የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዮሐንስ 9:13-34

ዮሐንስ 9:13-34 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ያን ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደ​ው​ንም ሰው ወደ ፈሪ​ሳ​ው​ያን ወሰ​ዱት። ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በም​ራቁ ጭቃ አድ​ርጎ ዐይ​ኖ​ቹን ያበ​ራ​በት ቀኑ ሰን​በት ነበ​ርና። ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም እን​ዴት እን​ዳየ ዳግ​መኛ ጠየ​ቁት፤ እር​ሱም፥ “በም​ራቁ ጭቃ አድ​ርጎ በዐ​ይ​ኖች አኖ​ረው፥ ታጥ​ቤም አየሁ” አላ​ቸው። ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያ​ንም አን​ዳ​ን​ዶች፥ “ይህ ሰው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለም፤ ሰን​በ​ትን አያ​ከ​ብ​ር​ምና” አሉ፤ ሌሎች ግን “ኀጢ​ኣ​ተኛ ሰው እን​ዲህ ያለ ተአ​ም​ራት ማድ​ረግ እን​ዴት ይች​ላል?” አሉ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተለ​ያዩ። ዳግ​መ​ኛም ዕዉ​ሩን፥ “አንተ ስለ እርሱ ምን ትላ​ለህ? ዐይ​ኖ​ች​ህን ከፍ​ቶ​ል​ሃ​ልና” አሉት፤ እር​ሱም፥ “ነቢይ ነው” አላ​ቸው። አይ​ሁ​ድም የዚ​ያን ያየ​ውን ሰው ወላ​ጆች እስ​ኪ​ጠሩ ድረስ ዕዉር ሆኖ እንደ ተወ​ለደ፥ እን​ዳ​የም አላ​መ​ኑም። “ዕዉር ሆኖ ተወ​ለደ የም​ት​ሉት ልጃ​ችሁ ይህ ነውን? እን​ግ​ዲያ አሁን እን​ዴት ያያል?” ብለው ጠየ​ቁ​አ​ቸው። ወላ​ጆ​ቹም መል​ሰው እን​ዲህ አሉ፥ “ይህ ልጃ​ችን እንደ ሆነ፥ ዕዉር ሆኖም እንደ ተወ​ለደ እና​ው​ቃ​ለን። አሁን ግን እን​ዴት እን​ደ​ሚ​ያይ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ማን እንደ አበ​ራ​ለት አና​ው​ቅም፤ እር​ሱን ጠይ​ቁት፤ ዐዋቂ ነውና፤ ስለ ራሱም መና​ገር ይች​ላ​ልና።” ወላ​ጆቹ አይ​ሁ​ድን ስለ ፈሩ ይህን አሉ፥ “እርሱ ክር​ስ​ቶስ ነው ብሎ በእ​ርሱ የሚ​ያ​ምን ቢኖር ከም​ኵ​ራብ ይውጣ” ብለው አይ​ሁድ ተስ​ማ​ም​ተው ነበ​ርና። ስለ​ዚ​ህም ወላ​ጆቹ፥ “ዐዋቂ ነውና እር​ሱን ጠይ​ቁት” አሉ። ዕውር የነ​በ​ረ​ው​ንም ሰው ዳግ​መኛ ጠር​ተው፥ “ሂድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና አቅ​ርብ፤ ይህ ሰው ኀጢ​ኣ​ተኛ እንደ ሆነ እኛ እና​ው​ቃ​ለን” አሉት። ያም ሰው መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እርሱ ኀጢ​ኣ​ተኛ እንደ ሆነ እኔ አላ​ው​ቅም፤ እኔ ዕዉር እንደ ነበ​ርሁ፤ አሁን ግን እን​ደ​ማይ ይህን አንድ ነገር ብቻ አው​ቃ​ለሁ።” ዳግ​መ​ኛም፥ “ምን አደ​ረ​ገ​ልህ? ዐይ​ኖ​ች​ህ​ንስ እን​ደ​ምን አበ​ራ​ልህ?” አሉት። እር​ሱም መልሶ፥ “አት​ሰ​ሙ​ኝም እንጂ ነገ​ር​ኋ​ችሁ፤ እን​ግ​ዲህ ደግሞ ምን ልት​ሰሙ ትሻ​ላ​ችሁ? እና​ን​ተም ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ልት​ሆኑ ትሻ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም ሰደ​ቡት፤ እን​ዲ​ህም አሉት፥ “አንተ የእ​ርሱ ደቀ መዝ​ሙር ሁን፤ እኛስ የሙሴ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ነን። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እንደ ተነ​ጋ​ገ​ረው እና​ው​ቃ​ለን፤ ይህን ግን ከወ​ዴት እንደ ሆነ አና​ው​ቅም።” ያም ሰው መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ከወ​ዴት እንደ ሆነ፥ አታ​ው​ቁ​ት​ምና ይህ እጅግ ድንቅ ነው፤ ነገር ግን ዐይ​ኖ​ችን አበ​ራ​ልኝ። እኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ራ​ው​ንና ፈቃ​ዱን የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን እር​ሱን ይሰ​ማ​ዋል እንጂ ኃጥ​ኣ​ንን እን​ደ​ማ​ይ​ሰ​ማ​ቸው እና​ው​ቃ​ለን። ዓለም ከተ​ፈ​ጠረ ጀምሮ ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ዐይ​ኖች ያበራ አል​ተ​ሰ​ማም። ይህ ሰው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባይ​ሆን ኖሮ ምንም ማድ​ረግ ባል​ቻ​ለም ነበር።” እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “ራስህ በኀ​ጢ​ኣት የተ​ወ​ለ​ድህ አንተ እኛን ታስ​ተ​ም​ረ​ና​ለ​ህን?” አሉት፤ ወደ ውጭም አወ​ጡት።

ዮሐንስ 9:13-34 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እነርሱም ዐይነ ስውር የነበረውን ሰው ወደ ፈሪሳውያን ወሰዱት። ኢየሱስ ጭቃ የሠራበት፣ የሰውየውንም ዐይን የከፈተበት ቀን ሰንበት ነበር። ስለዚህ ፈሪሳውያንም እንዴት ማየት እንደ ቻለ ጠየቁት። ሰውየውም፣ “እርሱ ዐይኔን ጭቃ ቀባኝ፤ እኔም ታጠብሁ፤ ይኸው አያለሁ” አላቸው። ከፈሪሳውያንም አንዳንዶቹ፣ “ይህ ሰው ሰንበትን ስለማያከብር፣ ከእግዚአብሔር አይደለም” አሉ። ሌሎች ግን፣ “ኀጢአተኛ፣ እንዲህ ያሉትን ታምራዊ ምልክቶች እንዴት ሊያደርግ ይችላል?” አሉ። በመካከላቸውም አለመስማማት ተፈጠረ። ስለዚህ፣ ዐይነ ስውር ወደ ነበረው ሰው ተመልሰው፣ “ዐይንህን ስለ ከፈተው ሰው፣ እንግዲህ አንተ ምን ትላለህ?” አሉት። ሰውየውም፣ “እርሱ ነቢይ ነው” አለ። አይሁድ ወደ ወላጆቹ ልከው እስኪያስጠሯቸው ድረስ፣ ሰውየው ዐይነ ስውር እንደ ነበረና እንዳየ አላመኑም ነበር። እነርሱም፣ “ዐይነ ስውር ሆኖ ተወልዷል የምትሉት ልጃችሁ ይህ ነውን? ታዲያ አሁን እንዴት ሊያይ ቻለ?” አሏቸው። ወላጆቹም እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “ልጃችን መሆኑንና ዐይነ ስውር ሆኖ መወለዱን እናውቃለን፤ አሁን ግን እንዴት ማየት እንደ ቻለና ዐይኖቹን ማን እንደ ከፈተለት እኛ አናውቅም። ሙሉ ሰው ስለሆነ፣ ስለ ራሱ መናገር ይችላልና እርሱን ጠይቁት።” ኢየሱስን፣ ክርስቶስ ነው ብሎ የመሰከረ ሁሉ ከምኵራብ እንዲባረር አይሁድ አስቀድመው ወስነው ስለ ነበር፣ ወላጆቹ ይህን ያሉት አይሁድን ፈርተው ነው። ስለዚህ ወላጆቹ፣ “ሙሉ ሰው ስለሆነ እርሱን ጠይቁት” አሉ። ዐይነ ስውር የነበረውንም ሰው ዳግመኛ ጠርተው፣ “አንተ ሰው፤ እግዚአብሔርን አክብር፤ ይህ ሰው ኀጢአተኛ መሆኑን እኛ እናውቃለን” አሉት። እርሱም፣ “ኀጢአተኛ መሆኑን እኔ አላውቅም፤ ነገር ግን ዐይነ ስውር እንደ ነበርሁ፤ አሁን ግን እንደማይ ይህን አንድ ነገር ዐውቃለሁ” አለ። እነርሱም፣ “ምን አደረገልህ? እንዴትስ ዐይንህን ከፈተ?” ብለው ጠየቁት። እርሱም፣ “አስቀድሜ ነገርኋችሁ፤ አላዳመጣችሁኝም፤ ለምን እንደ ገና መስማት ፈለጋችሁ? እናንተም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱ ልትሆኑ ትሻላችሁ?” አለ። ከዚህ በኋላ በእርሱ ላይ የስድብ ናዳ በማውረድ እንዲህ አሉት፤ “የዚህ ሰው ደቀ መዝሙር አንተ ነህ፤ እኛስ የሙሴ ደቀ መዛሙርት ነን! እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተናገረው እናውቃለን፤ ይህ ሰው ግን ከየት እንደ መጣ እንኳ አናውቅም።” ሰውየውም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እናንተ ከየት እንደ መጣ አለማወቃችሁ የሚያስደንቅ ነው፤ ይሁን እንጂ እርሱ ዐይኖቼን ከፈተልኝ። እግዚአብሔር የሚሰማው፣ የሚፈራውንና ፈቃዱን የሚያደርገውን እንጂ፣ ኀጢአተኞችን እንደማይሰማ እናውቃለን፤ ዐይነ ስውር ሆኖ የተወለደን ሰው ዐይን የከፈተ አለ ሲባል፣ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ማንም ሰምቶ አያውቅም። ይህ ሰው ከእግዚአብሔር ባይሆን ኖሮ ይህን ማድረግ ባልቻለ ነበር።” እነርሱም፣ “ሁለንተናህ በኀጢአት ተነክሮ የተወለድህ፣ አንተ እኛን ለማስተማር እንዴት ትደፍራለህ?” ሲሉ መለሱለት፤ አባረሩትም።

ዮሐንስ 9:13-34 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በፊት ዕውር የነበረውን ሰው ወደ ፈሪሳውያን ወሰዱት። ኢየሱስም ጭቃ አድርጎ ዓይኖቹን የከፈተበት ቀን ሰንበት ነበረ። ስለዚህ ፈሪሳውያን ደግሞ እንዴት እንዳየ እንደ ገና ጠየቁት። እርሱም፦ “ጭቃ በዓይኖቼ አኖረ ታጠብሁም አያለሁም” አላቸውም። ከፈሪሳውያንም አንዳንዶቹ፦ “ይህ ሰው ሰንበትን አያከብርምና ከእግዚአብሔር አይደለም” አሉ። ሌሎች ግን፦ “ኃጢአትኛ ሰው እንደነዚህ ያሉ ምልክቶች ሊያደርግ እንዴት ይችላል?” አሉ። በመካከላቸውም መለያየት ሆነ። ከዚህም የተነሣ ዕውሩን፦ “አንተ ዓይኖችህን ስለ ከፈተ ስለ እርሱ ምን ትላለህ?” ደግሞ አሉት። እርሱም፦ “ነቢይ ነው” አለ። አይሁድ የዚያን ያየውን ወላጆች እስኪጠሩ ድረስ ዕውር እንደ ነበረ እንዳየም ስለ እርሱ አላመኑም፥ እነርሱንም፦ “እናንተ ዕውር ሆኖ ተወለደ የምትሉት ልጃችሁ ይህ ነውን? ታድያ አሁን እንዴት ያያል?” ብለው ጠየቁአቸው። ወላጆቹም መልእሰው፦ “ይህ ልጃችን እንደ ሆነ ዕውርም ሆኖ እንደ ተወለደ አናውቃለን፤ ዳሩ ግን አሁን እንዴት እንዳየ አናውቅም፥ ወይም ዓይኖቹን ማን እንደ ከፈተ እኛ አናውቅም፤ ጠይቁት እርሱ ሙሉ ሰው ነው፤ እርሱ ስለ ራሱ ይናገራል” አሉ። ወላጆቹ አይሁድን ስለ ፈሩ ይህን አሉ፤ እርሱ ክርስቶስ ነው ብሎ የሚመሰክር ቢኖር ክምኵራብ እንዲያወጡት አይሁድ ከዚህ በፊት ተስማምተው ነበርና። ስለዚህ ወላጆቹ፦ “ሙሉ ሰው ነው፥ ጠኡቁት” አሉ። ስለዚህ ዕውር የነበረው ሰው ሁለተኛ ጠርተው፦ “እግዚአብሔርን አክብር፤ ይህ ሰው ኃጢአተኛ መሆኑን እኛ እናውቃለን” አሉት። እርሱም መልሶ፦ “ኃጢአተኛ መሆኑን አላውቅም፤ ዕውር እንደ ነበርሁ አሁንም እንዳይ ይህን አንድ ነገር አውቃለሁ” አለ። ደግመውም፦ “ምን አደረገህ? እንዴትስ ዓይኖችህን ከፈተ?” አሉት። እርሱም መልሶ፦ “አስቀድሜ ነገርኋችሁ አልሰማችሁምም፤ ስለ ምን ዳግመኛ ልትሰሙ ትወዳላችሁ? እናንተ ደግሞ ደቀ መዛሙርቱ ልትሆኑ ትወዳላችሁን?” አላቸው። ተሳድበውም፦ “አንተ የእርሱ ደቀ መዝሙር ነህ፥ እኛ ግን የሙሴ ደቀ መዛሙርት ነን፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተናገረው እኛ እናውቃለን፥ ይህ ሰው ግን ከወዴት እንደ ሆነ አናውቅም” አሉት። ሰውዬው መለሰ እንዲህም አላቸው፦ “ከወዴት እንደ ሆነ እናንተ አለማወቃችሁ ይህ ድንቅ ነገር ነው፥ ዳሩ ግን ዓይኖቼን ከፈተ። እግዚአብሔርን የሚፈራ ፈቃዱንም የሚያደርግ ቢኖር ያንን እግዚአብሔር ይሰማዋል እንጂ ኃጢአተኞችን እንዳይሰማ እናውቃለን። ዕውር ሆኖ የተወለደውን ዓይኖች ማንም እንደ ከፈተ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ አልተሰማም፤ ይህ ሰው ከእግዚአብሔር ባይሆን ምንም ሊያደርግ ባልቻለም ነበር።” መልሰው፦ “አንተ ሁለንተናህ በኃጢአት ተወልድህ፥ አንተም እኛን ታስተምረናለህን?” አሉት። ወደ ውጭም አወጡት።

ዮሐንስ 9:13-34 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ከዚህ በኋላ ሰዎቹ ዕውር የነበረውን ሰው ወደ ፈሪሳውያን ወሰዱት። ኢየሱስ ጭቃ ለውሶ የሰውዬውን ዐይኖች እንዲበሩ ያደረገው በሰንበት ቀን ነበር፤ ፈሪሳውያን “እንዴት ማየት ቻልክ?” ብለው ሰውየውን እንደገና ጠየቁት። እርሱም “ዐይኖቼ ላይ ጭቃ አደረገልኝና ታጠብኩ፤ ከዚያም በኋላ ማየት ቻልኩ” አለ። በዚህ ጊዜ ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ፥ “ይህ ሰው ሰንበትን ስለማያከብር ከእግዚአብሔር አይደለም” አሉ። ሌሎች ግን “ታዲያ፥ ኃጢአተኛ የሆነ ሰው እነዚህን ተአምራት እንዴት ማድረግ ይችላል?” አሉ። በዚህ ምክንያት በመካከላቸው መለያየት ሆነ። ስለዚህ ዕውር የነበረውን ሰው፥ “አንተስ ዐይኖችህን አበራልኝ ስለምትለው ስለዚያ ሰው ምን ትላለህ?” ሲሉ ደግመው ጠየቁት። እርሱም “ነቢይ ነው!” አለ። ይህ ሰው ዕውር እንደ ነበረና ዐይኖቹም በኋላ እንዴት እንደ ተከፈቱ ወላጆቹን ጠርተው እስከ ጠየቁአቸው ድረስ የአይሁድ ባለ ሥልጣኖች አላመኑም ነበር። ስለዚህ ወላጆቹን፥ “ዕውር ሆኖ ተወለደ የምትሉት ልጃችሁ ይህ ነውን? አሁንስ እንዴት ማየት ቻለ?” ሲሉ ጠየቁአቸው። ወላጆቹም እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ “ይህ ሰው ልጃችን መሆኑንና ዕውር ሆኖ መወለዱን እናውቃለን፤ ነገር ግን አሁን እንዴት እንደሚያይና ዐይኖቹንም ማን እንደአበራለት አናውቅም፤ እርሱን ጠይቁት፤ እርሱ በዕድሜው ሙሉ ሰው ስለ ሆነ ስለ ራሱ መናገር ይችላል።” ወላጆቹ ይህን ያሉት ኢየሱስን “መሲሕ ነው” የሚል ሰው ቢኖር የአይሁድ ባለሥልጣኖች ከምኲራብ ሊያስወጡት ተስማምተው ስለ ነበረ እነርሱን በመፍራት ነበር። ስለዚህ ወላጆቹ፥ “እርሱ በዕድሜው ሙሉ ሰው ነው፤ እርሱን ጠይቁት” አሉ። በዚህ ምክንያት ዕውር የነበረውን ሰው እንደገና ጠርተው “አንተ እውነቱን በመናገር እግዚአብሔርን አክብር፤ ይህ ሰው ኃጢአተኛ መሆኑን እኛ እናውቃለን” አሉት። ዕውር የነበረውም ሰው፥ “እርሱ ኃጢአተኛ መሆኑን እኔ አላውቅም፤ አንድ ነገር ዐውቃለሁ፤ ይኸውም እኔ ዕውር እንደ ነበርኩና አሁን ማየት እንደ ቻልኩ ብቻ ነው” ሲል መለሰ። እነርሱም “ምን አደረገልህ? ዐይኖችህንስ ያዳነው እንዴት ነው?” አሉት። እርሱም “አስቀድሜ ነገርኳችሁ፤ እናንተ ግን መስማት አልፈለጋችሁም፤ ታዲያ፥ ስለምን እንደገና መስማት ትፈልጋላችሁ? እናንተም የእርሱ ደቀ መዛሙርት መሆን ትፈልጋላችሁን?” አላቸው። እነርሱም እንዲህ እያሉ ሰደቡት፦ “የእርሱስ ደቀ መዝሙር አንተ ነህ፤ እኛ ግን የሙሴ ደቀ መዛሙርት ነን፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳነጋገረው እናውቃለን፤ ይህ ሰው ግን ከየት እንደ ሆነ አናውቅም።” ሰውየውም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ይህ ሰው ከየት እንደ ሆነ አለማወቃችሁ ያስደንቃል! ነገር ግን ዐይኖቼን የአበራ እርሱ ነው። እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን እንደማይሰማ የታወቀ ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን የሚያመልክና ፈቃዱንም የሚፈጽም ሰው ሲኖር እርሱን እግዚአብሔር ይሰማዋል። ዕውር ሆኖ የተወለደውን ሰው ዐይኖች ያበራ አለ ሲባል ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ተሰምቶ አይታወቅም። ይህ ሰው ከእግዚአብሔር ባይሆን ኖሮ ምንም ለማድረግ ባልቻለም ነበር።” እነርሱም “ሁለንተናህ በኃጢአት ተወርሶ የተወለድክ! አንተ እኛን ልታስተምር ነውን?” አሉና ከምኲራብ አስወጡት።

ዮሐንስ 9:13-34 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በፊት ዐይነ ስውር የነበረውን ሰው ወደ ፈሪሳውያን ወሰዱት። ኢየሱስም ጭቃ አድርጎ ዐይኖቹን የከፈተበት ቀን ሰንበት ነበረ። ስለዚህ ፈሪሳውያን እንዴት እንዳየ እንደገና ጠየቁት። እርሱም “ጭቃ በዐይኖቼ አኖረ፤ ታጠብሁም፤ አያለሁም፤” አላቸውም። ከፈሪሳውያንም አንዳንዶቹ “ይህ ሰው ሰንበትን አያከብርምና ከእግዚአብሔር አይደለም፤” አሉ። ሌሎች ግን “ኃጢአትኛ ሰው እንደነዚህ ያሉ ምልክቶችን ሊያደርግ እንዴት ይችላል?” አሉ። በመካከላቸውም መለያየት ሆነ። ከዚህም የተነሣ ዐይነ ሥውሩን፥ “አንተ ዐይኖችህን ስለ ከፈተ፥ ስለ እርሱ ምን ትላለህ?” ደግሞ አሉት። እርሱም “ነቢይ ነው፤” አለ። አይሁድ የዚያን ማየት የቻለውን ወላጆች እስኪጠሩ ድረስ፥ ዐይን ሥውር እንደ ነበረና ማየትም እንደ ጀመረ አላመኑም፤ እነርሱንም “እናንተ ዐይን ሥውር ሆኖ ተወለደ የምትሉት ልጃችሁ ይህ ነውን? ታድያ አሁን እንዴት ያያል?” ብለው ጠየቁአቸው። ወላጆቹም መልሰው “ይህ ልጃችን እንደሆነ ዐይነ ስውርም ሆኖ እንደ ተወለደ እናውቃለን፤ ዳሩ ግን አሁን እንዴት ማየት እንደቻለ አናውቅም፤ ወይም ዐይኖቹን ማን እንደ ከፈተለት እኛ አናውቅም፤ እርሱን ጠይቁት፤ እርሱ ሙሉ ሰው ነው፤ እርሱ ስለ እራሱ መናገር ይችላል፤” አሉ። ወላጆቹ አይሁድን ስለ ፈሩ ይህንን አሉ፤ “እርሱ ክርስቶስ ነው፤” ብሎ የሚመሰክር ቢኖር ከምኵራብ እንዲያወጡት አይሁድ ከዚህ በፊት ተስማምተው ነበርና። ስለዚህ ወላጆቹ “ሙሉ ሰው ነው፤ እርሱን ጠይቁት፤” አሉ። ስለዚህ ዐይን ሥውር የነበረውን ሰው ለሁለተኛ ጊዜ ጠርተው “እግዚአብሔርን አክብር፤ ይህ ሰው ኀጢአተኛ መሆኑን እኛ እናውቃለን፤” አሉት። እርሱም መልሶ “ኀጢአተኛ መሆኑን አላውቅም፤ ዐይን ሥውር እንደ ነበርሁ፥ አሁንም እንደማይ፥ ይህንን አንድ ነገር አውቃለሁ፤” አለ። ደግመውም “ምን አደረገልህ? እንዴትስ ዐይኖችህን ከፈተ?” አሉት። እርሱም መልሶ “አስቀድሜ ነገርኋችሁ፤ አልሰማችሁምም፤ ስለምን ዳግመኛ ልትሰሙ ትፈልጋላችሁ? እናንተ ደግሞ ደቀመዛሙርቱ ልትሆኑ ትፈልጋላችሁን?” አላቸው። ተሳድበውም “አንተ የእርሱ ደቀመዝሙር ነህ፤ እኛ ግን የሙሴ ደቀ መዛሙርት ነን፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተናገረው እኛ እናውቃለን፤ ይህ ሰው ግን ከወዴት እንደሆነ አናውቅም፤” አሉት። ሰውዬው መለሰ፤ እንዲህም አላቸው “ከወዴት እንደሆነ እናንተ አለማወቃችሁ ይህ ድንቅ ነገር ነው፤ ዳሩ ግን ዐይኖቼን ከፈተ። እግዚአብሔርን የሚፈራ ፈቃዱንም የሚያደርግ ቢኖር፥ ያንን እግዚአብሔር ይሰማዋል እንጂ ኀጢአተኞችን እንደማይሰማ እናውቃለን። ዐይን ሥውር ሆኖ የተወለደውን ሰው ዐይኖች ማንም እንደ ከፈተ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ አልተሰማም፤ ይህ ሰው ከእግዚአብሔር ባይሆን ኖሮ ምንም ሊያደርግ ባልቻለ ነበር።” መልሰው “አንተ ሙሉ በሙሉ በኃጢአት ተወልድህ፤ እኛን ታስተምረናለህን?” አሉት። ወደ ውጭም አወጡት።