የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዮሐንስ 15:1-13

ዮሐንስ 15:1-13 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

“እው​ነ​ተኛ የወ​ይን ሐረግ እኔ ነኝ፤ ተካ​ዩም አባቴ ነው። በእኔ ያለ​ውን፥ ፍሬ የማ​ያ​ፈ​ራ​ውን ቅር​ን​ጫ​ፍም ሁሉ ያስ​ወ​ግ​ደ​ዋል፤ የሚ​ያ​ፈ​ራ​ውን ቅር​ን​ጫፍ ሁሉ ግን በብዙ እን​ዲ​ያ​ፈራ ያጠ​ራ​ዋል። እና​ንተ ግን ስለ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ቃል ፈጽ​ማ​ችሁ ንጹ​ሓን ናችሁ። በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእ​ና​ንተ፤ ቅር​ን​ጫፍ በወ​ይኑ ግንድ ከአ​ል​ኖረ ብቻ​ውን ሊያ​ፈራ እን​ደ​ማ​ይ​ችል እና​ን​ተም እን​ዲሁ በእኔ ካል​ኖ​ራ​ችሁ ፍሬ ማፍ​ራት አት​ች​ሉም። እኔ የወ​ይን ግንድ ነኝ፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹም እና​ንተ ናችሁ፤ በእኔ የሚ​ኖር እኔም በእ​ርሱ፥ ብዙ ፍሬ የሚ​ያ​ፈራ እርሱ ነው፤ ያለ እኔ ምንም ማድ​ረግ አት​ች​ሉ​ምና። በእኔ የማ​ይ​ኖር ቢኖር እንደ ደረቅ ቅር​ን​ጫፍ ወደ ውጭ ይጥ​ሉ​ታል፤ ሰብ​ስ​በ​ውም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​ታል። በእ​ኔም ብት​ኖሩ ቃሌም በእ​ና​ንተ ቢኖር የም​ት​ሹ​ትን ሁሉ ትለ​ም​ና​ላ​ችሁ፤ ይደ​ረ​ግ​ላ​ች​ሁ​ማል። ብዙ ፍሬ ብታ​ፈሩ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቴም ብት​ሆኑ በዚህ አባቴ ይከ​በ​ራል። አብ እንደ ወደ​ደኝ እን​ዲሁ ወደ​ድ​ኋ​ችሁ፤ በፍ​ቅ​ሬም ኑሩ። የም​ት​ወ​ዱኝ ብት​ሆኑ ትእ​ዛ​ዜን ጠብቁ፤ እኔ የአ​ባ​ቴን ትእ​ዛዝ እንደ ጠበ​ቅሁ፥ በፍ​ቅ​ሩም እን​ደ​ም​ኖር እና​ን​ተም ትእ​ዛ​ዜን ብት​ጠ​ብቁ በፍ​ቅሬ ትኖ​ራ​ላ​ችሁ። ደስ​ታዬ በእ​ና​ንተ ይኖር ዘንድ፥ ደስ​ታ​ች​ሁም ፍጹም ይሆን ዘንድ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ። “እኔ እንደ ወደ​ድ​ኋ​ችሁ እርስ በር​ሳ​ችሁ እን​ድ​ቷ​ደዱ የእኔ ትእ​ዛዝ ይህች ናት። ስለ ወዳ​ጆቹ ሕይ​ወ​ቱን አሳ​ልፎ የሚ​ሰጥ ሰው ያለ እንደ ሆነ ከዚህ የሚ​በ​ልጥ ፍቅር የለም።

ዮሐንስ 15:1-13 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“እውነተኛው የወይን ተክል እኔ ነኝ፤ አትክልተኛውም አባቴ ነው። እርሱም በእኔ ያለውን፣ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ቈርጦ ይጥለዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ግን የበለጠ እንዲያፈራ ይገርዘዋል። ከነገርኋችሁ ቃል የተነሣ እናንተ አሁን ንጹሓን ናችሁ። በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእናንተ እኖራለሁ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ካልሆነ በቀር ብቻውን ፍሬ ሊያፈራ አይችልም፤ እናንተም በእኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ልታፈሩ አትችሉም። “እኔ የወይን ተክል ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ማንም በእኔ ቢኖር እኔም በእርሱ ብኖር፣ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል፤ ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና። በእኔ የማይኖር ተጥሎ እንደሚደርቅ ቅርንጫፍ ነው፤ እንዲህ ያሉት ቅርንጫፎች ተለቅመው ወደ እሳት ይጣላሉ፤ ይቃጠላሉም። በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ፣ የምትፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ለምኑ፤ ይሰጣችኋልም። ብዙ ፍሬ በማፍራት ደቀ መዛሙርቴ መሆናችሁን ብትገልጡ፣ በዚህ አባቴ ይከብራል። “አብ እንደ ወደደኝ ሁሉ እኔም ወደድኋችሁ፤ በፍቅሬ ኑሩ። እኔ የአባቴን ትእዛዝ ጠብቄ በፍቅሩ እንደምኖር፣ እናንተም ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ። ደስታዬ በእናንተ እንዲሆንና ደስታችሁም ሙሉ እንዲሆን ይህን ነግሬአችኋለሁ። ትእዛዜ ይህች ናት፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። ስለ ወዳጆቹ ሕይወቱን አሳልፎ ከመስጠት የሚበልጥ ፍቅር ማንም የለውም፤

ዮሐንስ 15:1-13 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው። ፍሬ የማያፈራውን በእኔ ያለውን ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውንም ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ያጠራዋል። እናንተ ስለ ነገርኋላችሁ ቃል አሁን ንጽሐን ናችሁ፤ በእኔ ኑሩ እኔም በእንናተ። ቅርንጫፍ በወኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም። እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል። በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል ይደርቅማል፤ እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል፥ ያቃጥሉአቸውማል። በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከብራል። አብ እንደ ወደደኝ እኔ ደግሞ ወደድኋችሁ፤ በፍቅሬ ኑሩ። እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ በፍቅሩም እንደምኖር፥ ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ። ደስታዬም በእናንተ እንዲሆን ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን ነግሬአችኋለሁ። እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት። ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።

ዮሐንስ 15:1-13 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

“እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ አትክልተኛውም አባቴ ነው፤ በእኔ ላይ ያለውን ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ አባቴ ቈርጦ ይጥለዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ግን አብዝቶ እንዲያፈራ ገርዞ ያጠራዋል። እናንተም ስለ ነገርኳችሁ ቃል አሁን ንጹሖች ናችሁ። በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእናንተ እኖራለሁ፤ ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ላይ ጸንቶ ካልኖረ በቀር በራሱ ብቻ ፍሬ ማፍራት እንደማይቻለው እናንተም በእኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ማፍራት አትችሉም። “እኔ የወይን ግንድ ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ፤ ብዙ ፍሬ የሚያፈራው በእኔ የሚኖርና እኔም በእርሱ የምኖርበት ነው፤ ነገር ግን ያለ እኔ ምንም ማድረግ አትችሉም። በእኔ የማይኖር እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጪ ተጥሎ ይደርቃል፤ እንዲህ ያሉት ቅርንጫፎች ተሰብስበው ወደ እሳት ይጣሉና ይቃጠላሉ። በእኔ ብትኖሩ ቃሌም በእናንተ ቢኖር የፈለጋችሁትን ብትለምኑ ታገኛላችሁ። ብዙ ፍሬ ስታፈሩ በዚህ አባቴ ይከብራል፤ እናንተም የእኔ ደቀ መዛሙርት መሆናችሁን ታሳያላችሁ። አብ እኔን እንደ ወደደኝ እኔም እናንተን ወደድኳችሁ፤ ስለዚህ በፍቅሬ ኑሩ። እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ፈጸምኩና በፍቅሩ እንደምኖር እናንተም የእኔን ትእዛዝ ብትፈጽሙ በፍቅሬ ትኖራላችሁ። ይህን የነገርኳችሁ ደስታዬ በእናንተ እንዲሆንና የእናንተም ደስታ ፍጹም እንዲሆን ነው። የእኔ ትእዛዝ እኔ እንደ ወደድኳችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው። ሰው ሕይወቱን ስለ ወዳጆቹ አሳልፎ ከመስጠት የበለጠ ፍቅር የለውም።

ዮሐንስ 15:1-13 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

“እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው። በእኔ ያለውን ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውንም ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ያጠራዋል። እናንተ ስለ ነገርኋችሁ ቃል አሁን ንጹሐን ናችሁ፤ በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእንናተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንደማይችል፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ ማፍራት አትችሉም። እኔ የወይን ግንድ ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና፤ በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል። በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል፤ ይደርቅማል፤ እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል፤ ያቃጥሉአቸውማል። በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ፤ ይሆንላችሁማል። ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ አባቴ ይከበራል። አብ እንደ ወደደኝ እኔ ደግሞ ወደድኋችሁ፤ በፍቅሬ ኑሩ። እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ በፍቅሩም እንደምኖር፥ ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ። ደስታዬም በእናንተ እንዲሆን፥ ደስታችሁም ፍጹም እንዲሆን ይህን ነግሬአችኋለሁ። “ትእዛዜ ይህች ናት፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ። ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።

ዮሐንስ 15:1-13

ዮሐንስ 15:1-13 NASVዮሐንስ 15:1-13 NASV