የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዮሐንስ 12:35-46

ዮሐንስ 12:35-46 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ ገና ለጥ​ቂት ጊዜ ብር​ሃን ከእ​ና​ንተ ጋር ነው፤ በጨ​ለማ የሚ​መ​ላ​ለስ የሚ​ሄ​ድ​በ​ትን አያ​ው​ቅ​ምና ጨለማ እን​ዳ​ያ​ገ​ኛ​ችሁ ብር​ሃን ሳለ​ላ​ችሁ ተመ​ላ​ለሱ፤ የብ​ር​ሃን ልጆች ትሆኑ ዘንድ ብር​ሃን ሳለ​ላ​ችሁ በብ​ር​ሃን እመኑ” ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ተና​ግሮ ሄደ፤ ተሰ​ወ​ራ​ቸ​ውም። ይህ​ንም ያህል ተአ​ም​ራት በፊ​ታ​ቸው ሲያ​ደ​ርግ አላ​መ​ኑ​በ​ትም። “አቤቱ፥ ምስ​ክ​ር​ነ​ታ​ች​ንን ማን ያም​ነ​ናል? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ክንድ ለማን ተገ​ለጠ?” ያለው የነ​ቢዩ የኢ​ሳ​ይ​ያስ ቃል ይደ​ርስ ዘንድ። ስለ​ዚ​ህም ማመን ተሳ​ና​ቸው፤ ኢሳ​ይ​ያስ ዳግ​መኛ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና። “በዐ​ይ​ና​ቸው አይ​ተው፥ በል​ባ​ቸ​ውም አስ​ተ​ው​ለው እን​ዳ​ይ​መ​ለ​ሱና እን​ዳ​ል​ፈ​ው​ሳ​ቸው ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው ታወሩ፤ ልባ​ቸ​ውም ደነ​ደነ።” ኢሳ​ይ​ያስ ጌት​ነ​ቱን አይ​ቶ​አ​ልና፥ ይህን ተና​ገረ፤ ስለ እር​ሱም መሰ​ከረ። ከሕ​ዝቡ አለ​ቆ​ችም ያመ​ኑ​በት ብዙ​ዎች ነበሩ፤ ነገር ግን ከም​ኵ​ራብ አስ​ወ​ጥ​ተው እን​ዳ​ይ​ሰ​ዱ​አ​ቸው በፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ምክ​ን​ያት አል​መ​ሰ​ከ​ሩ​ለ​ትም። ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ይልቅ የሰ​ውን ክብር ወደ​ዋ​ልና። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ እን​ዲህ አለ፥ “በእኔ የሚ​ያ​ምን በላ​ከ​ኝም ነው እንጂ በእኔ ብቻ የሚ​ያ​ምን አይ​ደ​ለም። እኔን ያየ የላ​ከ​ኝን አየ። በእኔ የሚ​ያ​ምን ሁሉ በጨ​ለማ እን​ዳ​ይ​ኖር ብር​ሃን እኔ ወደ ዓለም መጣሁ።

ዮሐንስ 12:35-46 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ኢየሱስም እንዲህ ሲል ተናገራቸው፤ “ከእንግዲህ ለጥቂት ጊዜ ብርሃን አለላችሁ፤ ጨለማ ሳይመጣባችሁ፣ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማ የሚመላለስ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም። የብርሃን ልጆች እንድትሆኑ ብርሃን ሳለላችሁ በዚህ ብርሃን እመኑ።” ኢየሱስ ይህን ተናግሮ እንደ ጨረሰ ተለያቸው፤ ተሰወረባቸውም። ኢየሱስ እነዚህን ታምራዊ ምልክቶች ሁሉ በፊታቸው ቢያደርግም እንኳ፣ አሁንም አላመኑበትም፤ ይኸውም ነቢዩ ኢሳይያስ፣ “ጌታ ሆይ፤ ምስክርነታችንን ማን አመነ? የጌታ ክንድስ ለማን ተገለጠ?” ያለው ቃል እንዲፈጸም ነው። ስለዚህ ማመን አልቻሉም፤ ይህም ኢሳይያስ በሌላ ቦታ እንዲህ ሲል እንደ ተናገረው ነው፤ “ዐይናቸውን አሳውሯል፤ ልባቸውንም አደንድኗል፤ ስለዚህ በዐይናቸው አያዩም፤ በልባቸውም አያስተውሉም፤ እንዳልፈውሳቸውም አይመለሱም።” ኢሳይያስ ይህን ያለው የኢየሱስን ክብር ስላየ ነው፤ ስለ እርሱም ተናገረ። ይህም ቢሆን፣ ከአለቆች መካከል እንኳ ሳይቀር ብዙዎች በእርሱ አመኑ፤ ይሁን እንጂ ፈሪሳውያን ከምኵራብ እንዳያስወጧቸው ስለ ፈሩ ማመናቸውን አይገልጡም ነበር። ይህም የሆነው በእግዚአብሔር ከመመስገን ይልቅ በሰው መመስገንን ስለ ወደዱ ነው። ከዚያም ኢየሱስ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፤ “ማንም በእኔ ቢያምን በእኔ ብቻ ሳይሆን በላከኝም ማመኑ ነው፤ እኔንም የሚያይ የላከኝን ያያል። በእኔ የሚያምን በጨለማ እንዳይኖር ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ።

ዮሐንስ 12:35-46 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ኢየሱስም፦ “ገና ጥቂት ጊዜ ብርሃን ከእናንተ ጋር ነው። ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማም የሚመላለስ ወዴት እንዲሄድ አያውቅም። የብርሃን ልጆች እንድትሆ ብርሃን ሳለላችሁ በብርሃኑ እመኑ” አላቸው። ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ሄደና ተሰወረባቸው። ነገር ግን ይህን ያህል ምልክት በፊታቸው ምንም ቢያደርግ፤ ነቢዩ ኢሳይያስ፦ “ጌታ ሆይ፥ ማን ምስክርነታችንን አመነ? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ?” ብሎ የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ በእርሱ አላመኑም። ኢሳይያስ ደግሞ፦ “በዓይኖቻቸው እንዳያዩ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ እንዳይመለሱም፥ እኔም እንዳልፈውሳቸው፥ ዓኖቻቸውን አሳወረ ልባቸውውንም አደነደነ” ብሎአልና ስለዚህ ማመን አቃታቸው። ክብሩን ስለ አየ ኢሳይያስ ይህን አለ፥ ስለ እርሱም ተናገረ። ከዚህም ጋር ከአለቆች ደግሞ ብዙዎች በእርሱ አመኑ፤ ነገር ግን ከምኵራብ እንዳያስወጡአቸው በፈሪሳውያን ምክንያት አልመሰከሩለትም፤ ከእግዚአብሔር ክብር ይልቅ የሰውን ክብር ወደዋልና። ኢየሱስም ጮኸ፥ እንዲህም አለ፦ “በእኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በእኔ አይደለም፤ እኔንም የሚያይ የላከኝን ያያል። በእኔ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር እኔ ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ።

ዮሐንስ 12:35-46 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “አሁን ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ብርሃን አለ፤ ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማ የሚመላለስ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም። የብርሃን ልጆች እንድትሆኑ ብርሃን ሳለላችሁ በብርሃን እመኑ።” ኢየሱስ ይህን ከተናገረ በኋላ ሄደና ተሰወረባቸው። ኢየሱስም ብዙ ተአምራትን በፊታቸው ቢያደርግም እንኳ አይሁድ በእርሱ አላመኑም። ይህም የሆነው ነቢዩ ኢሳይያስ፥ “ጌታ ሆይ! ምስክርነታችንን ማን አመነ? የጌታስ ኀይል ለማን ተገለጠ?” ሲል የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው። እንደገናም ኢሳይያስ እንዲህ ሲል አለማመናቸውን ገለጠ፦ “በዐይናቸው አይተውና በልባቸው አስተውለው እንዳይመለሱና እንዳይፈውሳቸው እግዚአብሔር ዐይናቸውን አሳውሮአል፤ ልባቸውንም አደንድኖአል።” ኢሳይያስ ይህን ያለው የመሲሕን ክብር ስላየ ነው፤ ስለዚህ ይህን ስለ ኢየሱስ ተናገረ። ሆኖም ከአይሁድ አለቆች እንኳ ብዙዎቹ በኢየሱስ አምነዋል፤ ነገር ግን ፈሪሳውያን ከምኲራብ እንዳያስወጡአቸው በመፍራት፥ በግልጥ አልመሰከሩለትም። ይህንንም ያደረጉት ከእግዚአብሔር ከሚገኘው ክብር ይልቅ ከሰው የሚገኘውን ክብር ስለ ወደዱ ነው። ኢየሱስም ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ “በእኔ የሚያምን በእኔ ብቻ ሳይሆን፥ በላከኝም ያምናል፤ እኔን የሚያይ የላከኝን ያያል፤ በእኔ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር እኔ ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ።

ዮሐንስ 12:35-46 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ኢየሱስም “ገና ጥቂት ጊዜ ብርሃን ከእናንተ ጋር ነው። ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማም የሚመላለስ ወዴት እንዲሄድ አያውቅም። የብርሃን ልጆች እንድትሆኑ ብርሃን ሳለላችሁ በብርሃኑ እመኑ፤” አላቸው። ኢየሱስም ይህን ከተናገረ በኋላ ሄዶ ተሰወረባቸው። ነገር ግን ይህን ያህል ምልክት በፊታቸው ምንም ቢያደርግም፤ እነርሱ ግን በእርሱ አላመኑም። ይህም ነቢዩ ኢሳይያስ “ጌታ ሆይ! ማን ምስክርነታችንን አመነ? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ?” ብሎ የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው። ስለዚህ ማመን ተሳናቸው፤ ኢሳይያስ እንዲህ ብሎአልና፥ “በዐይኖቻቸው እንዳያዩ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ እንዳይመለሱም፥ እኔም እንዳልፈውሳቸው፥ ዐኖቻቸውን አሳወረ፤ ልባቸውውንም አደነደነ።” ክብሩን ስላየ ኢሳይያስ ይህን አለ፤ ስለ እርሱም ተናገረ። ከዚህም ጋር ከአለቆች ደግሞ ብዙዎች በእርሱ አመኑ፤ ነገር ግን ከምኵራብ እንዳያስወጡአቸው በፈሪሳውያን ምክንያት አልመሰከሩለትም፤ ከእግዚአብሔር ክብር ይልቅ የሰውን ክብር ወደዋልና። ኢየሱስም ጮኸ፤ እንዲህም አለ “በእኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በእኔ አይደለም፤ እኔንም የሚያይ የላከኝን ያያል። በእኔ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር እኔ ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ።