የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዮሐንስ 9:1-25

ዮሐንስ 9:1-25 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ከዚ​ያም ሲያ​ልፍ ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ሰው አየ። ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም፥ “መም​ህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደው በማን ኀጢ​ኣት ነው? በራሱ ነውን? ወይስ በወ​ላ​ጆቹ?” ብለው ጠየ​ቁት። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ ሊገ​ለ​ጥ​በት ነው እንጂ እርሱ አል​በ​ደ​ለም፤ ወላ​ጆ​ቹም አል​በ​ደ​ሉም። ነገር ግን ቀን ሳለ የላ​ከ​ኝን ሥራ ልሠራ ይገ​ባ​ኛል፤ ማንም ሥራ ሊሠራ የማ​ይ​ች​ል​ባት ሌሊት ትመ​ጣ​ለ​ችና። በዓ​ለም ሳለሁ፤ የዓ​ለም ብር​ሃን እኔ ነኝ።” ይህ​ንም ብሎ በም​ድር ላይ ምራ​ቁን እን​ትፍ አለ፤ በም​ራ​ቁም ጭቃ አድ​ርጎ የዕ​ዉ​ሩን ዐይ​ኖች ቀባው። እን​ዲ​ህም አለው፥ “ሂድና በሰ​ሊ​ሆም መጠ​መ​ቂያ ታጠብ” ትር​ጓ​ሜ​ውም የተ​ላከ ማለት ነው፤ ሄዶም ታጠ​በና እያየ ተመ​ለሰ። ጎረ​ቤ​ቶ​ቹና ቀድሞ የሚ​ያ​ው​ቁት፥ ሲለ​ም​ንም ያዩት የነ​በ​ሩት ግን፥ “ይህ በመ​ን​ገድ ተቀ​ምጦ ይለ​ምን የነ​በ​ረው አይ​ደ​ለም?” አሉ። “ይህ እርሱ ነው” ያሉ አሉ፤ ሌሎ​ችም፥ “አይ​ደ​ለም፤ ይመ​ስ​ለ​ዋል እንጂ” አሉ፤ እርሱ ራሱ ግን፥ “እኔ ነኝ” አለ። እነ​ር​ሱም፥ “ዐይ​ኖ​ችህ እን​ዴት ተገ​ለጡ?” አሉት። እር​ሱም መልሶ፥ “ኢየ​ሱስ የሚ​ባ​ለው ሰው በም​ራቁ ጭቃ አድ​ርጎ ዐይ​ኖ​ችን ቀባ​ኝና ሂደህ በሰ​ሊ​ሆም ውኃ ታጠብ አለኝ፤ ሄጄም ታጠ​ብ​ሁና አየሁ” አላ​ቸው። አይ​ሁ​ድም፥ “ሰው​የው የት አለ?” አሉት፤ እር​ሱም፥ “አላ​ው​ቅም” አላ​ቸው። ያን ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደ​ው​ንም ሰው ወደ ፈሪ​ሳ​ው​ያን ወሰ​ዱት። ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በም​ራቁ ጭቃ አድ​ርጎ ዐይ​ኖ​ቹን ያበ​ራ​በት ቀኑ ሰን​በት ነበ​ርና። ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም እን​ዴት እን​ዳየ ዳግ​መኛ ጠየ​ቁት፤ እር​ሱም፥ “በም​ራቁ ጭቃ አድ​ርጎ በዐ​ይ​ኖች አኖ​ረው፥ ታጥ​ቤም አየሁ” አላ​ቸው። ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያ​ንም አን​ዳ​ን​ዶች፥ “ይህ ሰው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለም፤ ሰን​በ​ትን አያ​ከ​ብ​ር​ምና” አሉ፤ ሌሎች ግን “ኀጢ​ኣ​ተኛ ሰው እን​ዲህ ያለ ተአ​ም​ራት ማድ​ረግ እን​ዴት ይች​ላል?” አሉ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተለ​ያዩ። ዳግ​መ​ኛም ዕዉ​ሩን፥ “አንተ ስለ እርሱ ምን ትላ​ለህ? ዐይ​ኖ​ች​ህን ከፍ​ቶ​ል​ሃ​ልና” አሉት፤ እር​ሱም፥ “ነቢይ ነው” አላ​ቸው። አይ​ሁ​ድም የዚ​ያን ያየ​ውን ሰው ወላ​ጆች እስ​ኪ​ጠሩ ድረስ ዕዉር ሆኖ እንደ ተወ​ለደ፥ እን​ዳ​የም አላ​መ​ኑም። “ዕዉር ሆኖ ተወ​ለደ የም​ት​ሉት ልጃ​ችሁ ይህ ነውን? እን​ግ​ዲያ አሁን እን​ዴት ያያል?” ብለው ጠየ​ቁ​አ​ቸው። ወላ​ጆ​ቹም መል​ሰው እን​ዲህ አሉ፥ “ይህ ልጃ​ችን እንደ ሆነ፥ ዕዉር ሆኖም እንደ ተወ​ለደ እና​ው​ቃ​ለን። አሁን ግን እን​ዴት እን​ደ​ሚ​ያይ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ማን እንደ አበ​ራ​ለት አና​ው​ቅም፤ እር​ሱን ጠይ​ቁት፤ ዐዋቂ ነውና፤ ስለ ራሱም መና​ገር ይች​ላ​ልና።” ወላ​ጆቹ አይ​ሁ​ድን ስለ ፈሩ ይህን አሉ፥ “እርሱ ክር​ስ​ቶስ ነው ብሎ በእ​ርሱ የሚ​ያ​ምን ቢኖር ከም​ኵ​ራብ ይውጣ” ብለው አይ​ሁድ ተስ​ማ​ም​ተው ነበ​ርና። ስለ​ዚ​ህም ወላ​ጆቹ፥ “ዐዋቂ ነውና እር​ሱን ጠይ​ቁት” አሉ። ዕውር የነ​በ​ረ​ው​ንም ሰው ዳግ​መኛ ጠር​ተው፥ “ሂድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና አቅ​ርብ፤ ይህ ሰው ኀጢ​ኣ​ተኛ እንደ ሆነ እኛ እና​ው​ቃ​ለን” አሉት። ያም ሰው መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እርሱ ኀጢ​ኣ​ተኛ እንደ ሆነ እኔ አላ​ው​ቅም፤ እኔ ዕዉር እንደ ነበ​ርሁ፤ አሁን ግን እን​ደ​ማይ ይህን አንድ ነገር ብቻ አው​ቃ​ለሁ።”

ዮሐንስ 9:1-25 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በመንገድ ሲያልፍም ከተወለደ ጀምሮ ዐይነ ስውር የሆነ ሰው አየ። ደቀ መዛሙርቱም፣ “ረቢ፤ ይህ ሰው ዐይነ ስውር ሆኖ እንዲወለድ ኀጢአት የሠራ ማን ነው? እርሱ ራሱ ወይስ ወላጆቹ?” ብለው ጠየቁት። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እርሱ ወይም ወላጆቹ ኀጢአት አልሠሩም፤ ይህ የሆነው ግን የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ ሕይወት እንዲገለጥ ነው። ቀን ሳለ፣ የላከኝን ሥራ መሥራት አለብን፤ ማንም ሊሠራ የማይችልበት ሌሊት ይመጣል፤ በዓለም ሳለሁ የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ።” ይህን ካለ በኋላ፣ በምድር ላይ እንትፍ ብሎ በምራቁ ጭቃ አበጀ፤ የሰውየውንም ዐይን ቀባና፣ “ሄደህ በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ” አለው፤ ሰሊሆም ማለት “የተላከ” ማለት ነው። ሰውየውም ሄዶ ታጠበ፤ እያየም ተመልሶ መጣ። ጎረቤቶቹና ከዚህ ቀደም ብሎ ሲለምን ያዩት ሰዎች፣ “ይህ ሰው ተቀምጦ ሲለምን የነበረው አይደለምን?” አሉ። አንዳንዶቹም፣ “በርግጥ እርሱ ነው” አሉ። ሌሎችም፣ “ይመስለዋል እንጂ እርሱ አይደለም” አሉ። እርሱ ግን፣ “እኔው ነኝ” አለ። እነርሱም፣ “ታዲያ ዐይኖችህ እንዴት ተከፈቱ?” ሲሉ ጠየቁት። እርሱም፣ “ኢየሱስ የሚሉት ሰው ጭቃ አድርጎ ዐይኔን ቀባኝ፤ ወደ ሰሊሆም ሄጄ እንድታጠብም ነገረኝ፤ ሄጄ ታጠብሁ፤ ማየትም ቻልሁ” ሲል መለሰ። እነርሱም፣ “ታዲያ፣ ያ ሰው የት አለ?” አሉት። እርሱም፣ “እኔ አላውቅም” አለ። እነርሱም ዐይነ ስውር የነበረውን ሰው ወደ ፈሪሳውያን ወሰዱት። ኢየሱስ ጭቃ የሠራበት፣ የሰውየውንም ዐይን የከፈተበት ቀን ሰንበት ነበር። ስለዚህ ፈሪሳውያንም እንዴት ማየት እንደ ቻለ ጠየቁት። ሰውየውም፣ “እርሱ ዐይኔን ጭቃ ቀባኝ፤ እኔም ታጠብሁ፤ ይኸው አያለሁ” አላቸው። ከፈሪሳውያንም አንዳንዶቹ፣ “ይህ ሰው ሰንበትን ስለማያከብር፣ ከእግዚአብሔር አይደለም” አሉ። ሌሎች ግን፣ “ኀጢአተኛ፣ እንዲህ ያሉትን ታምራዊ ምልክቶች እንዴት ሊያደርግ ይችላል?” አሉ። በመካከላቸውም አለመስማማት ተፈጠረ። ስለዚህ፣ ዐይነ ስውር ወደ ነበረው ሰው ተመልሰው፣ “ዐይንህን ስለ ከፈተው ሰው፣ እንግዲህ አንተ ምን ትላለህ?” አሉት። ሰውየውም፣ “እርሱ ነቢይ ነው” አለ። አይሁድ ወደ ወላጆቹ ልከው እስኪያስጠሯቸው ድረስ፣ ሰውየው ዐይነ ስውር እንደ ነበረና እንዳየ አላመኑም ነበር። እነርሱም፣ “ዐይነ ስውር ሆኖ ተወልዷል የምትሉት ልጃችሁ ይህ ነውን? ታዲያ አሁን እንዴት ሊያይ ቻለ?” አሏቸው። ወላጆቹም እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “ልጃችን መሆኑንና ዐይነ ስውር ሆኖ መወለዱን እናውቃለን፤ አሁን ግን እንዴት ማየት እንደ ቻለና ዐይኖቹን ማን እንደ ከፈተለት እኛ አናውቅም። ሙሉ ሰው ስለሆነ፣ ስለ ራሱ መናገር ይችላልና እርሱን ጠይቁት።” ኢየሱስን፣ ክርስቶስ ነው ብሎ የመሰከረ ሁሉ ከምኵራብ እንዲባረር አይሁድ አስቀድመው ወስነው ስለ ነበር፣ ወላጆቹ ይህን ያሉት አይሁድን ፈርተው ነው። ስለዚህ ወላጆቹ፣ “ሙሉ ሰው ስለሆነ እርሱን ጠይቁት” አሉ። ዐይነ ስውር የነበረውንም ሰው ዳግመኛ ጠርተው፣ “አንተ ሰው፤ እግዚአብሔርን አክብር፤ ይህ ሰው ኀጢአተኛ መሆኑን እኛ እናውቃለን” አሉት። እርሱም፣ “ኀጢአተኛ መሆኑን እኔ አላውቅም፤ ነገር ግን ዐይነ ስውር እንደ ነበርሁ፤ አሁን ግን እንደማይ ይህን አንድ ነገር ዐውቃለሁ” አለ።

ዮሐንስ 9:1-25 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ሲያልፍም ከመወለዱ ጀምሮ ዕውር የሆነውን ሰው አየ። ደቀ መዛሙርቱም፦ “መምህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕውር ሆኖ እንዲወለድ ኃጢአት የሠራ ማን ነው? እርሱ ወይስ ወላጆቹ?” ብለው ጠየቁት። ኢየሱስም እንዲ ብሎ መልሰ፦ “የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ ነው እንጂ እርሱ ወይም ወላጆቹ ኃጢአት አልሠሩም። ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች። በዓለም ሳለሁ የዓለም ብርሃን ነኝ።” ይህን ብሎ ወደ መሬት እንትፍ አለ በምራቁም ጭቃ አድርጎ በጭቃው የዕውሩን ዓይኖች ቀባና፦ “ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ” አለው፤ ትርጓሜው የተላከ ነው። ስለዚህ ሄዶ ታጠበ እያየም መጣ። ጐረቤቶቹም ቀድሞም ሲለምን አይተውት የነበሩ፦ “ይህ ተቀምጦ ይለምን የነበረ አይደለምን?” አሉ። ሌሎች፦ “እሩ ነው” አሉ፤ ሌሎች፦ “አይደለም እርሱን ይመስላል እንጂ” አሉ፤ እርሱ፦ “እኔ ነኝ አለ።” ታድያ፦ “ዓይኖችህ እንዴት ተከፈቱ?” አሉት። እርሱ መልሶ፦ “ኢየሱስ የሚባለው ሰው ጭቃ አድርጎ አይኖቼን ቀባና፦ ‘ወደ ሰሊሆም መጠመቂያ ሄደህ ታጠብ’ አለኝ፤ ሄጄ ታጥቤም አየሁ” አለ። “ያ ሰው ወዴት ነው?” አሉት። “አላውቅም” አለ። በፊት ዕውር የነበረውን ሰው ወደ ፈሪሳውያን ወሰዱት። ኢየሱስም ጭቃ አድርጎ ዓይኖቹን የከፈተበት ቀን ሰንበት ነበረ። ስለዚህ ፈሪሳውያን ደግሞ እንዴት እንዳየ እንደ ገና ጠየቁት። እርሱም፦ “ጭቃ በዓይኖቼ አኖረ ታጠብሁም አያለሁም” አላቸውም። ከፈሪሳውያንም አንዳንዶቹ፦ “ይህ ሰው ሰንበትን አያከብርምና ከእግዚአብሔር አይደለም” አሉ። ሌሎች ግን፦ “ኃጢአትኛ ሰው እንደነዚህ ያሉ ምልክቶች ሊያደርግ እንዴት ይችላል?” አሉ። በመካከላቸውም መለያየት ሆነ። ከዚህም የተነሣ ዕውሩን፦ “አንተ ዓይኖችህን ስለ ከፈተ ስለ እርሱ ምን ትላለህ?” ደግሞ አሉት። እርሱም፦ “ነቢይ ነው” አለ። አይሁድ የዚያን ያየውን ወላጆች እስኪጠሩ ድረስ ዕውር እንደ ነበረ እንዳየም ስለ እርሱ አላመኑም፥ እነርሱንም፦ “እናንተ ዕውር ሆኖ ተወለደ የምትሉት ልጃችሁ ይህ ነውን? ታድያ አሁን እንዴት ያያል?” ብለው ጠየቁአቸው። ወላጆቹም መልእሰው፦ “ይህ ልጃችን እንደ ሆነ ዕውርም ሆኖ እንደ ተወለደ አናውቃለን፤ ዳሩ ግን አሁን እንዴት እንዳየ አናውቅም፥ ወይም ዓይኖቹን ማን እንደ ከፈተ እኛ አናውቅም፤ ጠይቁት እርሱ ሙሉ ሰው ነው፤ እርሱ ስለ ራሱ ይናገራል” አሉ። ወላጆቹ አይሁድን ስለ ፈሩ ይህን አሉ፤ እርሱ ክርስቶስ ነው ብሎ የሚመሰክር ቢኖር ክምኵራብ እንዲያወጡት አይሁድ ከዚህ በፊት ተስማምተው ነበርና። ስለዚህ ወላጆቹ፦ “ሙሉ ሰው ነው፥ ጠኡቁት” አሉ። ስለዚህ ዕውር የነበረው ሰው ሁለተኛ ጠርተው፦ “እግዚአብሔርን አክብር፤ ይህ ሰው ኃጢአተኛ መሆኑን እኛ እናውቃለን” አሉት። እርሱም መልሶ፦ “ኃጢአተኛ መሆኑን አላውቅም፤ ዕውር እንደ ነበርሁ አሁንም እንዳይ ይህን አንድ ነገር አውቃለሁ” አለ።

ዮሐንስ 9:1-25 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ኢየሱስ በመንገድ ሲያልፍ ዕውር ሆኖ የተወለደ ሰው አየ። ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን “መምህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕውር ሆኖ የተወለደው በማን ኃጢአት ነው? በራሱ ኃጢአት ነውን ወይስ በወላጆቹ?” ሲሉ ጠየቁት። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ይህ ሰው ዕውር ሆኖ የተወለደው በእርሱ ወይም በወላጆቹ ኃጢአት ምክንያት አይደለም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ ነው። ቀን ሆኖ ሳለ የላከኝን ሥራ መሥራት አለብኝ፤ ማንም ሰው ሊሠራ የማይችልበት ሌሊት ይመጣል። በዓለም ላይ ሳለሁ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ።” ይህን ከተናገረ በኋላ በመሬት ላይ እንትፍ አለና በምራቁ ዐፈር ለወሰ፤ በጭቃውም የዕውሩን ዐይኖች ቀባና፥ “ሄደህ በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ” አለው። (ሰሊሆም “የተላከ” ማለት ነው።) ስለዚህ ሰውየው ሄዶ ታጠበና እያየ ተመለሰ። ጐረቤቶቹና ቀድሞ ሲለምን ያዩት የነበሩ ሰዎች፥ “ይህ ሰው ያ ተቀምጦ ይለምን የነበረው አይደለምን?” አሉ። አንዳንዶች “አዎ፥ እርሱ ነው!” አሉ፤ ሌሎች ደግሞ “እርሱን ይመስላል እንጂ እርሱ አይደለም!” አሉ። እርሱ ግን “እኔው ነኝ!” አለ። ሰዎቹም “ታዲያ፥ ዐይኖችህ እንዴት ተከፈቱ?” አሉት። እርሱም “ኢየሱስ የተባለ ሰው ጭቃ ለውሶ ዐይኖቼን ቀባና ‘ወደ ሰሊሆም ሄደህ ታጠብ’ አለኝ፤ እኔም ሄጄ ታጠብኩና ለማየት ቻልኩ” ሲል መለሰ። እነርሱም “ሰውየው አሁን የት አለ?” አሉት። እርሱም “የት እንዳለ እኔ አላውቅም” አላቸው። ከዚህ በኋላ ሰዎቹ ዕውር የነበረውን ሰው ወደ ፈሪሳውያን ወሰዱት። ኢየሱስ ጭቃ ለውሶ የሰውዬውን ዐይኖች እንዲበሩ ያደረገው በሰንበት ቀን ነበር፤ ፈሪሳውያን “እንዴት ማየት ቻልክ?” ብለው ሰውየውን እንደገና ጠየቁት። እርሱም “ዐይኖቼ ላይ ጭቃ አደረገልኝና ታጠብኩ፤ ከዚያም በኋላ ማየት ቻልኩ” አለ። በዚህ ጊዜ ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ፥ “ይህ ሰው ሰንበትን ስለማያከብር ከእግዚአብሔር አይደለም” አሉ። ሌሎች ግን “ታዲያ፥ ኃጢአተኛ የሆነ ሰው እነዚህን ተአምራት እንዴት ማድረግ ይችላል?” አሉ። በዚህ ምክንያት በመካከላቸው መለያየት ሆነ። ስለዚህ ዕውር የነበረውን ሰው፥ “አንተስ ዐይኖችህን አበራልኝ ስለምትለው ስለዚያ ሰው ምን ትላለህ?” ሲሉ ደግመው ጠየቁት። እርሱም “ነቢይ ነው!” አለ። ይህ ሰው ዕውር እንደ ነበረና ዐይኖቹም በኋላ እንዴት እንደ ተከፈቱ ወላጆቹን ጠርተው እስከ ጠየቁአቸው ድረስ የአይሁድ ባለ ሥልጣኖች አላመኑም ነበር። ስለዚህ ወላጆቹን፥ “ዕውር ሆኖ ተወለደ የምትሉት ልጃችሁ ይህ ነውን? አሁንስ እንዴት ማየት ቻለ?” ሲሉ ጠየቁአቸው። ወላጆቹም እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ “ይህ ሰው ልጃችን መሆኑንና ዕውር ሆኖ መወለዱን እናውቃለን፤ ነገር ግን አሁን እንዴት እንደሚያይና ዐይኖቹንም ማን እንደአበራለት አናውቅም፤ እርሱን ጠይቁት፤ እርሱ በዕድሜው ሙሉ ሰው ስለ ሆነ ስለ ራሱ መናገር ይችላል።” ወላጆቹ ይህን ያሉት ኢየሱስን “መሲሕ ነው” የሚል ሰው ቢኖር የአይሁድ ባለሥልጣኖች ከምኲራብ ሊያስወጡት ተስማምተው ስለ ነበረ እነርሱን በመፍራት ነበር። ስለዚህ ወላጆቹ፥ “እርሱ በዕድሜው ሙሉ ሰው ነው፤ እርሱን ጠይቁት” አሉ። በዚህ ምክንያት ዕውር የነበረውን ሰው እንደገና ጠርተው “አንተ እውነቱን በመናገር እግዚአብሔርን አክብር፤ ይህ ሰው ኃጢአተኛ መሆኑን እኛ እናውቃለን” አሉት። ዕውር የነበረውም ሰው፥ “እርሱ ኃጢአተኛ መሆኑን እኔ አላውቅም፤ አንድ ነገር ዐውቃለሁ፤ ይኸውም እኔ ዕውር እንደ ነበርኩና አሁን ማየት እንደ ቻልኩ ብቻ ነው” ሲል መለሰ።

ዮሐንስ 9:1-25 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ሲያልፍም ከመወለዱ ጀምሮ ዐይነ ስውር ሆኖ የተወለደውን ሰው አየ። ደቀ መዛሙርቱም “መምህር ሆይ! ይህ ሰው ዐይነ ስውር ሆኖ እንዲወለድ ኃጢአትን የሠራው ማን ነው? እርሱ ነው ወይስ ወላጆቹ?” ብለው ጠየቁት። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ ነው እንጂ እርሱ ወይም ወላጆቹ ኃጢአት አልሠሩም። ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች። በዓለም እስካለሁ ድረስ የዓለም ብርሃን ነኝ።” ይህንንም ብሎ ወደ መሬት እንትፍ አለ፤ በምራቁም ጭቃ አድርጎ በጭቃው የዐይነ ሥውሩን ዐይኖች ቀባና “ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ፤” አለው፤ ትርጓሜውም “የተላከ” ማለት ነው። ስለዚህም ሄዶ ታጠበ፤ እያየም መጣ። ጐረቤቶቹና ቀድሞ ሲለምን አይተውት የነበሩ “ይህ ተቀምጦ ይለምን የነበረው አይደለምን?” አሉ። ሌሎችም “እርሱ ነው፤” አሉ፤ ሌሎች ደግሞ “እርሱን ይመስላል እንጂ፥ እርሱ አይደለም፤” አሉ፤ እርሱ “እኔ ነኝ፤” አለ። ታድያ “ዐይኖችህ እንዴት ተከፈቱ?” አሉት። እርሱ መልሶ “ኢየሱስ የሚባለው ሰው ጭቃ አድርጎ ዐይኖቼን ቀባና ‘ወደ ሰሊሆም መጠመቂያ ሄደህ ታጠብ፤’ አለኝ፤ ሄጄ ታጥቤም አየሁ፤” አለ። “ያ ሰው ወዴት ነው?” አሉት። “አላውቅም” አለ። በፊት ዐይነ ስውር የነበረውን ሰው ወደ ፈሪሳውያን ወሰዱት። ኢየሱስም ጭቃ አድርጎ ዐይኖቹን የከፈተበት ቀን ሰንበት ነበረ። ስለዚህ ፈሪሳውያን እንዴት እንዳየ እንደገና ጠየቁት። እርሱም “ጭቃ በዐይኖቼ አኖረ፤ ታጠብሁም፤ አያለሁም፤” አላቸውም። ከፈሪሳውያንም አንዳንዶቹ “ይህ ሰው ሰንበትን አያከብርምና ከእግዚአብሔር አይደለም፤” አሉ። ሌሎች ግን “ኃጢአትኛ ሰው እንደነዚህ ያሉ ምልክቶችን ሊያደርግ እንዴት ይችላል?” አሉ። በመካከላቸውም መለያየት ሆነ። ከዚህም የተነሣ ዐይነ ሥውሩን፥ “አንተ ዐይኖችህን ስለ ከፈተ፥ ስለ እርሱ ምን ትላለህ?” ደግሞ አሉት። እርሱም “ነቢይ ነው፤” አለ። አይሁድ የዚያን ማየት የቻለውን ወላጆች እስኪጠሩ ድረስ፥ ዐይን ሥውር እንደ ነበረና ማየትም እንደ ጀመረ አላመኑም፤ እነርሱንም “እናንተ ዐይን ሥውር ሆኖ ተወለደ የምትሉት ልጃችሁ ይህ ነውን? ታድያ አሁን እንዴት ያያል?” ብለው ጠየቁአቸው። ወላጆቹም መልሰው “ይህ ልጃችን እንደሆነ ዐይነ ስውርም ሆኖ እንደ ተወለደ እናውቃለን፤ ዳሩ ግን አሁን እንዴት ማየት እንደቻለ አናውቅም፤ ወይም ዐይኖቹን ማን እንደ ከፈተለት እኛ አናውቅም፤ እርሱን ጠይቁት፤ እርሱ ሙሉ ሰው ነው፤ እርሱ ስለ እራሱ መናገር ይችላል፤” አሉ። ወላጆቹ አይሁድን ስለ ፈሩ ይህንን አሉ፤ “እርሱ ክርስቶስ ነው፤” ብሎ የሚመሰክር ቢኖር ከምኵራብ እንዲያወጡት አይሁድ ከዚህ በፊት ተስማምተው ነበርና። ስለዚህ ወላጆቹ “ሙሉ ሰው ነው፤ እርሱን ጠይቁት፤” አሉ። ስለዚህ ዐይን ሥውር የነበረውን ሰው ለሁለተኛ ጊዜ ጠርተው “እግዚአብሔርን አክብር፤ ይህ ሰው ኀጢአተኛ መሆኑን እኛ እናውቃለን፤” አሉት። እርሱም መልሶ “ኀጢአተኛ መሆኑን አላውቅም፤ ዐይን ሥውር እንደ ነበርሁ፥ አሁንም እንደማይ፥ ይህንን አንድ ነገር አውቃለሁ፤” አለ።