የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዮሐንስ 14:1-10

ዮሐንስ 14:1-10 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

“ልባ​ችሁ አይ​ደ​ን​ግጥ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እመኑ፤ በእ​ኔም እመኑ። በአ​ባቴ ቤት ብዙ ማደ​ሪ​ያና ማረ​ፊያ አለ፤ እን​ዲ​ህስ ባይ​ሆን ኖሮ ቦታ ላዘ​ጋ​ጅ​ላ​ችሁ እሄ​ዳ​ለሁ እላ​ችሁ ነበር። ከሄ​ድ​ሁና ቦታ ካዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ላ​ች​ሁም ዳግ​መኛ እመ​ጣ​ለሁ፤ እና​ን​ተም እኔ በአ​ለ​ሁ​በት ትኖሩ ዘንድ ወደ እኔ እወ​ስ​ዳ​ች​ኋ​ለሁ። ወዴ​ትም እን​ደ​ም​ሄድ ራሳ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ መን​ገ​ዱ​ንም ታው​ቃ​ላ​ችሁ።” ቶማ​ስም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ የም​ት​ሄ​ድ​በ​ትን የማ​ና​ውቅ እን​ግ​ዲህ መን​ገ​ዱን እን​ዴት እና​ው​ቃ​ለን?” አለው። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “የእ​ው​ነ​ትና የሕ​ይ​ወት መን​ገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካል​ሆነ በቀር ወደ አብ የሚ​መጣ የለም። እኔ​ንስ ብታ​ው​ቁኝ አባ​ቴ​ንም ባወ​ቃ​ች​ሁት ነበር፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ግን አው​ቃ​ች​ሁ​ታል፤ አይ​ታ​ች​ሁ​ት​ማል።” ፊል​ጶ​ስም፥ “ጌታ ሆይ፥ አብን አሳ​የ​ንና ይበ​ቃ​ናል” አለው። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “ፊል​ጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን አብ​ሬ​አ​ችሁ ስኖር አታ​ወ​ቀ​ኝ​ምን? እኔን ያየ አብን አየ፤ እን​ግ​ዲህ እን​ዴት አብን አሳ​የን ትላ​ለህ? እኔ በአብ እን​ዳ​ለሁ አብም በእኔ እን​ዳለ አታ​ም​ን​ምን? እኔ የም​ነ​ግ​ራ​ችሁ ይህ ቃልም ከራሴ የተ​ና​ገ​ር​ሁት አይ​ደ​ለም፤ በእኔ ያለ አብ እርሱ ይህን ሥራ ይሠ​ራ​ዋል እንጂ።

ዮሐንስ 14:1-10 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“ልባችሁ አይጨነቅ፤ በእግዚአብሔር እመኑ ፤ በእኔም ደግሞ እመኑ። በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ ይህ ባይሆንማ ኖሮ እነግራችሁ ነበር፤ የምሄደውም ስፍራ ላዘጋጅላችሁ ነው። ሄጄም ስፍራ ካዘጋጀሁላችሁ በኋላ፣ እኔ ባለሁበት እናንተም ከእኔ ጋር እንድትሆኑ ልወስዳችሁ ዳግመኛ እመጣለሁ። እኔ ወደምሄድበትም ስፍራ የሚያደርሰውን መንገድ ታውቃላችሁ።” ቶማስም፣ “ጌታ ሆይ፤ ወዴት እንደምትሄድ አናውቅም፤ ታዲያ፣ መንገዱን እንዴት ማወቅ እንችላለን?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ባወቃችሁት ነበር። ከአሁን ጀምሮ ግን ታውቁታላችሁ፤ አይታችሁታልም።” ፊልጶስም፣ “ጌታ ሆይ፤ አብን አሳየንና ይበቃናል” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “አንተ ፊልጶስ! ይህን ያህል ጊዜ ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቷል፤ እንዴትስ፣ ‘አብን አሳየን’ ትላለህ? እኔ በአብ እንዳለሁ፣ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? የምነግራችሁ ቃል ከራሴ አይደለም፤ ነገር ግን ሥራውን የሚሠራው በእኔ የሚኖረው አብ ነው።

ዮሐንስ 14:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

“ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ። ወደምሄድበትም ታውቃላችሁ፥ መንገዱንም ታውቃላችሁ።” ቶማስም፦ “ጌታ ሆይ፥ ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን?” አለው። ኢየሱስም፦ “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር። አሁንም ጀምራችሁ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል” አለው። ፊልጶስ፦ “ጌታ ሆይ፥ አብን አሳየንና ይበቃናል” አለው። ኢየሱስም አለው፦ “አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ፦ ‘አብን አሳየን’ ትላለህ? እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እኔ የምነገራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል።

ዮሐንስ 14:1-10 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ልባችሁ አይጨነቅ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም እመኑ፤ በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ አለበለዚያ ግን ‘የምትኖሩበትን ስፍራ ላዘጋጅላችሁ እሄዳለሁ’ ባልኳችሁ ነበር። ሄጄ ስፍራ ካዘጋጀሁላችሁ በኋላ እኔ ባለሁበት እንድትኖሩ እንደገና መጥቼ እወስዳችኋለሁ። እኔ የምሄድበትንም መንገድ ታውቃላችሁ።” ቶማስ “ጌታ ሆይ! ወዴት እንደምትሄድ አናውቅም፤ ታዲያ፥ መንገዱን እንዴት ማወቅ እንችላለን?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “መንገድና እውነት ሕይወትም እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ማንም ወደ አብ የሚመጣ የለም። እኔን ዐውቃችሁኝ ቢሆን ኖሮ አባቴንም ባወቃችሁት ነበር፤ ከእንግዲህ ወዲህ ግን ታውቁታላችሁ፤ አይታችሁታልም።” ፊልጶስም “ጌታ ሆይ! አብን አሳየንና ይበቃናል” አለው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ፊልጶስ ሆይ! ይህን ያኽል ጊዜ ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አየ፤ ታዲያ፥ አንተ ‘አብን አሳየን’ እንዴት ትላለህ? እኔ በአብ እንዳለሁ፥ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? ለእናንተ የምናገረውን ቃል የምናገረው በራሴ ሥልጣን አይደለም፤ ነገር ግን ሥራውን ሁሉ የሚሠራው፥ በእኔ የሚኖረው አብ ነው።

ዮሐንስ 14:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

“ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም ደግሞ እመኑ። በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ኖሮ ስፍራ ላዘጋጅላችሁ እሄዳለሁ እላችሁ ነበርን? ሄጄም ስፍራ ሳዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተም እንድትኖሩ ዳግምኛ እመጣለሁ፤ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ። የምሄድበትንም መንገድ ታውቃላችሁ።” ቶማስም “ጌታ ሆይ! ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን?” አለው። ኢየሱስም “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ ማንም ወደ አብ የሚመጣ የለም። እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ባወቃችሁት ነበር። ከአሁንም ጀምሮ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል፤” አለው። ፊልጶስ “ጌታ ሆይ! አብን አሳየንና ይበቃናል” አለው። ኢየሱስም አለው “አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ ‘አብን አሳየን’ ትላለህ? እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እኔ የምነገራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ ሥራውን ይሠራል።

ዮሐንስ 14:1-10

ዮሐንስ 14:1-10 NASVዮሐንስ 14:1-10 NASVዮሐንስ 14:1-10 NASV