረኝ፥ አንድ ወዳጄ ከመንገድ ወደ እኔ መጥቶ የማቀርብለት የለኝምና ይላልን? ያም ከውስጥ መልሶ፦ አታድክመኝ፤ አሁን ደጁ ተቈልፎአል ልጆቼም ከእኔ ጋር በአልጋ ላይ አሉ፤ ተነሥቼ ልሰጥህ አልችልም ይላልን? እላችኋለሁ፥ ወዳጅ ስለ ሆነ ተነሥቶ ባይሰጠው እንኳ፥ ስለ ንዝነዛው ተነስቶ የሚፈልገውን ሁሉ ይሰጠዋል። እኔም እላችኋለሁ፦ ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፍትላችሁማል። የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልግም ያገኛል፥ መዝጊያውንም ለሚያንኳኳው ይከፈትለታል። አባት ከሆናችሁ ከእናንተ ከማንኛችሁም ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ እርሱም ድንጋይ ይሰጠዋልን? ዓሣ ደግሞ ቢለምነው በዓሣ ፋንታ እባብ ይሰጠዋልን? ወይስ እንቍላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማይ ያለው አባት ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መንፈስ ቅዱስን ይሰጣቸው? ዲዳውንም ጋኔን ያወጣ ነበር፤ ጋኔኑም ከወጣ በኋላ ዲዳው ተናገረ ሕዝቡም ተደነቁ፤ ነገር ግን ከእነርሱ አንዳንዱ፦ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል አሉ። ሌሎችም ሲፈትኑት ከሰማይ ምልክት ከእርሱ ይፈልጉ ነበር። እርሱ ግን አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው፦ እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ሁሉ ትጠፋለች፤ ቤትም በቤት ላይ ይወድቃል። እኔ አጋንንትን በብዔል ዜቡል እንዳወጣ ትላላችሁና ሰይጣን ደግሞ እርስ በርሱ ከተለያየ መንግሥቱ እንዴት ትቆማለች? እኔስ በብዔል ዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ ልጆቻችሁ በማን ያወጡአቸዋል? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል። እኔ ግን በእግዚአብሔር ጣት አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች። ኃይለኛ ሰው ጋሻና ጦር ይዞ የራሱን ግቢ ቢጠብቅ፥ ያለው ገንዘቡ በሰላም ይሆናል፤ ከእርሱ ይልቅ የሚበረታ ወጥቶ ሲያሸንፈው ግን፥ ታምኖበት የነበረውን ጋሻና ጦር ይወስድበታል ምርኮውንም ያካፍላል። ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፥ ከእኔ ጋርም የማያከማች ይበትናል። ርኵስ መንፈስ ከሰው በወጣ ጊዜ ዕረፍትን እየፈለገ ውኃ በሌለበት ቦታ ያልፋል፤ ባያገኝም፦ ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ ይላል፤ ሲመጣም ተጠርጎ አጊጦም ያገኘዋል። ከዚያ ወዲያ ይሄድና ከእርሱ የከፉትን ሌሎችን ሰባት አጋንንት ከእርሱ ጋር ይይዛል፥ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ፤ ለዚያም ሰው ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው ይብስበታል። ይህንም ሲናገር፥ ከሕዝቡ አንዲት ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ፦ የተሸከመችህ ማኅፀንና የጠባሃቸው ጡቶች ብፁዓን ናቸው አለችው። እርሱ ግን፦ አዎን፥ ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው አለ።

ሉቃስ 11:1-28 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

አንድ ቀን ኢየሱስ በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፤ ጸሎቱንም ባበቃ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፥ “ጌታ ሆይ! ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን ጸሎት እንዳስተማራቸው፥ አንተም እኛን መጸለይ አስተምረን!” አለው። ኢየሱስም “ስትጸልዩ እንዲህ በሉ አላቸው፤ ‘[በሰማይ የምትኖር] አባታችን ሆይ! ስምህ ይቀደስ! መንግሥትህ ትምጣ! የዕለት እንጀራችንን በየቀኑ ስጠን! እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል፥ በደላችንን ይቅር በልልን፤ ወደ ፈተናም አታግባን’ [ከክፉ አድነን እንጂ።]” ቀጥሎም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “ለምሳሌ ከእናንተ አንዱ ወዳጅ ኖሮት፥ ያ ወዳጁ በእኩለ ሌሊት ወደዚያ ወደ ወዳጁ ቤት ሄዶ፥ ‘ወዳጄ ሆይ፥ እባክህ ሦስት እንጀራ አበድረኝ፤ ወዳጄ የሆነ አንድ ሰው ከሩቅ መንገድ መጥቶብኝ የማቀርብለት ምንም ምግብ የለኝም!’ ቢለው ታዲያ፥ ያ ወዳጁ ከውስጥ ሆኖ፥ ‘እባክህ አታስቸግረኝ! በሩ ተቈልፎአል፤ ልጆቼም ከእኔ ጋር በአልጋ ላይ ተኝተዋል፤ ስለዚህ ተነሥቼ የፈለግኸውን እንጀራ ልሰጥህ አልችልም፤’ ይለዋልን? ምንም እንኳ ስለ ወዳጅነቱ ተነሥቶ ሊሰጠው ባይፈልግ ስለ ነዘነዘው ተነሥቶ የሚያስፈልገውን ሁሉ ይሰጠዋል እላችኋለሁ። “ስለዚህ እኔም እናንተን የምላችሁ ይህን ነው፤ ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ መዝጊያ አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤ የሚለምን ሁሉ ይቀበላል፤ የሚፈልግም ያገኛል፤ መዝጊያ ለሚያንኳኳም ይከፈትለታል። ከእናንተስ አባት ሆኖ፥ ልጁ [ዳቦ ቢለምነው ድንጋይ የሚሰጠው ማን ነው?] ዓሣስ ቢለምነው በዓሣ ፈንታ እባብ ይሰጠዋልን? ወይስ ዕንቊላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋልን? እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ነገር መስጠትን ካወቃችሁ በሰማይ የሚኖር አባታችሁማ ለሚለምኑት መንፈስ ቅዱስን እንዴት አብልጦ አይሰጣቸውም!” አንድ ቀን ኢየሱስ የማያናግር ጋኔን ከአንድ ድዳ ሰው ያስወጣ ነበር፤ ጋኔኑም በወጣ ጊዜ ድዳው ሰው መናገር ጀመረ፤ ሕዝቡም በዚህ ነገር እጅግ ተደነቁ። አንዳንዶች ግን “አጋንንትን የሚያስወጣው የአጋንንት አለቃ በሆነው በብዔልዜቡል ነው፤” አሉ። ሌሎች ደግሞ ሊፈትኑት ፈልገው ከሰማይ አንድ ምልክት እንዲያሳያቸው ጠየቁት። ኢየሱስ ግን ሐሳባቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፦ “አንድ መንግሥት ተከፋፍሎ እርስ በርስ የሚለያይ ከሆነ፥ ያ መንግሥት ይጠፋል፤ እንዲሁም አንድ ቤተሰብ እርስ በርሱ ከተለያየ ይወድቃል። ስለዚህ ሰይጣን እርስ በርሱ የሚለያይ ከሆነ የእርሱ መንግሥት እንዴት ጸንቶ መቆም ይችላል? እናንተ ግን ‘እርሱ አጋንንትን የሚያስወጣ በብዔልዜቡል ነው፤’ ትሉኛላችሁ። ታዲያ፥ እኔ አጋንንትን በብዔልዜቡል የማስወጣ ከሆንኩ ልጆቻችሁስ በማን ያስወጡአቸዋል? ስለዚህ የገዛ ልጆቻችሁ እንኳ ይፈርዱባችኋል። እንግዲህ እኔ አጋንንትን በእግዚአብሔር ኀይል የማስወጣ ከሆነ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ መምጣትዋን ዕወቁ። “አንድ ኀይለኛ ሰው የጦር መሣሪያ ይዞ ቤቱን የሚጠብቅ ከሆነ ንብረቱ በደንብ ይጠበቅለታል፤ ነገር ግን ከእርሱ የበለጠ ኀይለኛ ሰው መጥቶ ካሸነፈው የተማመነበትን የጦር መሣሪያ ይወስድበታል ንብረቱንም ሁሉ ዘርፎ ያካፍላል። “ከእኔ ጋር ያልሆነ ሁሉ እኔን ይቃወማል፤ ከእኔም ጋር የማይሰበስብ ይበትናል። “ርኩስ መንፈስ ከሰው ውስጥ በወጣ ጊዜ የሚያርፍበት ቦታ በመፈለግ ውሃ በሌለበት በደረቅ ምድር ሁሉ ይዞራል፤ የሚያርፍበት ቦታ ካላገኘ ግን ‘ወደወጣሁበት ቤቴ ተመልሼ ልሂድ’ ይላል። ተመልሶ ሲመጣ ጸድቶና ተዘጋጅቶ ያገኘዋል። ከዚህ በኋላ ሄዶ ከእርሱ ይብስ የከፉ ሌሎች ሰባት አጋንንት ይዞ ይመጣል፤ ቀድሞ እርሱ በነበረበት ቤትም ገብተው በዚያ ይኖራሉ፤ የዚያም ሰው የመጨረሻ ሁኔታ ከመጀመሪያው ይልቅ የባሰ ይሆናል።” ኢየሱስ ይህን በሚናገርበት ጊዜ አንዲት ሴት ከሕዝቡ መካከል ድምፅዋን ከፍ አድርጋ “አንተን ወልዳ ያጠባች እናት የተባረከች ናት፤” አለች። ኢየሱስ ግን “የተባረኩስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው በሥራ ላይ የሚያውሉት ናቸው፤” አላት።

ሉቃስ 11:1-28 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

እርሱም በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፤ በጨረሰም ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፦ “ጌታ ሆይ! ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እንዲሁ መጸለይን አስተምረን፤” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “በማናቸውም ጊዜ ስትጸልዩ እንዲህ በሉ፦ ‘በሰማያት የምትኖር አባት ሆይ! ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤ የዕለት እንጀራችንን ዕለት ዕለት ስጠን፤ ኀጢአታችንንም ይቅር በለን፤ እኛ ደግሞ የበደሉንን ሁሉ ይቅር እንላለንና፤ ወደ ፈተናም አታግባን።’ ” እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “ከእናንተ ማን ይሆን ወዳጅ ኖሮት፥ በእኩለ ሌሊት ወደ እርሱ ሄዶ እንዲህ የሚለው፦ ‘ወዳጄ ሆይ! ሦስት እንጀራ አበድረኝ፤ አንድ ወዳጄ ከመንገድ ወደ እኔ መጥቶ የማቀርብለት ምንም የለኝምና’፤ ያም ከውስጥ መልሶ፦ ‘አታስቸግረኝ፤ አሁን ደጁ ተቈልፎአል ልጆቼም ከእኔ ጋር በአልጋ ላይ ናቸው፤ ተነሥቼ ልሰጥህ አልችልም፤’? እላችኋለሁ፤ ወዳጁ ስለ ሆነ እንኳ ተነሥቶ ባይሰጠው፥ ስለ ንዝነዛው ግን ተነሥቶ የሚፈልገውን ያህል ይሰጠዋል። እኔም እላችኋለሁ፤ ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤ የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፤ የሚፈልግም ያገኛል፤ መዝጊያውንም ለሚያንኳኳው ይከፈትለታል። አባት ከሆናችሁ ከእናንተ ከማንኛችሁም ልጁ ዓሣ ቢለምነው፥ በዓሣ ፋንታ እባብ ይሰጠዋልን? ወይስ እንቁላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋልን? እንግዲያውስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታን መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማይ ያለው አባት ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መንፈስ ቅዱስን ይሰጣቸው!” መናገርም የተሳነውን ጋኔን ያወጣ ነበር፤ ጋኔኑም ከወጣ በኋላ መናገር የተሳነው ሰው ተናገረ፥ ሕዝቡም ተደነቁ፤ ከእነርሱ ዘንድ አንዳንዶች ግን፦ “በብዔልዜቡል በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል፤” አሉ። ሌሎችም ሊፈትኑት ከሰማይ ምልክት ከእርሱ ይፈልጉ ነበር። ኢየሱስ ግን አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው፦ “እርስ በርሱ የተለያየ መንግሥት ሁሉ ይጠፋል፤ ቤትም በቤት ላይ ይወድቃል። ሰይጣንም ደግሞ እርስ በርሱ ቢለያይ መንግሥቱ እንዴት ይቆማል? እኔ አጋንንትን በብዔልዜቡል እንደማወጣ እናንተ ብላችኋልና፤ እኔስ በብዔልዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆንኩ፥ ልጆቻችሁ በማን ያስወጣሉ? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል። እኔ ግን በእግዚአብሔር ጣት አጋንንትን የማወጣ ከሆንኩ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ መጥቷል። በማናቸውም ጊዜ ኀይለኛ ሰው በሚገባ የጦር ዕቃውን ታጥቆ የራሱን ግቢ ቢጠብቅ፥ ያለው ንብረቱ በሰላም የተጠበቀ ይሆናል፤ ከእርሱ ይልቅ የሚበረታ አደጋ ጥሎበት ካሸነፈው ግን፥ ታምኖበት የነበረውን የጦር ዕውቃን ይወስድበታል፤ ምርኮውንም ያካፍላል። ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፤ ከእኔ ጋርም የማይሰበስብ ይበትናል። “ርኩስ መንፈስ ከሰው በወጣ ጊዜ ዕረፍትን ፈልጎ ውሃ በሌለበት ቦታ ያልፋል፤ ባለማግኘቱ ግን፦ ‘ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ፤’ ይላል፤ ሲመጣም ተጠርጎና ተስተካክሎ ያገኘዋል። በዚያም ጊዜ ሄዶ ከእርሱ የባሱ ክፉ ሌሎች ሰባት መናፍስትን ከእርሱ ጋር ያመጣል፤ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ፤ የዚያም ሰው ሁኔታ ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው የባሰ ይሆናል።” ኢየሱስም ይህንን በመናገር ላይ ሳለ፥ ከሕዝቡ አንዲት ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ፦ “የተሸከመችህ ማኅፀንና የጠባሃቸው ጡቶች ብፁዓን ናቸው፤” አለችው። እርሱ ግን፦ “በእርግጥ ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው፤” አለ።