የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኢያሱ 2:1-14

ኢያሱ 2:1-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የነ​ዌም ልጅ ኢያሱ፥ “ውጡና ምድ​ሪ​ቱን ኢያ​ሪ​ኮን እዩ” ብሎ ከሰ​ጢም ሁለት ጐል​ማ​ሶች ሰላ​ዮ​ችን በስ​ውር ላከ። እነ​ዚ​ያም ሁለት ጐል​ማ​ሶች ሄዱ፤ ወደ ኢያ​ሪ​ኮም ደረሱ፤ ረዓብ ወደ​ሚ​ሉ​አ​ትም ዘማ ቤት ገቡ፤ በዚ​ያም ዐደሩ። ለኢ​ያ​ሪ​ኮም ንጉሥ፥ “እነሆ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሰላ​ዮች ሀገ​ራ​ች​ንን ሊሰ​ልሉ ወደ​ዚህ በሌ​ሊት ገቡ” ብለው ነገ​ሩት። የኢ​ያ​ሪ​ኮም ንጉሥ፥ “ሀገ​ራ​ች​ንን ሁሉ ሊሰ​ልሉ መጥ​ተ​ዋ​ልና ወደ አንቺ የመ​ጡ​ትን በዚ​ችም ሌሊት ወደ ቤትሽ የገ​ቡ​ትን ሰዎች አውጪ በሉ​አት” ብሎ ወደ ረዓብ ላከ። ሴቲ​ቱም ሁለ​ቱን ሰዎች ወስዳ ሸሸ​ገ​ቻ​ቸው፤ እር​ስ​ዋም፥ “አዎን፥ ሰዎቹ ወደ እኔ መጡ፤ ከወ​ዴት እንደ ሆኑ ግን አላ​ወ​ቅ​ሁም፤ በሩም ሲዘጋ፥ ሲጨ​ል​ምም ሰዎቹ ወጡ፤ ወዴት እንደ ሄዱ አላ​ው​ቅም፤ ፈጥ​ና​ችሁ ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው፤ ምን​አ​ል​ባት ታገ​ኙ​አ​ቸው ይሆ​ናል” አለ​ቻ​ቸው። እር​ስዋ ግን ወደ ሰገ​ነቱ አው​ጥታ በተ​ከ​መረ እን​ጨት መካ​ከል በቀ​ር​ከሃ ጠቅ​ልላ ደብ​ቃ​ቸው ነበር። ሰዎ​ቹም ወደ ዮር​ዳ​ኖስ መሻ​ገ​ሪያ በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው፤ በሩም ተቈ​ለፈ። እነ​ዚ​ህም ሳይ​ተኙ ሴቲቱ ወደ እነ​ርሱ ወደ ሰገ​ነቱ ወጣች። ሰዎ​ቹ​ንም እን​ዲህ አለ​ቻ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ሪ​ቱን አሳ​ልፎ እንደ ሰጣ​ችሁ ዐወ​ቅሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እና​ን​ተን መፍ​ራ​ት​ን በ​ላ​ያ​ችን አም​ጥ​ት​ዋ​ልና፥ በም​ድ​ሪ​ቱም የሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ከፊ​ታ​ችሁ የተ​ነሣ ቀል​ጠ​ዋ​ልና። ከግ​ብፅ ምድር በወ​ጣ​ችሁ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኤ​ር​ት​ራን ባሕር በፊ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ደ​ረቀ፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ በነ​በ​ሩት፥ እና​ን​ተም ፈጽ​ማ​ችሁ ባጠ​ፋ​ች​ኋ​ቸው በሁ​ለቱ በአ​ሞ​ራ​ው​ያን ነገ​ሥ​ታት፥ በሴ​ዎ​ንና በዐግ ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ትን ሰም​ተ​ናል። ይህ​ንም ነገር ሰም​ተን በል​ባ​ችን ደነ​ገ​ጥን፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላይ በሰ​ማይ፥ በታ​ችም በም​ድር እርሱ አም​ላክ ነውና ከእ​ና​ንተ የተ​ነሣ ከእኛ የአ​ን​ዱም እን​ኳን ነፍስ አል​ቀ​ረም። አሁ​ንም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማሉ​ልኝ፤ እኔ ለእ​ና​ንተ ቸር​ነት እንደ አደ​ረ​ግሁ እና​ንተ ደግሞ ለአ​ባቴ ቤት ቸር​ነት እን​ድ​ታ​ደ​ርጉ፥ በእ​ው​ነት ምል​ክት ስጡኝ። የአ​ባ​ቴን ቤት፥ እና​ቴ​ንም፥ ወን​ድ​ሞ​ቼ​ንና ቤቴ​ንም ሁሉ፥ ያላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አድኑ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ን​ንም ከሞት አድኑ።” ሰዎ​ቹም፥ “ሕይ​ወ​ታ​ች​ንን ስለ እና​ንተ አሳ​ል​ፈን ለሞት እን​ሰ​ጣ​ለን” አሉ፤ እር​ስ​ዋም አለች፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ሪ​ቱን በሰ​ጣ​ችሁ ጊዜ ቸር​ነ​ት​ንና ጽድ​ቅን ታደ​ር​ጉ​ል​ና​ላ​ችሁ።” ሰዎ​ቹም፥ “ይህን ነገ​ራ​ች​ንን ባት​ገ​ልጪ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሀገ​ራ​ች​ሁን በእ​ው​ነት አሳ​ልፎ ከሰ​ጠን ከአ​ንቺ ጋር ቸር​ነ​ትን እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አሏት።

ኢያሱ 2:1-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከዚያም የነዌ ልጅ ኢያሱ፣ “ሄዳችሁ ምድሪቱን፣ በተለይም የኢያሪኮን ከተማ ሰልሉ” ብሎ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር ላከ፤ ሰዎቹም ሄደው ረዓብ ከተባለች ጋለሞታ ቤት ገቡ፤ በዚያም ዐደሩ። ለኢያሪኮም ንጉሥ፣ “እነሆ፤ ምድሪቱን ሊሰልሉ ጥቂት እስራኤላውያን በሌሊት ወደዚህ መጥተዋል” ተብሎ ተነገረው። የኢያሪኮም ንጉሥ፣ “ወደ አንቺ መጥተው ወደ ቤትሽ የገቡት ሰዎች ምድሪቱን በሙሉ ለመሰለል ስለሆነ፣ እንድታስወጪአቸው” የሚል መልእክት ወደ ረዓብ ላከ። ሴቲቱ ግን ሁለቱን ሰዎች ተቀብላ ሸሽጋቸው ስለ ነበር እንዲህ አለች፤ “በርግጥ ሰዎቹ ወደ እኔ መጥተዋል፤ ነገር ግን ከወዴት እንደ መጡ አላውቅም። ጨልሞ የቅጥሩ በር ከመዘጋቱ በፊት ወጥተው ሄደዋል፤ በየት በኩል እንደ ሄዱ ግን እኔ አላውቅም፤ ልትደርሱባቸው ትችላላችሁና ፈጥናችሁ ተከታተሏቸው።” ነገር ግን ሰዎቹን ጣራ ላይ አውጥታ በረበረበችው የተልባ እግር ውስጥ ደብቃቸው ነበር። ሰዎቹም ሰላዮቹን በመከታተል ወደ ዮርዳኖስ መሻገሪያ የሚወስደውን መንገድ ይዘው ሄዱ፤ አሳዳጆቹ ወጥተው እንደ ሄዱም የቅጥሩ በር ተዘጋ። ሰላዮቹ ከመተኛታቸው በፊት ሴቲቱ ወደ ጣራው ወጥታ፣ እንዲህ አለቻቸው፤ “እግዚአብሔር ይህችን ምድር እንደ ሰጣችሁ፣ እናንተንም መፍራት እንዳደረብን፣ የዚህች አገር ነዋሪዎች ሁሉ ልባቸው በፊታችሁ መቅለጡንም ዐውቃለሁ። ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ እግዚአብሔር ቀይ ባሕርን በፊታችሁ እንዴት እንዳደረቀ፣ እናንተም ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ፈጽሞ ያጠፋችኋቸውን ሁለቱን የአሞራውያን ነገሥታት፣ ሴዎንንና ዐግን ምን እንዳደረጋችኋቸው ሰምተናል። ይህን በሰማን ጊዜ ልባችን ቀለጠ፤ እናንተን ከመፍራት የተነሣም ያልተሸበረ ሰው አልነበረም፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ በላይም በሰማይ፣ በታችም በምድር እርሱ አምላክ ነውና። እንግዲህ እኔ በጎነትን እንዳሳየኋችሁ ሁሉ፣ እናንተም በጎነትን ለአባቴ ቤት እንድታሳዩ በእግዚአብሔር ማሉልኝ፤ መተማመኛ የሚሆን ምልክትም ስጡኝ፤ የአባቴንና የእናቴን፣ የወንድሞቼንና የእኅቶቼን እንዲሁም የእነርሱ የሆነውን ነፍስ ሁሉ እንድታተርፉልኝ፤ ከሞትም አድኑን።” ሰዎቹም፣ “የእናንተን ሞት ለእኛ ያድርገው! እኛ የምናደርገውን ሁሉ ካልተናገራችሁ፣ እግዚአብሔር ምድሪቱን በሚሰጠን ጊዜ፣ በጎነትና ታማኝነት እናሳይሻለን” አሏት።

ኢያሱ 2:1-14 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የነዌም ልጅ ኢያሱ፦ ሄዳችሁ ምድሪቱንና ኢያሪኮን እዩ ብሎ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር ላከ። ሄዱም፥ ረዓብም ወደሚሉአት ጋለሞታ ቤት ገቡ፥ በዚያም አደሩ። የኢያሪኮም ንጉሥ፦ እነሆ፥ ሰዎች ከእስራኤል ልጆች አገሩን ሊሰልሉ ወደዚህ በሌሊት ገቡ ሲባል ወሬ ሰማ። የኢያሪኮም ንጉሥ፦ አገሩን ሁሉ ሊሰልሉ መጥተዋልና ወደ አንቺ የመጡትን ወደ ቤትሽም የገቡትን ሰዎች አውጪ ብሎ ወደ ረዓብ ላከ። ሴቲቱም ሁለቱን ሰዎች ወስዳ ሸሸገቻቸው፥ እርስዋም፦ አዎን፥ ሰዎቹ ወደ እኔ መጡ፥ ከወዴት እንደሆኑ ግን አላወቅሁም፥ በሩም ሲዘጋ ሲጨልምም ሰዎቹ ወጡ፥ ወዴት እንደ ሄዱ አላውቅም፥ ፈጥናችሁ አሳድዱአቸው፥ ታገኙአቸውማላችሁ አለች። እርስዋ ግን ወደ ሰገነቱ አውጥታቸው ነበር፥ በዚያም በረበረበችው በተልባ እግር ውስጥ ሸሽጋቸው ነበር። ሰዎቹም ወደ ዮርዳኖስ መሻገሪያ በሚወስደው መንገድ አሳደዱአቸው፥ አሳዳጆችም ከወጡ በኋላ በሩ ተቈለፈ። እነዚህም ሳይተኙ ሴቲቱ ወደ እነርሱ ወደ ሰገነቱ ወጣች። ሰዎቹንም እንዲህ አለቻቸው፦ እግዚአብሔር ምድሪቱን እንደ ሰጣችሁ፥ እናንተንም መፍራት በላያችን እንደ ወደቀ፥ በምድሪቱም የሚኖሩት ሁሉ ከፊታችሁ እንደ ቀለጡ አወቅሁ። ከግብጽ ምድር በወጣችሁ ጊዜ እግዚአብሔር የኤርትራን ባሕር በፊታችሁ እንዳደረቀ፥ በዮርዳኖስም ማዶ በነበሩት እናንተም ፈጽማችሁ ባጠፋችኋቸው በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት፥ በሴዎንና በዐግ ያደረጋችሁትን ሰምተናል። ይህንም ነገር ሰምተን ልባችን ቀለጠ፥ አምላካችሁም እግዚአብሔር በላይ በሰማይ በታችም በምድር እርሱ አምላክ ነውና ከእናንተ የተነሣ ከዚያ ወዲያ ለማንም ነፍስ አልቀረለትም። አሁንም፥ እባካችሁ፥ በእግዚአብሔር ማሉልኝ፥ በእውነትም ምልክት ስጡኝ፥ እኔ ለእናንተ ቸርነት እንደ ሠራሁ እናንተ ደግሞ ለአባቴ ቤት ቸርነት እንድትሠሩ፥ አባቴንና እናቴንም ወንድሞቼንና እኅቶቼንም ያላቸውንም ሁሉ እንድታድኑ፥ ሰውነታችንንም ከሞት እንድታድኑ። ሰዎቹም፦ ይህን ነገራችንን ባትገልጪ ነፍሳችን በነፍሳችሁ ፋንታ ለሞት ይሆናል፥ እግዚአብሔርም ምድሪቱን በሰጠን ጊዜ ከአንቺ ጋር ቸርነትንና እውነትን እናደርጋለን አሉአት።

ኢያሱ 2:1-14 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ከዚህ በኋላ የነዌ ልጅ ኢያሱ ከሺጢም ሰፈር ሁለት ሰላዮችን ላከ፤ እነርሱም የከነዓንን ምድር በተለይም የኢያሪኮን ከተማ በምሥጢር ሰልለው እንዲመለሱ አዘዛቸው፤ ወደ ከተማይቱ በመጡ ጊዜ “ረዓብ” ተብላ ወደምትጠራ ወደ አንዲት ሴትኛ ዐዳሪ ቤት ገብተው ዐደሩ። “አገሪቱን ለመሰለል ከእስራኤላውያን መካከል ዛሬ ማታ ወደዚህ መጥተዋል” ተብሎ ለኢያሪኮ ንጉሥ ተነገረው። ከዚህ በኋላ የኢያሪኮ ንጉሥ “ምድሪቱን ሊሰልሉ የመጡ ስለ ሆኑ ወደ ቤትሽ የገቡትን ሰዎች አውጥተሽ አስረክቢ!” ብሎ ወደ ረዓብ ትእዛዝ ላከ። ሴቲቱም ሁለቱን ሰዎች ወስዳ ሸሸገቻቸው፤ እርስዋም፦ “አዎን፥ ሰዎቹ ወደ እኔ መጡ፤ ከወዴት እንደ ሆኑ ግን አላውቅም፤ ጊዜው መሽቶ በመጨለሙ በሩ ሲዘጋ ሰዎቹ ወጥተው ሄዱ፤ ወዴት እንደ ሄዱ ግን አላውቅም፤ ፈጥናችሁ ብታሳድዱአቸው ትደርሱባቸዋላችሁ” አለች። እርስዋ ግን ወደ ሰገነቱ አውጥታ በዚያ በረበረበችው በተልባ እግር ውስጥ ሸሽጋቸው ነበር። የንጉሡም መልእክተኞች ከከተማይቱ ወጥተው ሄዱ፤ የቅጽር በሩም ተዘጋ፤ መልእክተኞቹም ሰላዮችን በመፈለግ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግሮ እስከሚያልፈው ስፍራ ድረስ ሄዱ። ረዓብም ከመተኛታቸው በፊት ወዳሉበት የቤት ጣራ ወጥታ፥ እንዲህ አለቻቸው፦ “የሀገሪቱ ኗሪዎች በሙሉ በፍርሃት ተውጠው ልባቸው ቀለጠ፤ በሁላችንም ላይ ፍርሀት ስላደረብን እግዚአብሔር ምድሪቱን ለእናንተ እንደ ሰጠ ዐውቃለሁ፤ ግብጽን ለቃችሁ በወጣችሁ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ቀይ ባሕርን በፊታችሁ እንዴት እንዳደረቀ ሰምተናል፤ ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ የነበሩትን ሁለቱን የአሞራውያን ነገሥታት ሲሖንንና ዖግን እንዴት እንደ ገደላችሁም ሰምተናል። ስለዚህም ይህን ሁሉ ነገር በሰማን ጊዜ በፍርሃት ልባችን ቀለጠ፤ ወኔአችን ሁሉ ጠፋ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር በእርግጥ የሰማይና የምድር አምላክ ነው። አሁንም እኔ ለእናንተ መልካም ነገር እንዳደረግሁላችሁ ሁሉ ቤተሰቤን ከጥፋት በማትረፍ መልካም ነገር ታደርጉልኝ ዘንድ ማሉልኝ፤ ለዚህም መተማመኛ የሚሆን ምልክት ስጡኝ። አባቴንና እናቴን፥ ወንድሞቼን፥ እኅቶቼንና የእነርሱን ቤተሰቦች ሁሉ ከሞት ለማዳን ቃል ግቡልኝ!” ሰዎቹም እንዲህ አሉአት፤ “እኛ በገባንልሽ ቃል መሠረት ባንፈጽም እግዚአብሔር በሞት ይቅጣን! እኛ ያደረግነውን ሁሉ ለማንም ባትነግሪ፥ እግዚአብሔር ይህቺን ምድር ለእኛ አሳልፎ በሚሰጠን ጊዜ ለአንቺ መልካም ነገር ለማድረግ ቃል እንገባለን።”

ኢያሱ 2:1-14 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የነዌም ልጅ ኢያሱ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር እንዲህ ብሎ ላከ፦ “ሄዱ፥ ምድሪቱንና ኢያሪኮን እዩ።” ሄዱም፤ ረዓብም ወደሚሉአት አመንዝራ ቤት ገቡ፥ በዚያም አደሩ። ለኢያሪኮም ንጉሥ እንዲህ ተብሎ ተነገረው፦ “እነሆ፥ ሰዎች ከእስራኤል ልጆች አገሩን ሊሰልሉ ወደዚህ በሌሊት ገቡ።” የኢያሪኮም ንጉሥ እንዲህ ብሎ ወደ ረዓብ ላከ፦ “አገሩን ሁሉ ሊሰልሉ መጥተዋልና ወደ አንቺ የመጡትን ወደ ቤትሽም የገቡትን ሰዎች አውጪ።” ሴቲቱም ሁለቱን ሰዎች ወስዳ ሸሸገቻቸው፤ እርሷም እንዲህ አለች፦ “አዎን፥ ሰዎቹ ወደ እኔ መጥተዋል፥ ከወዴት እንደ ሆኑ ግን አላወቅሁም፤ በሩ በሚዘጋበት ጊዜ ሲመሻሽ ሰዎቹ ወጥተው ሄደዋል፤ ወዴት እንደ ሄዱ ግን አላውቅም፤ ፈጥናችሁ አሳድዱአቸው፥ ትደርሱባቸዋላችሁ።” እርሷ ግን ወደ ሰገነቱ አውጥታቸው ነበር፤ በዚያም በረበረበችው በተልባ እግር ውስጥ ሸሽጋቸው ነበር። ሰዎቹም ወደ ዮርዳኖስ መሻገሪያ እስከሚወስደው መንገድ ድረስ አሳደዱአቸው፤ አሳዳጆችም ከወጡ በኋላ በሩ ተዘጋ። እነርሱም ከመተኛታቸው በፊት ሴቲቱ ወደ እነርሱ ወደ ሰገነቱ ወጣች። ሰዎቹንም እንዲህ አለቻቸው፦ “ጌታ ምድሪቱን እንደ ሰጣችሁ፥ ከእናንተም የተነሣ በፍርሃት መዋጣችንን፥ በምድሪቱም የሚኖሩት ሁሉ ከፊታችሁ በፍርሃት እንደ ቀለጡ አወቅሁ። ከግብጽ ምድር በወጣችሁ ጊዜ ጌታ የኤርትራን ባሕር በፊታችሁ እንዳደረቀ፥ በዮርዳኖስም ማዶ በነበሩት እናንተም ፈጽማችሁ ባጠፋችኋቸው በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት፥ በሴዎንና በዐግ ያደረጋችሁትን ሰምተናል። ይህንንም ነገር ሰምተን ልባችን ቀለጠ፤ ጌታ አምላካችሁም በላይ በሰማይ በታችም በምድር እርሱ አምላክ ነውና ከእናንተ የተነሣ ከእግዲህ ወዲያ ሰው ሁሉ ሐሞተ ቢስ ሆኖአል። አሁንም፥ እባካችሁ፥ በጌታ ማሉልኝ፥ በእውነትም ምልክት ስጡኝ፥ እኔ ለእናንተ ቸርነት እንደሠራሁ እናንተ ደግሞ ለአባቴ ቤት ቸርነት ሥሩ፥ አባቴንና እናቴንም ወንድሞቼንና እኅቶቼንም ያላቸውንም ሁሉ አድኑ፥ ነፍሳችንንም ከሞት ታደጉ።” ሰዎቹም እንዲህ አሉአት፦ “ይህን ነገራችንን ለማንም ባትናገሩ ነፍሳችን በነፍሳችሁ ፋንታ ለሞት ይሆናል፤ ጌታም ምድሪቱን በሰጠን ጊዜ ለአንቺ ቸርነትንና ታማኝነትን እናደርጋለን።”