ዮሐንስ 8:30-34
ዮሐንስ 8:30-34 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ይህንም በተናገረ ጊዜ ብዙዎች በእርሱ አመኑ። ጌታችን ኢየሱስም ያመኑበትን አይሁድ እንዲህ አላቸው፥ “እናንተም በቃሌ ጸንታችሁ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ። እውነትንም ታውቋታላችሁ፤ እውነትም አርነት ታወጣችኋለች።” እነርሱም መልሰው፥ “እኛ የአብርሃም ዘር ነን፤ ከሆነ ጀምሮ ለማንም ከቶ ባሮች አልሆንም፤ እንግዲህ እንዴት አርነት ትወጣላችሁ ትለናለህ?” አሉት። ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ኀጢኣትን የሚሠራ ሁሉ የኀጢኣት ባርያ ነው።
ዮሐንስ 8:30-34 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ይህንም እንደ ተናገረ ብዙዎች በርሱ አመኑ። ኢየሱስም በርሱ ያመኑትን አይሁድ እንዲህ አላቸው፤ “በትምህርቴ ብትጸኑ እናንተ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤ እውነትንም ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነጻ ያወጣችኋል።” እነርሱም መልሰው፣ “እኛ የአብርሃም ልጆች ነን፤ ለማንም ባሪያዎች ሆነን አናውቅም፤ ታዲያ፣ ‘ነጻ ትወጣላችሁ’ እንዴት ትለናለህ?” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ ኀጢአት የሚያደርግ የኀጢአት ባሪያ ነው፤
ዮሐንስ 8:30-34 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ይህን ሲናገር ብዙዎች በእርሱ አመኑ። ኢየሱስም ያመኑትን አይሁድ፦ “እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል” አላቸው። እነርሱም መልሰው፦ “የአብርሃም ዘር ነን ለአንድም ስንኳ ከቶ ባሪያዎች አልሆንም፤ አንተ፦ ‘አርነት ትወጣላችሁ’ እንዴት ትላለህ?” አሉት። ኢየሱስ መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ኃጢአት የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባርያ ነው።
ዮሐንስ 8:30-34 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ኢየሱስ ይህን በተናገረ ጊዜ ብዙ ሰዎች በእርሱ አመኑ። ኢየሱስ በእርሱ ላመኑት አይሁድ እንዲህ አለ፤ “እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእርግጥ ደቀ መዛሙርቴ ትሆናላችሁ፤ እውነትን ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነጻ ያወጣችኋል።” እነርሱ ግን “እኛ የአብርሃም ዘር ነን፤ ከቶ ለማንም ባሪያ ሆነን አናውቅም፤ ታዲያ፥ አንተ ‘ነጻ ትወጣላችሁ’ የምትለን እንዴት ነው?” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ ኃጢአት የሚሠራ ሁሉ የኃጢአት ባሪያ ነው፤
ዮሐንስ 8:30-34 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ይህን ሲናገር ብዙዎች በእርሱ አመኑ። ኢየሱስም ያመኑትን አይሁድ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤ እውነትንም ታውቃላችሁ፤ እውነትም አርነት ያወጣችኋል፤” እነርሱም መልሰው “የአብርሃም ዘር ነን፤ ከቶ ለማንም ባርያዎች አልሆንም፤ አንተ ‘አርነት ትወጣላችሁ፤’ እንዴት ትላለህ?” አሉት። ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ኃጢአት የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባርያ ነው።