የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዮሐንስ 14:15-25

ዮሐንስ 14:15-25 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“ብትወድዱኝ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ። እኔ አብን እለምናለሁ፤ እርሱም ከእናንተ ጋራ ለዘላለም የሚኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም የእውነት መንፈስ ነው፤ ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው አይችልም። እናንተ ግን፣ ዐብሯችሁ ስለሚኖርና በውስጣችሁ ስለሚሆን ታውቁታላችሁ። ወላጅ እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ ዓለም ከቶ አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ። እኔ ሕያው ስለ ሆንሁ እናንተም ሕያዋን ትሆናላችሁ። እኔ በአባቴ እንዳለሁ፣ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ፣ እኔም ደግሞ በእናንተ እንዳለሁ በዚያ ቀን ትረዳላችሁ። የሚወድደኝ ትእዛዜን ተቀብሎ የሚጠብቅ ነው፤ የሚወድደኝንም አባቴ ይወድደዋል፤ እኔም እወድደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።” ከዚያም የአስቆሮቱ ያልሆነው ይሁዳ፣ “ጌታ ሆይ፤ ታዲያ፣ ለዓለም ሳይሆን ራስህን ለእኛ የምትገልጠው እንዴት ነው?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “የሚወድደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወድደዋል፤ ወደ እርሱ እንመጣለን፤ ከርሱም ጋራ እንኖራለን። የማይወድደኝ ቃሌን አይጠብቅም። ይህ የምትሰሙት ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም። “አሁን ከእናንተ ጋራ እያለሁ ይህን ሁሉ ነግሬአችኋለሁ፤

ዮሐንስ 14:15-25 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

“ከወ​ደ​ዳ​ች​ሁ​ኝስ ትእ​ዛ​ዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለ​ም​ነ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ከእ​ና​ንተ ጋር ይኖር ዘንድ ሌላ አጽ​ናኝ ይል​ክ​ላ​ች​ኋል። እር​ሱም ዓለም ስለ​ማ​ያ​የ​ውና ስለ​ማ​ያ​ው​ቀው ሊቀ​በ​ለው የማ​ይ​ቻ​ለው የእ​ው​ነት መን​ፈስ ነው፤ እና​ንተ ግን ታው​ቁ​ታ​ላ​ችሁ፤ በእ​ና​ንተ ዘንድ ይኖ​ራ​ልና፤ ያድ​ር​ባ​ች​ሁ​ማ​ልና። “የሙት ልጆች ትሆኑ ዘንድ አል​ተ​ዋ​ች​ሁም፤ ወደ እና​ንተ እመ​ጣ​ለሁ። ገና ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ዓለም አያ​የ​ኝም፤ እና​ንተ ግን ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና፤ እና​ን​ተም ሕያ​ዋን ትሆ​ና​ላ​ችሁ። እኔ በአብ እን​ዳ​ለሁ፥ አብም በእኔ እን​ዳለ፥ እና​ን​ተም በእኔ፥ እኔም በእ​ና​ንተ እን​ዳ​ለሁ ያን​ጊዜ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። ትእ​ዛዜ በእ​ርሱ ዘንድ ያለ የሚ​ጠ​ብ​ቀ​ውም የሚ​ወ​ደኝ እርሱ ነው፤ የሚ​ወ​ደ​ኝ​ንም አባቴ ይወ​ደ​ዋል፤ እኔም እወ​ደ​ዋ​ለሁ፤ ራሴ​ንም እገ​ል​ጥ​ለ​ታ​ለሁ።” የአ​ስ​ቆ​ሮቱ ሰው ያይ​ደለ ይሁ​ዳም፥ “ጌታ ሆይ፥ ለዓ​ለም ያይ​ደለ ለእኛ ራስ​ህን ትገ​ልጥ ዘንድ እን​ዳ​ለህ የተ​ና​ገ​ር​ኸው ምን​ድን ነው?” አለው። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ አለው፥ “የሚ​ወ​ደኝ ቃሌን ይጠ​ብ​ቃል፤ አባ​ቴም ይወ​ደ​ዋል፤ ወደ እር​ሱም መጥ​ተን በእ​ርሱ ዘንድ ማደ​ሪያ እና​ደ​ር​ጋ​ለን። የማ​ይ​ወ​ደኝ ግን ቃሌን አይ​ጠ​ብ​ቅም፤ ይህም የም​ት​ሰ​ሙት ቃል የላ​ከኝ የአብ ቃል ነው እንጂ የእኔ ቃል አይ​ደ​ለም። “ከእ​ና​ን​ተም ጋር ሳለሁ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ።

ዮሐንስ 14:15-25 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“ብትወድዱኝ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ። እኔ አብን እለምናለሁ፤ እርሱም ከእናንተ ጋራ ለዘላለም የሚኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም የእውነት መንፈስ ነው፤ ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው አይችልም። እናንተ ግን፣ ዐብሯችሁ ስለሚኖርና በውስጣችሁ ስለሚሆን ታውቁታላችሁ። ወላጅ እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ ዓለም ከቶ አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ። እኔ ሕያው ስለ ሆንሁ እናንተም ሕያዋን ትሆናላችሁ። እኔ በአባቴ እንዳለሁ፣ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ፣ እኔም ደግሞ በእናንተ እንዳለሁ በዚያ ቀን ትረዳላችሁ። የሚወድደኝ ትእዛዜን ተቀብሎ የሚጠብቅ ነው፤ የሚወድደኝንም አባቴ ይወድደዋል፤ እኔም እወድደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።” ከዚያም የአስቆሮቱ ያልሆነው ይሁዳ፣ “ጌታ ሆይ፤ ታዲያ፣ ለዓለም ሳይሆን ራስህን ለእኛ የምትገልጠው እንዴት ነው?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “የሚወድደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወድደዋል፤ ወደ እርሱ እንመጣለን፤ ከርሱም ጋራ እንኖራለን። የማይወድደኝ ቃሌን አይጠብቅም። ይህ የምትሰሙት ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም። “አሁን ከእናንተ ጋራ እያለሁ ይህን ሁሉ ነግሬአችኋለሁ፤

ዮሐንስ 14:15-25 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

“ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ በዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ። “ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። ገና ጥቂት ዘመን አለ ከዚህም በኋላ ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ። እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ። ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትንም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።” የአስቆሮቱ ያይደለ ይሁዳ፦ “ጌታ ሆይ፥ ለዓለም ሳይሆን ራስህን ለእኛ ልትገልጥ ያለህ እንዴት ነው?” አለው። ኢየሱስም መለሰ አለውም፦ “የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን። የማይወደኝ ቃሌን አይጠብቅም፤ የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም። ከእናንተ ዘንድ ስኖር ይህን ነግሬአችኋለሁ፤

ዮሐንስ 14:15-25 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

“የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዜን ጠብቁ፤ እኔ አብን እለምነዋለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ከእናንተ ጋር የሚኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል። ይህም የእውነት መንፈስ ነው፤ ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው አይችልም፤ እናንተ ግን፥ እርሱ ከእናንተ ጋር ስለ ሆነና በውስጣችሁም ስላለ ታውቁታላችሁ። “እናትና አባት እንደሌላቸው ልጆች ብቻችሁን አልተዋችሁም፤ ተመልሼ ወደ እናንተ እመጣለሁ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ስለ ሆንኩ እናንተም በሕይወት ትኖራላችሁ፤ እኔ በአብ እንዳለሁ፥ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ፥ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ። “እኔን የሚወደኝ ትእዛዜን የሚቀበልና በሥራ ላይ የሚያውለው ነው፤ እኔንም የሚወደኝን አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።” አስቆሮታዊው ሳይሆን ሌላው ይሁዳ፥ “ጌታ ሆይ! ራስህን ለዓለም ሳይሆን ለእኛ የምትገልጠው እንዴት ነው?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “የሚወደኝ ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፤ እኛ ወደ እርሱ መጥተን ከእርሱ ጋር አብረን እንኖራለን። የማይወደኝ ቃሌን አይጠብቅም፤ ይህ የምትሰሙት ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም። “አሁን ከእናንተም ጋር እያለሁ ይህን ነገር ነግሬአችኋለሁ፤

ዮሐንስ 14:15-25 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

“የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ። እኔም አብን እለምናለሁ፤ ለዘለዓለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ምክንያቱም ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ነው። ነገር ግን በእናንተ ዘንድ ስለሚኖር፥ በውስጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቁታላችሁ። “ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። ገና ጥቂት ዘመን አለ፤ ከዚህም በኋላ ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና፤ እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ። እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ። ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትንም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።” የአስቆሮቱ ሳይሆን ሌላኛው ይሁዳ “ጌታ ሆይ! ለዓለም ሳይሆን ለእኛ ራስህን የምትገልጠው እንዴት ነው?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን፤ በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን። የማይወደኝ ቃሌን አይጠብቅም፤ የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም። “በእናንተ ዘንድ ስኖር ይህን ነግሬአችኋለሁ፤