ዮሐንስ 18:33-37

ዮሐንስ 18:33-37 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ጲላ​ጦ​ስም እን​ደ​ገና ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ ገብቶ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ጠራና፥ “የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ አንተ ነህን?” አለው። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ይህን የም​ት​ና​ገር ከራ​ስህ ነውን? ወይስ ስለ እኔ የነ​ገ​ረህ ሌላ አለን?” ብሎ መለ​ሰ​ለት። ጲላ​ጦ​ስም መልሶ፥ “እኔ አይ​ሁ​ዳዊ ነኝን? ለእኔ አሳ​ል​ፈው የሰ​ጡህ ወገ​ኖ​ች​ህና ሊቃነ ካህ​ናት አይ​ደ​ሉ​ምን? Aረ ምን አድ​ር​ገ​ሃል?” አለው። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የእኔ መን​ግ​ሥት ከዚህ ዓለም አይ​ደ​ለ​ችም፤ መን​ግ​ሥ​ቴስ በዚህ ዓለም ብት​ሆን ኖሮ ለአ​ይ​ሁድ እን​ዳ​ል​ሰጥ አሽ​ከ​ሮች በተ​ዋ​ጉ​ልኝ ነበር፤ አሁ​ንም መን​ግ​ሥቴ ከዚህ አይ​ደ​ለ​ችም” ብሎ መለ​ሰ​ለት። ጲላ​ጦ​ስም፥ “እን​ግ​ዲያ አንተ ንጉሥ ነህን?” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ራስህ ትላ​ለህ፤ እኔ ስለ​ዚህ ተወ​ለ​ድሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ለእ​ው​ነት ልመ​ሰ​ክር ወደ ዓለም መጣሁ፤ ከእ​ው​ነት የሆነ ሁሉ ቃሌን ይሰ​ማ​ኛል” አለው።