ዮሐንስ 4:32-34
ዮሐንስ 4:32-34 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ጌታችን ኢየሱስም፥ “እኔ የምበላው እናንተ የማታውቁት ምግብ አለኝ” አላቸው። ደቀ መዛሙርቱም እርስ በርሳቸው፥ “አንዳች የሚበላው ምግብ ያመጣለት ሰው ይኖር ይሆን?” ተባባሉ። ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የእኔስ መብል የላከኝን የአባቴን ፈቃድ አደርግ ዘንድ፥ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው።
ያጋሩ
ዮሐንስ 4 ያንብቡዮሐንስ 4:32-34 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እርሱ ግን፣ “እናንተ የማታውቁት፣ የምበላው ምግብ አለኝ” አላቸው። ደቀ መዛሙርቱም፣ “ሰው ምግብ አምጥቶለት ይሆን እንዴ?” ተባባሉ። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “የእኔ ምግብ የላከኝን ፈቃድ ማድረግና ሥራውን መፈጸም ነው፤
ያጋሩ
ዮሐንስ 4 ያንብቡዮሐንስ 4:32-34 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እርሱ ግን፦ እናንተ የማታውቁት የምበላው መብል ለእኔ አለኝ አላቸው። ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ፦ የሚበላው አንዳች ሰው አምጥቶለት ይሆንን? ተባባሉ። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው።
ያጋሩ
ዮሐንስ 4 ያንብቡ