የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዮሐንስ 19:19-24

ዮሐንስ 19:19-24 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ጲላ​ጦ​ስም ጽሕ​ፈት ጽፎ በመ​ስ​ቀሉ ላይ አኖረ፤ ጽሕ​ፈ​ቱም፥ “የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ የና​ዝ​ሬቱ ኢየ​ሱስ” የሚል ነበር። ከአ​ይ​ሁ​ድም ይህ​ቺን ጽሕ​ፈት ያነ​በ​ብ​ዋት ብዙ​ዎች ነበሩ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን የሰ​ቀ​ሉ​በት ቦታ ለከ​ተማ ቅርብ ነበ​ርና፤ ጽሕ​ፈ​ቱም የተ​ጻ​ፈው በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ፥ በሮ​ማ​ይ​ስ​ጥና በግ​ሪክ ነበር። ሊቃነ ካህ​ና​ትም ጲላ​ጦ​ስን አሉት፥ “እርሱ ራሱ ‘እኔ የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ ነኝ’ እን​ዳለ እንጂ የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ ብለህ አት​ጻፍ።” ጲላ​ጦ​ስም፥ “የጻ​ፍ​ሁ​ትን ጻፍሁ” ብሎ መለ​ሰ​ላ​ቸው። ጭፍ​ሮ​ችም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን በሰ​ቀ​ሉት ጊዜ ልብ​ሶ​ቹን ወስ​ደው ከጭ​ፍ​ሮቹ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አራት ክፍል አድ​ር​ገው መደ​ቡት፤ ቀሚ​ሱ​ንም ወሰዱ፤ ቀሚ​ሱም ከላይ ጀምሮ የተ​ሠራ ሥረ​ወጥ እንጂ የተ​ሰፋ አል​ነ​በ​ረም። እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ዕጣ እን​ጣ​ጣ​ልና ለደ​ረሰ ይድ​ረ​ሰው እንጂ አን​ቅ​ደ​ደው ተባ​ባሉ፤” ይህም “ልብ​ሶ​ችን ለራ​ሳ​ቸው ተካ​ፈሉ፤ በቀ​ሚ​ሴም ላይ ዕጣ ተጣ​ጣሉ” ያለው የመ​ጽ​ሐፍ ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ነው፤ ጭፍ​ሮ​ችም እን​ዲሁ አደ​ረጉ።

ዮሐንስ 19:19-24 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ጲላጦስም ደግሞ ጽሕፈት ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረው፤ ጽሕፈቱም፦ “የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ” የሚል ነበረ። ኢየሱስም የተሰቀለበት ስፍራ ለከተማ ቅርብ ነበረና ከአይሁድ ብዙዎች ይህን ጽሕፈት አነበቡት፤ በዕብራይስጥና በሮማይስጥ በግሪክም ተጽፎ ነበር። ስለዚህ የአይሁድ ካህናት አለቆች ጲላጦስን፦ “እርሱ፦ ‘የአይሁድ ንጉስ ነኝ’ እንዳለ እንጂ የአይሁድ ንጉሥ ብለህ አትጻፍ” አሉት። ጲላጦስም፦ “የጻፍሁትን ጽፌአለሁ” ብሎ መለሰ። ጭፍሮችም ኢየሱስን በሰቀሉት ጊዜ ልብሶቹን ወስደው ለእያንዳንዱ ጭፍራ አንድ ክፍል ሆኖ በአራት ከፋፈሉት፤ እጀጠባቡን ደግሞ ወሰዱ። እጀ ጠባቡም ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበረ እንጂ የተሰፋ አልነበረም። ስለዚህ እርስ በርሳቸው፦ “ለማን እንዲሆን በእርሱ ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ አንቅደደው” ተባባሉ። ይህም፦ “ልብሴን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ በእጀ ጠባቤም ዕጣ ተጣጣሉበት” የሚለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።

ዮሐንስ 19:19-24 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ጲላጦስ “የናዝሬቱ ኢየሱስ፥ የአይሁድ ንጉሥ” የሚል ጽሑፍ ጽፎ በመስቀሉ ራስጌ ላይ አኖረው። ኢየሱስ የተሰቀለበት ስፍራ ለከተማ ቅርብ ስለ ነበር፥ ከአይሁድ ብዙዎቹ ጽሑፉን አነበቡት፤ ጽሑፉም የተጻፈው በዕብራይስጥ፥ በላቲንና በግሪክ ቋንቋ ነበር። የአይሁድ ካህናት አለቆች ጲላጦስን፥ “አንተ ‘የአይሁድ ንጉሥ’ ብለህ አትጻፍ፤ ነገር ግን ‘ይህ ሰው እኔ የአይሁድ ንጉሥ ነኝ’ ብሎአል ብለህ ጻፍ” አሉት። ጲላጦስ ግን “የጻፍኩትን ጽፌአለሁ” ሲል መለሰ። ወታደሮቹ ኢየሱስን ከሰቀሉት በኋላ፥ ልብሶቹን ወስደው፥ ለእያንዳንዱ ወታደር አንድ ክፍል እንዲደርስ በአራት ከፋፈሉአቸው፤ እጀ ጠባቡንም እንዲሁ አደረጉ፤ ነገር ግን እጀ ጠባቡ ሳይሰፋ፥ ከላይ እስከ ታች ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበር፤ ስለዚህ ወታደሮቹ “ለማን እንደሚደርስ ለማወቅ ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ፥ አንቅደደው” ተባባሉ። ይህም የሆነው፥ “ልብሴን ተከፋፈሉ፤ በእጀ ጠባቤም ዕጣ ተጣጣሉ” የሚለው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው፤ ወታደሮቹም እንዲሁ አደረጉ።

ዮሐንስ 19:19-24 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ጲላጦስም ደግሞ ጽሕፈት ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረው፤ ጽሕፈቱም “የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ” የሚል ነበረ። ኢየሱስም የተሰቀለበት ስፍራ ለከተማ ቅርብ ነበረና ከአይሁድ ብዙዎች ይህን ጽሕፈት አነበቡት፤ በዕብራይስጥና በሮማይስጥ በግሪክም ተጽፎ ነበር። ስለዚህ የአይሁድ ካህናት አለቆች ጲላጦስን “እርሱ ‘የአይሁድ ንጉሥ ነኝ’ አለ ብለህ ጻፍ እንጂ የአይሁድ ንጉሥ ብለህ አትጻፍ፤” አሉት። ጲላጦስም “የጻፍሁትን ጽፌአለሁ” ብሎ መለሰ። ወታደሮቹም ኢየሱስን በሰቀሉት ጊዜ ልብሶቹን ወስደው ለእያንዳንዱ ወታደር አንድ ክፍል እንዲደርስ በአራት ከፋፈሉአቸው፤ እጀ ጠባቡንም እንዲሁ ወሰዱ። እጀ ጠባቡ ግን ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበረ እንጂ የተሰፋ አልነበረም። ስለዚህም እርስ በርሳቸው “ለማን እንዲሆን ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ አንቅደደው” ተባባሉ። ይህም “ልብሴን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ፤ በእጀ ጠባቤም ዕጣ ተጣጣሉበት” የሚለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነበር። ወታደሮቹም እንዲህ አደረጉ።